Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል፡፡ | Natnael Mekonnen

በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከብክለት ነፃ የሆኑ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የሚኒባስ ተሽከርካሪዎችን ከማዕከል እስከ ወረዳ ላሉ ተቋማት አስረክቧል።

ብክለትን በመከላከል ረገድ ፋይዳቸው ጉልህ የሆኑ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችም ከተማዋን ፅዱ ለማድረግ እንዲሁም ወጪም ለመቆጠብ የሚያስችሉ ሲሆን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ግዥና ስርጭትም አዲስ አበባን ውብና ፅዱ እንዲሁም ከአካባቢ ስነምህዳር ጋር የተስማማች ከተማ የማድረግ ውጥን አካል እንደሆነ ክብርት ከንቲባ ኣዳነች ኣቤቤ ተነግሯል። ኣክለውም ከዚህም ባሻገር ያለንን የኤሌክትሪክ ሀይል በመጠቀም ለነዳጅ የሚወጣው የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ ስለሚያስችለን ፊታችንን በኤሌክትሪክ ወደ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ማዞር እንደሚገባ መግለፃቸውን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።