Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 174.28K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 390

2022-05-21 16:03:17
አዲሱ ''ጫካ ፕሮጀክት'' ምንድን ነው?

#Ethiopia : የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ49 ቢሊዮን ብር አዲስ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ይህም 130 ቢሊዮን ብር በላይ ከሚፈጀው ከህዳሴው ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ ሀገራዊ ፕሮጀክት ይሆናል ተብሏል።

ይህ በመዲናዋ በየካ ክፍለከተማ በየካ ተራራ ላይ የሚገነባው አዲሱ ቤተመንግሥት በ503 ሄክታር መሬት ላይ ያርፋል ተብሏል። አምስት ወረዳዎችንም የሚነካ ሲሆን በውስጡም የአዳራሽ፣ የሰው ሰራሽ ሀይቅ፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የመንገድ ጨምሮ ሌሎች ግንባታዎችን ያካትታል።

በግንባታው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚፈናቀሉ ሲሆን ሆኖም ነዋሪዎቹ ቤተ መንግሥቱ የሚታነፅበት አካባቢ ካለው ደረጃ ጋር የሚስማማ ከሆነ በመሬታቸው ላይ የራሳቸውን ንብረት እንዲያለሙ ዕድል ይሰጣቸዋል ተብሏል።

እንደ ሪፖርተር ዘገባ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት መንግስት የተወሰነውን ወጪ የሚሸፍን እንደሚሆን ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በአካባቢው 20 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ መገንባት የጀመረ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ ተሰርቶ ተጠናቋል። የመንገድ ግንባታው ብቻውንም 15 ቢሊዮን ብር ይፈጃል ተብሏል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አዲሱን የቤተመንግሥት ግንባታ “ጫካ ፕሮጀክት” ብለው የሰየመው ሲሆን አዲስ የሚገነባው የብሄራዊ ቤተ መንግስት አካል የሆኑ ሦስት ሰው ሰራሽ ሀይቆች ግንባታን በውስጡ ይዟል።

በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚንስትር መኖሪያና ጽ/ቤት ሆኖ እያገለገለ የሚገኘው የምኒልክ ቤተ መንግሥትን በአንድ ቢሊዮን ብር እድሳት ላይ ካለው የኢዮቤልዩ ቤተ-መንግስት ጋር ወደ ብሔራዊ ሙዚየምነት ሊቀየር ታስቧል።
32.9K views13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 14:58:29
የቀድሞ የዩክሬን አርቲስት/ኮሜዲያን ያሁኑ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ በተለያዩ ሃገራት ያለው የሩሲያ ሃብት ተወርሶ ዩክሬንን ለመገንባት እንዲውል ጠየቁ ሃብቱ ለዩክሬናውያን ካሳ ነው ያሉት ዜሌንስኪ በሩሲያ የወደሙ መሰረተ ልማቶች ይገነቡበታል ብለዋል

ዜሌንስኪ ወዳጅ ሃገራት ሃሳባቸውን ተቀብለው እንዲፈርሙ ጠይቀዋል የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በተለያዩ ሃገራት ያለው የሩሲያ ሃብት ተወርሶ ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት እንዲውል ጠየቁ፡፡ ዜሌንስኪ የዩክሬን ወዳጅ ሃገራት ሃሳቡን ተቀብለው እንዲፈርሙ ጠይቀዋል፡፡

ሩሰያ ዩክሬንን በቻለችው ሁሉ እያወደመች ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ለዚህ መክፈል አለባት ብለዋል፡፡ በመሆኑም ወዳጆቻችን ተፈራርመን በሩሲያ ድርጊት የተጎዱ ዩክሬናውያን ሁሉ የሚካሱበትን መንገድ ማመቻቸት እንፈልጋለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ፊርማው በወዳጅ ሃገራቱ የሚገኝ የሩሲያን ሃብት ለመውረስ የሚያስችል ነው፡፡ ሃብቱ ወደሚቋቋመው ልዩ የካሳ ፈንድ የሚገባ ይሆናል፡፡

"ሩሲያም ወደ እኛ ስትተኩስ የነበረው እያንዳንዱ ሚሳዔል እና ቦምብ እንዲሰማት ማድረጉ ፍትሐዊ ነው" ሲሉም ነው ዜሌንስኪ የተናገሩት፡፡ ካናዳ ባሳለፍነው ሳምንት በእግድ የተያዙ ንብረቶች ተመልሰው ተጎጂዎችን ለመካስ በሚያስችል መልኩ ህጓን እንደምታሻሽል ማስታወቋ ይታወሳል፡፡
32.7K views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 14:40:52
ሩሲያ ፊንላንድና ስዊድን ኔቶን ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተከትሎ 12 አዳዲስ እዞችን እንደምታቋቁም አስታወቀች

ሩሲያ፤ ፊንላንድ እና ስዊድን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተከትሎ የአፀፋ እርምጃ መውሰድ መጀመሯን አስታወቀች።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጊ ሾይጉ በሰጡት አስተያየት፤ ፊንላንድ እና ስዊድን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) ለመቀላቀል መወሰናቸው በሩሲያ ድንበር አካባቢ ወታደራዊ ስጋቶች እንዲጨምሩ ያደርጋል ብለዋል።

ይህንን ተከትሎም ሩሲያ አስፈላጊ የሆኑ የአፀፋ እርምጃዎችን መውሰድ እንደጀመረች መግለጻቸውን ኢንትራፋክስ የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል።
30.9K views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 14:20:04 በሰሜን ጎንደር ዞን ስር ያሉ ሁሉም ያልተፈተኑና ፈተናውን ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በቀጣይ አመት እንደሚፈተኑ ተገለጸ።

ተማሪዎቹ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት ሃገር አቀፍ ፈተናውን ያልወሰዱና ፈተናውንም ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በቀጣይ አመት በሚሰጠው ፈተና ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከክልል በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የቲቶሪያል ትምህርት በወረዳቸው ከሚገኘው አዲምህረት ትምህርት ቤት ከግንቦት ወር ጀምሮ እንደሚሰጡ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ አጸደ በሬ አሳውቀዋል።

በቀጣይ ሁለት የክረምት ወራቶች የማጠናከሪያ ትምህርት እንደሚሰጥ የገለጹት ወ/ሮ አጸደ በሬ በተለያዩ ምክንያት ከወረዳው ውጭ የሚገኙ ተማሪዎችንና ወደ ወረዳው መሄድ የማይችሉ ተማሪዎችን የተማሪ መታወቂያ አይዲ ካርድ ይዘው በደባርቅ ከተማ መሰናዶ ትምህርት ቤት ከአዲ አርቃይ ከተማ ተማሪዎች ጋር መማር እንደሚችሉ አሳውቀዋል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በሰሜኑ የሃገሪቷ ክፍል በነበረው ጦርነት በተማሪዎች ውጤት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተገንዝቦ በ2013 ዓ.ም ኦንላይን ተመዝግበው ሃገር አቀፍ የ 12ኛ ክፍል ፈተና ያልወሰዱና ፈተናውን ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች ከ 2014 ዓ.ም ተፈታኞች ጋር በድጋሚ ፈተናውን እንዲፈተኑ ከሃገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር በጋራ መወሰናቸው የሚታወስ ነው።
29.9K views11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 14:19:12
ሉሃንስክ ህዝባዊት ሪፐብሊክን ነጻ ለማውጣት ተቃርበናል - ሩሲያ

ዶንባስ የተሰኘውን የዩክሬን ግዛት ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር መቃረቡን የገለጸው የሩሲያ ጦር ሉሃንስክ ህዝባዊት ሪፐብሊክን ነጻ ለማውጣት ከምችልበት የዘመቻ ምዕራፍ ላይ ደርሻለሁ ብሏል፡፡
27.6K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 14:19:01
የጆሮ የመስማት አቅም ማነስ ድምፅን ከሩቅ ለመስማት እንዳነቸገር 0911284905 ይደውሉል
HEARING AID
በተመጣጣኝ ዋጋ 6800birr ከ 2 አመት ዋስትናጋ
ይደውሉልን ያሉበት ድረስ እናደርሳለን

-በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ላለ የሚሆን
-በዛላይ ለአደራረግ እና ቢታይ ቀለል ያለ
-ለሁለቱም ጆሮ ለሚፈልጎ ማድረግ የሚችሉት
-ቻርጅ ተደርጎ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ
-እራሱላይ ፓወር ባንክ ያለው

በተለያያ ምክንያት በአደጋም በተፈጥሮ ለሚከሰት የመስማት ችግር ላጋጠማቸው

ተጨማሪ የማዳመጫ መሳሪያ ይዘንላቹ ቀርበናል
ይዘዙ ከፃን እስከ አዋቂ መጠቀም ይችላሉ ክፍለ ሀገር አንልካለን አዲስ አበባ በነፃ እናደርሳለን
26.2K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 14:18:41
Tedsport ቴድ-ስፖርት Tedsport

መልካም ዜና! ቦርጭን ባጭር ጊዜ!

SWEAT MAKER
(ውፍረት እና ቦርጭን መቀነስ ፈልገዋል?)

በእንቅስቃሴ ወቅት የሰውነት ሙቀት በመጨመር ውፍረትን ባጭር ጊዜ ይቀንሳል
በትንሽ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ካሎሪ ያቃጥላል
ሆዳችን ላይ ያለን ስብ (Fat) በማቅለጥ ያማረ የሆድ ቅርፅ ያላብሰናል

ያሉበት በነፃ እናደርሳለን
(1200ብር 0961276575 @theo41)

አድራሻ
ቁ-1: ቦሌ ት/ቤት ፊት ለፊት አለምነሽ ፕላዛ ምድር ላይ ሱ.ቁ - 014
ቁ-2:ቦሌ(አትላስ) ግሬስ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ ላይ

ሌላ እቃ https://t.me/tedtechofficial
24.9K views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 14:18:13
ለ 3 ቀን ብቻ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ ከ @habmartofficial

አዳዲስ ዘመናዊ ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ ከ HABMART :: ከሙሉ አክሰሰሪ እና ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር

REDMI 9A ( 64/4gb ) … 10,800br

A51 5g (128/6gb )….. 17,000br
A71 5g (128/8gb )….. 19,500br
A90 5g (128/6gb )…. 16,000br

Iphone X 256gb … 25,500br
Iphone 11 128gb …. 37,000br

Note 10+ 5g ( 256gb/12gb )… 29,000br

Redmi note 7 pro (128/6gb )… 14,500br
Redmi note 9 ( 128/4gb )…. 16,000br
Redmi note 10 pro (128/6gb 108mp camera ) … 18,800br
Redmi note 10 ( 128/6gb )…. 16,900br

ሌሎችም አሉን ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን 0913849228 @habworld
Join our channel for more products @habmartofficial

ቦሌ መድሃኒአለም Selam city mall, 3rd floor
ልደታ AIA የገበያ ማዕከል , ground floor
25.9K views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 13:34:27
በ12 አገራት ወደ 80 የሚጠጉ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ (ሞንኪፖክስ) መያዛቸው መረጋገጡን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

የአገራቱን ስም ሳይገልጽ ሌሎች 50 ተጠርጣሪዎችም በምርመራ ላይ መሆናቸውንም የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል።መጀመሪያ በአውሮፓ መታየቱን ተከትሎ ቀደም ሲል በጣሊያን፣ በስዊድን፣ በስፔን፣ በፖርቱጋል፣ በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በዩናይትድ ኪንግደም በሽታው መኖሩ ተረጋግጧል።
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በብዛት በመካከለኛው እና በምዕራብ አፍሪካ አካባቢዎች በብዛት የሚከሰት ነው።

የእንግሊዝ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት እንደገለጸው፣ ይህ ያልተለመደ የቫይረስ ኢንፌክሽን አብዛኛውን ጊዜ ቀላል ሲሆን ብዙዎች ላይም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሚድን ነው።ቫይረሱ በሰዎች መካከል በቀላሉ የማይሰራጭ ሲሆን በሰፊው ሕዝብ ጤና ላይ የሚያስከትለው ስጋት በጣም ዝቅተኛ ነው ተብሏል።

ለዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የተለየ ክትባት የለም። ከመደበኛው ፈንጣጣ ጋር ተመሳሳይ በመሆናቸው የፈንጣጣ ክትባት 85 በመቶ የመከላከል አቅም ይሰጣል።የዓለም ጤና ድርጅት አርብ ዕለት በሰጠው መግለጫ "በቅርብ ጊዜ በ11 አገሮች የተመዘገበው ወረርሽኞች ተላላፊ ባልሆኑ አገሮች ውስጥ መከሰቱ ያተለመደ ነው" ብሏል።

"ተጎጂዎችን ለማግኘት፣ ለመደገፍና የበሽታ ክትትልን ለማስፋፋት ከተጎዱት አገራት እና ከሌሎች ጋር እየሠራሁ ነው" ብሏል።በተጨማሪም ድርጅቱ በበሽታው ምክንያት ማግለል እንዳይኖር አስጠንቅቋል።

Via BBC
29.3K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 12:01:09 “የመዲናዋ ህንፃዎች ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው” በሚል የሚናፈሰው መረጃ ሀሰት መሆኑ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ህንፃዎች ሁሉ ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው በሚል ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ አስታወቁ።

የቢሮ ኃላፊው አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የህንፃ ስታንዳርድና የውጭ ማስታወቂያ ስታንዳርድ እየተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

ሆኖም ግን ይህን መነሻ አድርጎ በማህበራዊ ትስስር ገጾች አዲስ አበባ ግራጫ ቀለም ልትቀባ ነው በሚል በስፋት ሲዘዋወር የታየው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

እስካሁን ድረስ የከተማዋ ህንጻዎች ቀለም ምን አይነት ይሁን የሚለው ጉዳይ ለውይይት ቀረበ እንጂ የከተማ አስተዳደሩ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ውሳኔ እንዳላሳለፈ አመልክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይም ከዚህ ቀደም ‹‹ከተማችን ቡራቡሬ ሆና ባለቤት አልባ መስላለች›› ማለታቸውን ያስታወሱት የቢሮ ኃላፊው÷ ይህን ችግር ማንኛውም የመዲናዋ ነዋሪም ሊታዘብ ይችላል ፤የከተማ አስተዳደሩም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቷል ብለዋል።

ችግሩን ለመፍታት የውጭ ማስታወቂያውና የከተ ማዋ ቀለም ሁኔታ የሚመራበት ስታንዳርድ ዝግጅት ተደረገ እንጂ ውሳኔ ላይ አለመድረሱን ጠቁመዋል።

በቅርቡ በጉዳዩ ላይ ከባለሀብቶች ጋር ውይይት ተደርጎ እንደነበር ያስታወሱት ኃላፊው÷ ይህን መነሻ አድርገው አንዳንድ ግለሰቦች ለግራጫ ቀለም የመሰላ ቸውን ትርጓሜ ሲሰጡ ተመልክተናል፤ጉዳዩ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እንደሚዘዋወረው ተግባር ላይ የዋለ ሳይሆን ገና ለምክክር የቀረበ መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል።

ከተማዋ ላይ አንድ አይነት ቀለም ብቻ ለቀለም ቅብ ሥራ ያስፈልጋል የሚል እሳቤ መያዝ እንደሌለበት የተናገሩት ኃላፊ÷ ለአስፈላጊው ህንጻና አካባቢ የሚመጥን ዝብርቅርቅ ያልሆነና ለዓይን የሚማርኩ ቀለማትን የያዘ ስታንዳርድ እንደሚኖረን ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህ ረገድ በተከታታይ በምናደርጋቸው ውይይቶችና የሕዝብ ተሳትፎ መድረኮች ላይ የሚገኙ ግብዓቶችን ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረግ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪ ማወቅ አለበት ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

የከተማዋ ቀለም ስታንዳርዱን የጠበቀ መሆን አለበት የሚለው ሀሳብ ሁላችንንም ሊያስማማ የሚችል ጉዳይ ነው ያሉት ዮናስ ዘውዴ÷የከተማው ነዋሪ ያልመከረበትና ስምምነት ላይ ያልደረሰበት ምንም ነገር ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ጠቁመዋል።
31.6K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ