Get Mystery Box with random crypto!

#Ethiopia : በኦሮሚያና በአጎራባች ክልሎች የሸኔ የሽብር ቡድን ከሌሎች የጥፋት ኃይሎች ጋር | Natnael Mekonnen

#Ethiopia : በኦሮሚያና በአጎራባች ክልሎች የሸኔ የሽብር ቡድን ከሌሎች የጥፋት ኃይሎች ጋር በመተባበር ህዝባችን ላይ እያደረሰ የነበረውን ጥቃት ለመቀልበስ መንግስት የተሳካ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች በአልሸባብ የሽብር ኃይል ላይ እየተወሰደ የሚገኘውም እርምጃ ውጤታማ በሆነ መንገድ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በአዲስ አበባና በዙሪያው ኦሮሚያ ከተሞች በቡድን ተደራጅተው በልዩ ልዩ የዝርፊያ ወንጀሎች ላይ የተሰማሩ፣ የጦር መሳሪያና የገንዘብ ዝውውር አቀባባይ በሆኑ ቡድኖችና ግለሰቦች፤ እንዲሁም በወያኔ ሰርጎ ገቦች ላይም መንግስት ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡ በሁሉም ክልሎች እየተካሄደ በሚገኘው ኦፕሬሽን በርካታ ግለሰቦችና ቡድኖች ከነ ትጥቆቻቸዉ፤ ከዘረፉት ንብረትና ቀጣይ ሊፈፅሙ ያቀዷቸዉ ጥፋቶችን ካሰፈሩባቸው ሰነዶች ጋር በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ እየተደረገ ነው። ጉዳያቸውም ተገቢውን ሂደት ጠብቆ እየተጣራ ለፍርድ እንዲቀርቡ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የዜጎች ነፃነትና ዲሞክራሲም መስፈን የሚችለዉ የትኛውም ጉልበት አለኝ የሚል አካል ከህግ በታች መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ነፃነትንና መብትን ከለላ በማድረግ የሚፈፀም የትኛውም አይነት እኩይ ተግባርን መንግስት አይታገስም፡፡ መንግስት በሆደ ሰፊነት በተደጋጋሚ ጊዜ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ከቁብ ያልቆጠሩ ኃይሎችን መግታት የሚቻለው የህግ የበላይትን በማስከበር ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ዜጋና የተለየ አመለካከት ያላቸው ወገኖችም መብትና ጥቅሞቻቸዉን ማስከበር የሚችሉት የህግ የበላይነት ሲረጋገጥና ሰላም ሲሰፍን ብቻ ነው፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት!