Get Mystery Box with random crypto!

ሽልማቱን በትህትና አልቀበልም ውድድር በመኖሩ ጥሩ የሰራን በማበረታታት አጥብቄ አምናለሁ ግን | Natnael Mekonnen

ሽልማቱን በትህትና አልቀበልም

ውድድር በመኖሩ ጥሩ የሰራን በማበረታታት አጥብቄ አምናለሁ ግን ሰው ነኝና ደግሞ የራሴ እሳቤና መንገድ አለኝ::

ውድ የጉማ አዋርድ አዘጋጆች ለሁሉም ድርጅት በቅድሚያ እንዳሳወኩት ሁሉ ለተከበረ ድርጅታችሁ ምንም አይነት የእጩነትና ውድድር ክብር መድረክ አልሳተፍም ብዬ ቀደም ብዬ አሳውቄለሁ:: ለሌላ የሚገባው የስራ አጋሬ ማበርከት ሲገባው ሽልማቱ ለምን እንዲህ ማድረግ እንደተፈለገ አልገባኝም:: እኔና ህሊናዬ ግን ከእውነተኛ አክብሮት ጋር ሽልማቱን አንቀበልም::


ካለብን የፖሊሲ ገደብ የታክስ አከፍፈል ተመንና ለሙያው ያለው ምቾት የማይሰጥ ግንዛቤ እዚ ሙያ ውስጥ መስራታችን እየሰራንም መቆየታችን በራሱ ለሁሉም የሙያ አጋሮቼ ትልቅ አሸናፊነት ነው::

በውድድሩ ስማችሁ አብሮኝ የተጠቀሰ የሙያ አጋሮቼ በችሎታ ከእናንተ እኩል እንደ ደረስኩ ስለታሰብኩ ትልቅ ክብር ተሰምቶኛል:: የውድድር አዘጋጆችም ከሙያ አጋሮቼ እሚተካከል ችሎታ አላት ብላችሁ ስላሰባችሁኝም ከልቤ ደስ ብሎኛል ::

እድሉን አግንቼ እምሰራው የትኛውም ስራ የጥበብ ስራ አክባሪዎች በፈቀዱልኝ ልክ በተለየ የህይወት አጋጣሚ ለማሳለፍ መነገር ያለበትን ታሪክን ለማክተብና ስሜትን ለማጋባት እንደሆነ ብቻ ሁሌም ይታሰብልኝ::

የስራ አድናቂዎችሽ ምን ይሉሻል ዝም ብለሽ ተቀበይ ለምሉኝ ወዳጆቼ ሀሳባችሁን አከብራለሁ ከፍቅር ነውና
.
.
ግን
.
.
እኔና የእውነተኛ የስራዬ ወዳጆች እንተዋወቃለን እኔን ያውቁኛል የኔን እውነቴን በመናገሬ ብሳሳት "ቅሌት /ስህተት/ ብርቄ አይደለም" ለዛም ነው የሚወዱኝ የሚቀበሉኝ ብዬ ማስብን መርጫለሁ::

ስለዚህ በግሌ ከየትኛውም የውድድርና የእጩነት ክብር መድረክ እራሴን አግልያለሁ ወደፊትም:: ይህን ከግል አቋም ለስራዬ ካለኝ የተለየ ትርጉምና የስራዬን ወዳጆች ከማክበር እንጂ ከሌላ በፍፁም እንዳይታይብኝ አደራ እላለሁ አመሰግናለሁ::

ከአርቲስት ሳያት ደምሴ