Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 175.28K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 389

2022-05-19 12:55:26
29.3K views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 12:55:18 በህወሓት ቀንበር ስር ያለው የትግራይ ህዝብ በከፋ ባርነት ውስጥ እንደሚገኝ በቅርቡ አምልጠው የመጡት የቀድሞ የስራ ሀላፊ ተናገሩ

#Ethiopia : አሸባሪው ህወሓት የትግራይ ህዝብን በማፈን ክልሉ በከፋ ባርነት ውስጥ እንዲኖር አድርጓል ሲሉ በቅርቡ ከትግራይ ክልል አምልጠው ወደ አማራ ክልል የገቡት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አባል እና የቀድሞ የሰሜን ምዕራብ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር የማነ ሃይለ ገለጹ፡፡

ኢንጂነር የማነ የፌደራል መንግስት ባለፈው ሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ለትግራይ ህዝብ የጥሞና ጊዜ በመስጠት ከመቀሌ ለቆ መውጣቱን ተከትሎ ክልሉን የተቆጣጠረው አሸባሪው ህወሓት የጊዜያዊ አስተዳደር በነበሩ አባላት ላይ በርካታ ግፎች መፈጸሙን አስታውሰዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት የትግራይ ህዝብ ፈርቶት እንዲኖር፣ ሞራል እንዲያጣ እና የክልሉ ወጣቶች ባላቸው እውቀት ህዝብን እንዳያገለግሉ ከማሰብ የሚመነጭ የማፈን እና ሌሎች ዘግናኝ ግፎችን እየፈጸመ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላት በነበሩት አመራሮች እና ግለሰቦች ላይ የተጠና ግድያ መፈጸማቸውን ነው የገለጹት፡፡

ለዚህ ዕኩይ ተግባሩም ሲቪል መስለው የሚንቀሳቀሱ ገዳይ ቡድኖችን ማሰማራቱን ጠቁመው፥ እሳቸውም ከዚህ ቡድኑ ግድያ ማምለጣቸውን ተናግረዋል፡፡

የትግራይ ህዝብ ከተቀረው ወንድም የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲነጠል መደረጉን የገለጹት ኢንጂነር የማነ፥ አሸባሪው ህወሓት “አራት ኪሎ እገባለሁ” በሚል አይኑን ጨፍኖ በአማራ እና አፋር ክልሎች በለኮሰው ጦርነት የትግራይ ከተሞች በጦርነቱ ምክንያት አካላቸው የጎደሉ ወጣቶች መኖሪያ ማዕከል ሆነዋል ብለዋል፡፡

በዚህ ሳቢያም አዲግራት፣ ሽረ እና አክሱም ከተሞች በቁስለኛ እና አካላ ጉዳተኛ ወጣቶች የተሞሉ ከተሞች መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በጦርነቱ ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ወጣቶችም መቀሌ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ሆስፒታሎች እንደሚገኙ ነው ያብራሩት፡፡

በጦርነቱ ወጣቶች ላይ የደረሰው የአካል ጉዳት እጅግ የሚዘገንን መሆኑን በመግለጽ፥ የተጎጂ ቤተሰቦች ከፍተኛ ስቃይ እና ሀዘን ውስጥ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

ስለሆነም በአሸባሪ ህወሓት አገዛዝ የተማረረው ህዝብ ህይወቱን ለማዳን ሲል ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወደ አጎራባች ክልሎች እያመለጠ እንደሚገኝ ነው ኢንጂነር የማነ የተናገሩት፡፡

ይሁን እንጂ ከክልሉ ወጥተው ወደ አጎራባች ክልሎች የሚፈናቀሉ ዜጎችን የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች መንገድ ላይ በማገት ችግር እየፈጠሩባቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በዚህም የተፈናቃዮችን ንብረት እና ገንዘብ ከመዝረፍ ባለፈ ሴቶችን በመድፈር፣ ገንዘብ ከሌላቸውም ወደ መጡበት መልሰው በማሰር እንግልት እያደረሱባቸው መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በአንጻሩ ከአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች እገታ አልፈው ወደ አማራ ክልል ለመግባት እድሉን ያገኙ ተፈናቃዮች በክልሉ በሚገኙ የጸጥታ አካላት መልካም አቀባበል እየተደረገላቸው መሆኑን አውስተዋል ።

አሁን ላይም በአሸባሪው ህወሓት ቡድን ቁጥጥር ስር የሚገኘው የትግራይ ክልል ህዝብ በከፍተኛ ባርነት ውስጥ ይገኛል ሲሉ ነው ኢንጂነር የማነ ያስገነዘቡት፡፡
28.2K views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 12:48:39 ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ማድረግ እንድትጀምር የአውሮፓ ህብረት አሳሰበ

ተወካዩ የኢሰመኮ እና የተመድን የጋራ የምርመራ ሪፖርት የአውሮፓ ህብረት እንደሚቀበለው ተናግረዋል

የአውሮፓ ህብረት ልዩ የሰብዓዊ መብት ተወካይ ኢሞን ጊልሞር በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ጉብኝት አድርገዋል

ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ማድረግ እንድትጀምር የአውሮፓ ህብረት አሳሰበ፡፡

በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ጉብኝት አድርገው ወደ ብራስልስ የተመለሱት የህብረቱ ልዩ የሰብዓዊ መብት ልዩ ተወካይ ኢሞን ጊልሞር ጉብኝታቸውን የተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ኢሞን ጊልሞር የህብረቱ የኮሎምቢያ ልዩ የሰላም ተወካይም ነበሩ፡፡

በመግለጫው በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ዳይሬክተር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) እና ሌሎች የፌደራል ተቋማት መሪዎች ጋር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

የተመድ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በጋራ ሆነው ያጠኑት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምርመራ ጉዳይ፣ የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና የሰብዓዊ መብት ድጋፎች፤ በሶስት ቀናት የአዲስ አበባ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር የመከሩባቸው ዋነኛ አጀንዳዎች ናቸው እንደ ጊልሞር ገለጻ፡፡

ተወካዩ ኢሰመኮ እና የተመድ ሰብዓዊ መብት ባሳለፍነው ዓመት ይፋ ያደረጉት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የጋራ ምርመራ ሪፖርትን የአውሮፓ ህብረት እንደሚቀበለው ተናግረዋል፡፡

ይሁንና የጋራ ምርመራ ሪፖርቱ ግኝቶች ወደ ተግባር አልተቀየሩም፣ አጥፊዎችም ወደ ተጠያቂነት አልመጡም የሚሉት ልዩ ተወካዩ በዚህ ምርመራ መሰረት ዜጎችን በግፍ የገደሉ፣ አስገድደው የደፈሩ፣ የህግ ስልጣን ካለው አካል ውጪ ሰዎችን የሰወሩ እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የፈጸሙ ሁሉ ሊጠየቁ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በግጭቶች እና በድርቅ ምክንያት 13 ሚሊዮን ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአውሮፓ ህብረት መረጃ አለው ያሉት ጊልሞር ህብረቱ በተለይም በአማራ፣ በትግራይ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በሶማሊያ ክልሎች የሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ወደ ትግራይ ክልል ግጭቶችን በማቆም ለተጎጂዎች የሰብዓዊ መብት ድጋፍ ያለምንም ገደብ እንዲደርስ እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉም አክለዋል ልዩ ተወካዩ፡፡

ኢሰመኮ ባሳለፍነው ሳምንት በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል ያለው መካረር እየጨመረ መምጣቱን ገልጾ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይነሳ የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች ተጽዕኖ እንዲያደርጉ አሳስቦ ነበር፡፡

ጊልሞር በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይነሳ ህብረቱ ምን ሊያበረክት ይችላል? በሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄም "በጦርነት የሚፈታ ችግር የለም፣ ተጨማሪ ዜጎች ለሞት እና ጉስቁልና ሊዳረጉ አይገባም ሁሉም አካላት ችግሮቻቸውን በውይይት ሊፈቱ ይገባል" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል በኮሎምቢያ ከፋርክ አማጽያን ጋር የተደረሰውን ስምምነት እንደማሳያ በማንሳት፡፡

በሂደት ላይ ያለው ሃገራዊ የምክክር መድረክ 27ቱም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በበጎ እንደሚያዩት የተናገሩት ልዩ ተወካዩ በዚህ መድረክ ላይ ሴቶች እና ወጣቶችን ማሳተፍ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጊልሞር በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከህወሓት ባለስልጣናት ወይ ተወካዮቻቸው ጋር ተገናኝተው እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ የፌዴራል መንግስቱን እንጂ የህወሓት ባለስልጣናትን ሊያገኙ እንዳልመጡ በመጠቆም አላገኘሁም ሲሉ መልሰዋል፡፡
26.4K views09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 12:45:07
የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት 282 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት አስር ወራት 360 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 282 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተነገረ፡፡

ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥም 168 ነጥብ 7 ቢሊየን ብሩ ከአገር ውስጥ ገቢ ታክስ የተገኘ ሲሆን፥ 113 ነጥብ 8 ቢሊየን ብሩ ደግሞ ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ የተገኘ ገቢ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ጠቁመዋል፡፡

በዚህም የእቅዱን 93 ነጥብ 1 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው አቶ ላቀ በሪፖርታቸው ያመላከቱት፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት እያካሄደ በሚገኘው 8ኛ መደበኛ ጉባዔ የገቢዎች ሚኒስቴርን እና የተጠሪ ተቋማቱን የ2014 በጀት ዓመት የ10 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እያዳመጠ ነው፡፡
25.9K views09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 12:44:44
የጆሮ የመስማት አቅም ማነስ ድምፅን ከሩቅ ለመስማት እንዳነቸገር 0911284905 ይደውሉል
HEARING AID
በተመጣጣኝ ዋጋ 6800birr ከ 2 አመት ዋስትናጋ
ይደውሉልን ያሉበት ድረስ እናደርሳለን

-በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ላለ የሚሆን
-በዛላይ ለአደራረግ እና ቢታይ ቀለል ያለ
-ለሁለቱም ጆሮ ለሚፈልጎ ማድረግ የሚችሉት
-ቻርጅ ተደርጎ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ
-እራሱላይ ፓወር ባንክ ያለው

በተለያያ ምክንያት በአደጋም በተፈጥሮ ለሚከሰት የመስማት ችግር ላጋጠማቸው

ተጨማሪ የማዳመጫ መሳሪያ ይዘንላቹ ቀርበናል
ይዘዙ ከፃን እስከ አዋቂ መጠቀም ይችላሉ ክፍለ ሀገር አንልካለን አዲስ አበባ በነፃ እናደርሳለን
25.2K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 02:33:15

7.1K views23:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 02:32:54
የኢትዮጵያ አለኝታዎች

ስለእናት ኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት ስለሕዝቧ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም መከበር ያለእረፍት ሁሌም ተጓዥ ናቸው። ቆላ ይወርዳሉ። ደጋ ይወጣሉ። ጋራሸንተረሩን ያቋርጣሉ።
ሁሌም ስለኢትዮጵያ ክብር አንድያ ሕይወታቸውን መደበው ጠላትን በግንባሩ እየበረቀሱ ወደፊት በድል ይገሰግሳሉ

ኢትዮጵያ በእናንተ የጦር ሜዳ ጀግኖች ነፃነቷን ጠብቃ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች Good Night #Ethiopiaዬ
7.1K views23:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 01:49:29
7.5K views22:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 01:49:20 ኢትዮጵያ እና ቱርክ ወታደራዊ ትብብሮችን ለማድረግ የሚያስችላቸውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም በቱርክ አንካራ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

ከስምምነቱ መካከል በጥቂቱ ፦

(የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት)

ዓላማ፦ በ2ቱ አገሮች መካከል በመከላከያ ዘርፍ የሚደረገው ግንኙነት የሚመራበትን ግልጽ ማዕቀፍ ለመፍጠር ነው።

የስምምነቱ ይዘት ፦ በሁለቱ ሀገራት በትምህርት እና ስልጠና በተናጠልና በጋራ በሚዘጋጁ ወታደራዊ ልምምዶች ስለመካፈል፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪ፣ የመረጃ ልውውጥ፣ የሎጅስቲክ፣ የጤና አገልግሎት፣ የመረጃ ስርአት እና የሳይበር ጥቃትን መከላከልና በሌሎች ተያያዥ መስኮች ፣ ከመደበኛ ጦርነት ውጭ ባሉ የሰላም ማስከበር ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን ያካተተ ነው።

በኢትዮጵያ ላይ የሚጥለው ግዴታ ፦ ሚስጥራዊ መረጃዎች፣ ሰነዶች እና ማቴሪያሎች ፣ አእምሮአዊ ንብረቶችን አስፈላጊውን ጥበቃ የማድረግ ኢትዮጵያ ለትምህርት እና ስልጠና ወደ ቱርክ ለምትልካቸው የመከላከያ አባላት እና ተማሪዎች በተቀባይ ሀገር የማይሸፈኑትን የህክምና ወጪዎችን ፣ ሌሎችንም የትምህርት እና ስልጠና ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ ይጥላል።

ከዚህ ስምምነት ኢትዮጵያ የምታገኘው ጥቅም ፦ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ፣ የሎጅስቲክ አቅርቦቶችን እና ድጋፎችን ለማግኘት የሰራዊት ትጥቆችን እንዲሁም በሰው ኃይል እና አስተዳደር ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ፣ የትምህርትና ስልጠና እድሎችን ለማግኘት ያስችላል።

(የወታደራዊ ፋይናንስ ትብብር ስምምነት)

ዓላማው ፦ በሁለቱ ሀገራት መካከል በመከላከያ ዘርፍ የሚደረገው ግንኙነት የሚመራበት ግልፅ የህግ ማዕቀፍ በመፍጠር የቱርክ መንግስት 100 ሚሊዮን የቱርክ ሊሬ ተመጣጣኝ የሆነ የአሜሪካ ዶላር ለኢትዮጵያ መንግስት ፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ለመከላከያ ዓላማ የሚውል 100% በቱርክ ሀገር የተመረቱ የመከላከያ ቁሳቁሶችን እና አገልግሎቶችን መግዛት የሚችልበትን መርዕ ለመወሰን ነው።

የስምምነቱ ይዘት ፦ የቱርክ መንግስት 100 ሊሬ ተመጣጣኝ የአሜሪካ ዶላር ለኢትዮጵያ መንግስት ስለሚሰጥበት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት በዋናነት በቱርክ ከሚገኙ ኩባንያዎች 100% በቱርክ የተመረቱ የመከላከያ ቁሳቁሶችንና አገልግሎቶችን መግዛት የሚችልበትን መርህ ይደነግጋል።

በኢትዮጵያ ላይ የሚጥለው ግዴታ ፦ በሁለቱ ሀገራት የመረጃ ልውውጥ የተገኙ እና ሚስጥራዊ ተብለው የተለዩ መረጃዎችን ከሌላኛው ወገን የፅሁፍ ፍቃድ ሳይገኝ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ያለ መግለፅ እና ሚስጥራዊ መረጃዎችን መጠበቅ እንዲሁም ከቱርክ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የተላለፈ ሀብት ፣ እቃ ወይም አገልግሎት ያለ ቱርክ መንግስት የፅሁፍ ፍቃድ ለሌላ ሀገር ወይም ሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ ወይም ጥቅም ላይ እንዳይውል የማድረግ ግዴታን ይጥላል።

ከስምምነቱ ኢትዮጵያ የምታገኘው ጥቅም ፦ ኢትዮጵያ ከቱርክ መንግስት የምታገኘው 100 ሚሊዮን የቱርክ ሊሬ ተመጣጣኝ የአሜሪካ ዶላር ወታደራዊ ቁሳቁስ እና አገልግሎት ከቱርክ ድርጅቶች በመግዛት ለአስፈላጊ አገልግሎት ማዋል እንድትችል ያደርጋታል።
7.6K views22:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 01:43:08
አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምስጋና አቀረቡ!!

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምስጋና አቀረቡ።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር አብሮ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

"ክቡርነትዎ ከእርስዎ ጋር በመሆን የሁለቱን አገራት ዲፕሎማሲያዊና የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎችን እሰራለሁ" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በዚሁ መልዕክታቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፕሬዝዳንቱ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ማስተላለፋቸውም ይታወሳል።
7.6K views22:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ