Get Mystery Box with random crypto!

'ከሰሞኑ በአማራ ክልል በህገወጥ የጦር መሳሪያና ገንዘብ ዝውውር፤ በቡድን ተደራጅቶ ግለሰቦች ያፈሩ | Natnael Mekonnen

"ከሰሞኑ በአማራ ክልል በህገወጥ የጦር መሳሪያና ገንዘብ ዝውውር፤ በቡድን ተደራጅቶ ግለሰቦች ያፈሩትን ሃብትና ንብረት በመዝረፍና በማውደም ላይ የተሰማሩ፤ በነፍስ ግድያ የሚጠረጠሩ፣ አንዱን ህዝብ ከሌላው ጋር በማጋጨት ክልሉ እንዳይረጋጋ በሚያደርጉ ቡድኖች ላይ መጠነ ሰፊ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡ " - መንግስት

#Ethiopia : መንግስት፣ በሁሉም ክልሎች እየተካሄደ በሚገኘው ኦፕሬሽን በርካታ ግለሰቦችና ቡድኖች ከነ ትጥቆቻቸዉ፤ ከዘረፉት ንብረትና ቀጣይ ሊፈፅሙ ያቀዷቸዉ ጥፋቶችን ካሰፈሩባቸው ሰነዶች ጋር በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ እየተደረገ ነው። ጉዳያቸውም ተገቢውን ሂደት ጠብቆ እየተጣራ ለፍርድ እንዲቀርቡ እየተደረገ ይገኛል ብሏል፡፡

መንግስት ፣ በፋኖ ስም የሚነግዱ የዝርፊያ ቡድኖች በህዝባችን ላይ ከፍተኛ ክህደት የፈፀሙ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች እና የተላላኪዎቻቸው ዓላማ ማስፈፀሚያ መሆናቸው ነው ያለ ሲሆን መላው ህዝባችን ይህንን እኩይ ሴራ በመገንዘብ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመደገፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ይጠይቃል ብሏል።

የሚዲያና የጋዜጠኝነት ካባ ደርበው ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የሚወሰደውን የማያዳግም እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል፡፡(የመንግስት ኮሙኒኬሽን)