Get Mystery Box with random crypto!

በኬሌ ከተማ በተከሰተው የእሳት አደጋ ቤቶች መቃጠላቸው ተገለጸ በአማሮ ልዩ ወረዳ በኬሌ ከተማ | Natnael Mekonnen

በኬሌ ከተማ በተከሰተው የእሳት አደጋ ቤቶች መቃጠላቸው ተገለጸ

በአማሮ ልዩ ወረዳ በኬሌ ከተማ አስተዳደር በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ አንድ ምግብ ቤት ሙሉ ለሙሉ እና 3 ቤቶች ደግሞ በከፊል መውደማቸውን የከተማው ፖሊስ አስታውቋል።

የኬሌ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት መረጃ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ኢንስፔክተር ጌታነህ ተስፋዬ ትላንት በግምት ከቀኑ 4:30 በንግድ ባንክ አካባቢ አቶ ባይሳ ካሌብ በተባለ ግለሰብ ሱቅ ቤንዚል ሲቀዳ ከሙቀት ጋር ተያይዞ ድንገተኛ የእሳት አደጋ እንደተነሳ አስረድተዋል፡፡

ተመሳሳይ አደጋ ሲከሰት ይህ ለ3ኛ ጊዜ እንደሆነ ያስታወሱት ዳይሬክተሩ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰባቸውን የወረዳው ኮሚውኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።