Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 173.42K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 394

2022-05-20 13:42:25 ከሕግ አግባብ ውጪ በእስር ላይ የሚገኙ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባላት በአፋጣኝ ከእስር ሊለቀቁ ይገባል-ኢሰማኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጉዳዩ ላይ ዛሬ ግንቦት 11 ቀን ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በመግለጫው ሌሎች የቅድመ-ክስ ታሳሪዎችም ተዓማኒ ክስ ካልቀረበባቸው በአፋጣኝ ከእስር ሊለቀቁ ይገባል ያለው ኮሚሽኑ የተራዘመ ቅድመ-ክስ እስር (prolonged pre-trial detention) ሰዎች በፍትሕ አስተዳደር ላይ ያላቸውን እምነት ያጠፋል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በተለያዩ ፖሊስ መምሪያዎች በእስር ላይ ያሉ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባሎች የእስር ሁኔታን በተመለከተ ለረጅም ጊዜ ሲያደርገው ከነበረው ክትትል በተጨማሪ ከፓርቲው እና ከእስረኞች ቤተሰቦች በቀረቡ አቤቱታዎች መነሻነት ከመጋቢት 1 እስከ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በቡራዩ ከተማ፣ በገላን ከተማ እና በሰበታ ፖሊስ መምሪያዎች በአካል በመገኘት ክትትል በማድረግ እስረኞችን፣ የፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎችን፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንን እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተወካዮችን በማነጋገር ምርመራ አድርጓል።

በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜያት እስረኞቹን በሚመለከት በፍርድ ቤት እና በዐቃቤ ሕግ የተሰጡ ውሳኔዎችን እና ትዕዛዞችን እንዲሁም የሕክምና ሰነዶችን ተመልክቷል፡፡

በቡራዩ ፖሊስ መምሪያ በእስር ላይ የነበሩ አቶ ሚካኤል ጎበና፣ አቶ ኬኔሳ አያና፣ ዶ/ር ገዳ ወልጅራ፣ አቶ ዳዊት አብደታ፣ አቶ ለሚ ቤኛ፣ አቶ ገዳ ገቢሳ የተባሉ የፓርቲው አመራር መሆናቸውን የገለጹ ስድስት እስረኞችን ኮሚሽኑ አነጋግሯል። በተጨማሪም ኮሎኔል ገመቹ አያና በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ማዕከል፣ እንዲሁም አቶ አብዲ ረጋሳ ገላን ከተማ በሚገኘው የኦሮሚያ ክልል ልዩ ፖሊስ ካምፕ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙ መሆኑን ከቤተሰብ እና ከጠበቆቻቸው መረዳት ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ አቶ በቴ ኡርጌሳ በእስር ላይ እያሉ ባጋጠማቸው ሕመም ምክንያት በፖሊስ ዋስትና ተፈቅዶላቸው በአንድ የሕክምና ተቋም ሕክምና ላይ የነበሩ መሆኑን ኮሚሽኑ ተመልክቷል፡፡

በዚህ ምርመራ መሰረት፣ ፍርድ ቤት በዋስትና እንዲለቀቁ የፈቀደላቸው፣ የክስ መዝገቦቻቸው ተዘግተው በፍርድ ቤት ውሳኔ በነፃ የተሰናበቱ፣ ምንም አይነት ክስ ያልተመሰረተባቸው እና ዐቃቤ ሕግ ክስ የማይመሰርትባቸው መሆኑን በማረጋገጥ የምርመራ መዝገባቸው የተዘጋ፤ሆኖም ከወራት እስከ 2 ዓመት ለሚሆን ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች እየተዘዋወሩ ከሕግ አግባብ ውጪ በእስር ላይ የሚገኙና የተወሰኑትም በእስሩ ሂደት በተፈጸመ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እና ድብደባ ለተለያዩ የአካል ጉዳቶችና የጤና እክል የተጋለጡ እስረኞች መሆናቸውን ኢሰመኮ ተረድቷል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “የኦነግ ፓርቲ አመራሮች ለተራዘመ ጊዜ ከሕግ አግባብ ውጭ ታስረው የሚገኙ በመሆኑ በአፋጣኝ ከእስር ሊለቀቁ እና ለደረሰባችው ጉዳት ሊካሱ የሚገባ ሲሆን፤ በተጨማሪም የፍርድ ቤትና የዐቃቤ ሕግ ውሳኔዎች በተደጋጋሚ እየተጣሰ እስረኞቹ ከሕግ ውጪ ለተራዘመ እስር መዳረጋቸው ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ስለሆነ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አፋጣኝ ማጣራት አካሂዶ ተገቢውን እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል” ብለዋል፡፡

የኢሰመኮ የሲቪል፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጂብሪል በበኩላቸው “በተለይም ታሳሪዎቹ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በመሆናቸው በሕዝባዊ አገልግሎት ስራቸው ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዳይጋለጡ ጥበቃ ሊደረግ ሲገባ፤ በተግባር የተገላቢጦሽ መሆኑ አሳዛኝ መሆኑን አስታውሰው ጉዳዩ አፋጣኝ እልባት ያስፈልገዋል” ሲሉ አሳስበዋል።
ምስል ከኢሰመኮ
36.4K views10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 13:40:08 በዓለም ላይ ካሉ “በጣም አደገኛ” የጦር መርከቦች አንዱ የሆነው የቻይናው “ለሃሳ” መርከብ

መርከቡ የባህር ላይ ተልእኮዎችን የመፈጸም ሙከራውን በሙሉ አጠናቆ ለስምሪት ዝግጁ ሆኗል። መርከቡ ከምድር ወደ አየር ሚሳዔሎችን ጨምሮ የፀረ-መርከብና ፀረ-ሰርጓጅ ሚሳኤሎች ማስወንጨፍ ይችላል።
https://am.al-ain.com/article/china-s-second-type-055-large-destroyer-passes-test-for-sea-missions
31.2K views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 13:39:51
Telegram - t.me/qnashcom
Moving Helpers
Home moving furniture caster wheel heavy objects transporter small mover labor-saving moving wheels bed tool
Max 150 KG

ዋጋ፦ 1000 ብር

ውስን ፍሬ ነው የቀረው
Limited Stock

Telegram - t.me/qnashcom
Website - www.qnash.com
ጥራት ዋስትና ቅናሽ
አድራሻ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3 ተኛ ፎቅ ቁጥር 329 ከሊፍት እንደወረዱ በግራ በኩል የፎቁ መጨረሻ ዞር እንዳሉ
ስልክ:
0946966440
0905464599
+251118639952
29.7K views10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 13:38:57
በባለሙያ እና በመሳሪያ የተደራጀ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ
የብሬስ ህክምና ለማስጀመር ነፃ የማማከር አገልግሎት እና የአከፋፈል መንገድ
ለተማሪዎች ልዮ ቅናሽ( መታወቂያ መያዝ እንዳይረሱ )
ሁሉንም ህክምና በተመጣጣኝ ዋጋ እንሰጣለን
ቁጥር 1- 4ኪሎ ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ ላይ
ቁጥር 2- ኮተቤ 02 ጆሲ ሙል ላይ
ለበለጠ መረጃ  በ0911-42-42-42
0970-51-71-51 ይደውሉልን
በቲሊግራም - https://t.me/shalomdentalclinic
Face book- @shalomdentalclinic
30.0K views10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 11:51:36
#Ethiopia : የኢትዮ ቴሌኮም ከዘመን ባንክ ከዘምዘም ባንክ ዌብ ስፕሪክስ እና ከሬይስ ማይክሮ ፋይናንስ እና ከሂጅራ ባንክ ጋር የመረጃ ማዐከል በጋራ ለመጠቀም የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ::

ፕራይም ሚዲያ (አዲስ አበባ)በደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዞን ስምምነቱን ያደረገው ኢትዮ ቴሌኮም እየገነባቸው ያሉት የመረጃ ማዕከል ዘመናዊ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂ መሆናቸውን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሂወት ታምሩ ገልጸዋል።

አዳዲስ ምርቶችን ወደ ገበያ ለማምጣት እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ያለው ሚና ከፍ ያለ እንደሆነም ተናግረዋል::

የመረጃ ማዕከሉ ለአጋር ድርጅቶች ማጋራት የሀብት መባከን ይቀርፋል ያሉት ስራ አስፈጻሚዋ ቀልጣፋ እና አዋጭ መሆኑንም እንዲሁም አስተማማኝ እና ወጥ የሆነ አገልግሎትን ለመስጠት እንደሚያስችላቸውም ገልፀዋል::

ኢትዮ ቴሌኮም ያስገነባቸው ዳታ ማዕከሎች አርቴፊሻል ኢንተለጀንት አገልግሎት እና አስተማማኝ ማኔጅመንት ስርዓት የተዘረጋላቸው ናቸው::


ውስን ሀብቶችን በመጠቀም ዘመናዊ የቴሌኮም አገልግሎትን እየፈጠረ መሆኑን የሚገልፀው ኢትዮ ቴሌኮም የስራ አጥ ቁጥርን በመቀነስ እና ለዜጎች ምቹ የቴሌኮም አገልግሎትን በመስጠት ረገድ ድርሻው የጎላ እንደሆነም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለው ገልፀዋል::

የኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ የውሃ ቢል ክፍያ በቴሌ ብር እና በደራሽ አማካኝነት ለመክፈል የሚያስችለውን ስምምነት ከሰባት ከተሞች ጋር ማድረጉ ይታወቃል::
33.8K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 11:12:58 ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ በጥቂት ግዜ የሚጠናቀቁ ሰዉ ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን አስጀመሩ።

#Ethiopia : ሠው ተኮር የሆኑ አቅመ ደካሞችን ተጠቃሚ የሚያደረጉ 4 ባለ 9 ወለል ህንጻዎች የቤት ግንባታ፡ የምገባ ማዕከል ግንባታ ፥ የከተማ ግብርና ፥ 200 ቤቶችን በክረምት በጐ ፈቃድ ማደስ ፥ የዳቦ አቅርቦትን ለማሳደግ የሚየስችል ግንባታ ፥ ከተጀመሩት ፕሮጀክቶች ውስጥ ናቸው።

በፕሮጀክቱ ማስጀመር መርሃ ግብር ላይ ንግግር የደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሁላችንም : ሌት ተቀን ከሰራን ለውጥ ማምጣት እንችላለን ብለዋል።

ለለውጥ የቆመ መንግሥት ፥ ትጉህ ህብረተሰብ እና ባለሃብት ስላለን ካስተባበርነው የምንፈልገውን ለውጥ ማምጣት እንችላለን ሲሉም ገልፀዋል::

ኢትዮጵያዊነታች ከወደድን አቅመ ደካሞችን እየደገፈን ፥ መብላት የማይችሉት እንዲበሉ እያገዝን ፥ ተበብረን ለለውጥ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ለውጥ የትጋት ውጤት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፥ ሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች ተግተው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል :: የጎሮ አትክልት በማልማት፡ አካባቢን በማፅዳት ከተማችን ውብና ምቹ እንድትሆን ማድረግ ይጠበቅብናል::

ከተማችን የዲፕሎማቲክ ማዕከል ሆና ደረጃዋን የጠበቀች በውበትዋም በፅዳቱም ማራኪ መሆን ይጠበቅባታል : በዚህም በቅርቡ የጀመርናቸው የከተማችን ደረጃዋን የሚያሳድጉ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

በአጭር ጊዜ በከተማችን ሞዴል ሥራዎችን ለመሥራት ከጎናችን ለሆኑት ምስጋና አቅርበዋል ::

አቶ ጀማል አህመድ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሃላፊ ሚድሮክ ለድርጅቱ 2ኛ የሆነ ምገባ ማዕከል ግንባታና በክፍለ ከተማው ዛሬ ከተጀመሩት 4 ህንፃዎች አንዱን እንደሚገነቡ ገልፀዋል። ሚድሮክ ኩባንያ የመንግስትን ጥሪዎችን ተቀብሎ በልማቱ እየተስተፈ የሚገኝ ፧ በቀጣይም ከመንግስት ጒን ሆነን እንሰራለን ብለዋል።

አቶ ደርቤ አሰፋው የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሃለፊ እኛ ከተባበርን የከተማችን ውበት ማሳደግ እንችላለን ብለዋል። የአሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ የኮርፖሬት ሃላፊነቱን ለመመጣት በተለያዩ መስኮች እየሰራ መሆኑን ገልፀው ዛሬም አቅመደካሞችን ተጠቃሚ የሚያደርገው አንዱን ህንጻ ለመገንባት ቃል ገብተዋል። አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና አዲስ እናደርጋለን!
34.6K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 11:00:45 #Ethiopia : መንግስት ስርዓትና ደንብን የማስከበር ሐላፊነት አለበት:: ማንም ሰው ከህግ በላይ ሊሆን አይገባም:: ከመንጋ አስተሳሰብ የሚመነጭ እሳቤ የትም አያደርስም!
33.4K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 08:39:18 የኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ (ዶክሌ) የቀብር ስነስርአት የሚፈጸመው በትውልድ ሀገሩ ኢትዩጵያ ስለሆነ ለዚህም ማስፈጸሚያ የሚሆን እና ቤተሰቦቹን ለመርዳት ይህ የጎፈንድሚ አካውንት ተከፍቷል። ወዳጅ ጓደኞቹና የጥበብ አፍቃሪያን ይህ ታላቅና አይተኬ ኮሜዲያን በክብር ይሸኝ ዘንድ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን!!! ወዳጆቹ

https://www.gofundme.com/f/4bry7-emergency?fbclid=IwAR2a9BNW4yAWK2cnEoJbLSMEtWcj47P9zCD5Ni2iJa4C8pp9J4ggPoVKVKA
36.5K views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 08:19:42
በደቡብ ዕዝ ኮር የተካሄደው ወታደራዊ ስልጠና የሰራዊቱን የማድረግ አቅም ማሳደጉ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላክያ ሰራዊት

በኮር ደረጃ ሲሰጥ የቆየው ወታደራዊ ስልጠና የሰራዊቱን የማድረግ አቅም ያጠናከረ ነው ሲሉ የተናገሩት የኮሩ ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል መለስ ይግዛው ናቸው።

በኮሩ ስር በሚገኙ ክ/ጦሮች የተደረገው ወታደራዊ ስልጠና ሰራዊቱ በቀጣይ የሚሰጠውን ግዳጅ በአስተማማኝና በጀግንነት ለመፈፀም የሚያስችለው መሆኑንም ገልፀዋል።

የሰራዊቱን ሞራላዊ እና ስነ ልቦናዊ ዝግጁነት በከፍተኛ ደረጃ መገንባቱን የገለፁት ጀኔራል መኮንኑ ወቅቱን እና ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበ ስልጠናዎችን በማካሄድ የሠራዊቱን የማድረግ አቅም ማሳደግ ችለናል ብለዋል።
35.1K views05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 08:14:29 የፌዴራል መንግስቱን እንጂ የህወሓት ባለስልጣናትን ለማግኘት ወደ ኢትዮጵያ እንዳልመጡ የአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ መብት ተወካይ ተናገሩ

ተወካዩ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ማድረግ እንድትጀምር አሳስበዋል፡፡
ኢሞን ጊልሞር ሶስት ቀናት የወሰደውን የአዲስ አበባ ጉብኝታቸውን የተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
https://am.al-ain.com/article/eu-urges-ethiopia-to-start-holding-accountable-human-rights-violators
31.9K views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ