Get Mystery Box with random crypto!

ከሞጣ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ የሞጣ ከተማ አስተዳደር የጸጥ | Natnael Mekonnen

ከሞጣ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

የሞጣ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት በከተማዋ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለማስተካከል በአሁኑ ሰዓት የጸጥታ መዋቅሩ በሙሉ አቅም እየሰራ ይገኛል፡፡ ስለሆነም መላ ህዝባችን ፦

1ኛ. ማንኛውም ህዝብ/ግለሰብ በቡድን ሆኖ በከተማዋ መንቀሳቀስ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

2ኛ. ማንኛውም ሰው በህግ የሚፈለጉ አካላትን ደብቆ ወይም አከራይቶ ቢገኝ ተጠየቂ መሆኑን አውቆ ችግር ፈጣሪዎችንና ተፈላጊዎችን አሳልፎ እንዲሰጥ እናሳስባለን፡፡

3ኛ. ለህግ ማስከበር ሲባል ከጥዋቱ 12፡00 ሰዓት በፊትና ከምሽቱ 12፡30 ሰዓት በኋላ ስምሪት ከተሰጣቸው የጸጥታ ሃይሎች ውጭ እንቅስቃሴ ገደብ የተቀመጠ መሆኑን እያሳሰብን ይህንን በሚተላለፉ አካላት ላይ የጸጥታ ሃይላችን እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል፡፡

4ኛ. ስምሪት ከተሰጠው የጸጥታ ሃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

5ኛ. የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ነገር ለማባባስ የሚሰሩና የጸረ ሰላም እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ግለሰቦችን እንዲመክሩ እየጠየቅን የከተማችን ወጣቶችና መላ ህዝቡ ከጸጥታ መዋቅሩ ጎን እንዲቆሙ ጥሪያችንን እያቀረብን ከላይ የተጠቀሱ ክልከላዎችን በመተላለፍ ለሚወሰድ እርምጃ ምክርቤቱ ኃላፊነት አይወስድም፡፡

ግንቦት 13/2014ዓ.ም
የሞጣ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት