Get Mystery Box with random crypto!

ሩሲያ ፊንላንድና ስዊድን ኔቶን ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተከትሎ 12 አዳዲስ እዞችን እንደምታቋቁም | Natnael Mekonnen

ሩሲያ ፊንላንድና ስዊድን ኔቶን ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተከትሎ 12 አዳዲስ እዞችን እንደምታቋቁም አስታወቀች

ሩሲያ፤ ፊንላንድ እና ስዊድን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተከትሎ የአፀፋ እርምጃ መውሰድ መጀመሯን አስታወቀች።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጊ ሾይጉ በሰጡት አስተያየት፤ ፊንላንድ እና ስዊድን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) ለመቀላቀል መወሰናቸው በሩሲያ ድንበር አካባቢ ወታደራዊ ስጋቶች እንዲጨምሩ ያደርጋል ብለዋል።

ይህንን ተከትሎም ሩሲያ አስፈላጊ የሆኑ የአፀፋ እርምጃዎችን መውሰድ እንደጀመረች መግለጻቸውን ኢንትራፋክስ የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል።