Get Mystery Box with random crypto!

የቀድሞ የዩክሬን አርቲስት/ኮሜዲያን ያሁኑ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ በተለያዩ ሃገራት ያለው የ | Natnael Mekonnen

የቀድሞ የዩክሬን አርቲስት/ኮሜዲያን ያሁኑ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ በተለያዩ ሃገራት ያለው የሩሲያ ሃብት ተወርሶ ዩክሬንን ለመገንባት እንዲውል ጠየቁ ሃብቱ ለዩክሬናውያን ካሳ ነው ያሉት ዜሌንስኪ በሩሲያ የወደሙ መሰረተ ልማቶች ይገነቡበታል ብለዋል

ዜሌንስኪ ወዳጅ ሃገራት ሃሳባቸውን ተቀብለው እንዲፈርሙ ጠይቀዋል የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በተለያዩ ሃገራት ያለው የሩሲያ ሃብት ተወርሶ ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት እንዲውል ጠየቁ፡፡ ዜሌንስኪ የዩክሬን ወዳጅ ሃገራት ሃሳቡን ተቀብለው እንዲፈርሙ ጠይቀዋል፡፡

ሩሰያ ዩክሬንን በቻለችው ሁሉ እያወደመች ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ለዚህ መክፈል አለባት ብለዋል፡፡ በመሆኑም ወዳጆቻችን ተፈራርመን በሩሲያ ድርጊት የተጎዱ ዩክሬናውያን ሁሉ የሚካሱበትን መንገድ ማመቻቸት እንፈልጋለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ፊርማው በወዳጅ ሃገራቱ የሚገኝ የሩሲያን ሃብት ለመውረስ የሚያስችል ነው፡፡ ሃብቱ ወደሚቋቋመው ልዩ የካሳ ፈንድ የሚገባ ይሆናል፡፡

"ሩሲያም ወደ እኛ ስትተኩስ የነበረው እያንዳንዱ ሚሳዔል እና ቦምብ እንዲሰማት ማድረጉ ፍትሐዊ ነው" ሲሉም ነው ዜሌንስኪ የተናገሩት፡፡ ካናዳ ባሳለፍነው ሳምንት በእግድ የተያዙ ንብረቶች ተመልሰው ተጎጂዎችን ለመካስ በሚያስችል መልኩ ህጓን እንደምታሻሽል ማስታወቋ ይታወሳል፡፡