Get Mystery Box with random crypto!

ሀብት ከአገር የሚያሸሹ ግለሰቦችን ለመቅጣት የሚያስችል አዋጅ እየተዘጋጀ ነው ተባለ የሥነ ምግባር | Natnael Mekonnen

ሀብት ከአገር የሚያሸሹ ግለሰቦችን ለመቅጣት የሚያስችል አዋጅ እየተዘጋጀ ነው ተባለ

የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሀብት ከአገር የሚያሸሹ ግለሰቦች ላይ አስፈላጊውን ቅጣት ለመጣል የሚያስችል አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

አዋጁ ያካተታቸው ዝርዝር ጉዳዮች ወደፊት ይፋ እንደሚደረጉ የተገለጸ ሲሆን የፍትሕ ሚኒስቴርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አንድ ላይ በመሆን በዋናነት አዋጁን እያዘጋጁ መሆናቸውንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም እየተሳተፉበት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ፖሊስ፣ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎትና ሌሎችም ተቋማት በጋራ በመሆን የሚሸሹ ሀብቶችን ለመከላከል የጋራ ኮሚቴ መቋቋሙም ተመላክቷል፡፡