Get Mystery Box with random crypto!

ኢንጂነሩ - ከሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች በስተጀርባ #Ethiopia : ኢንጂነሩ ኅብር ኢትዮጵያ የ | Natnael Mekonnen

ኢንጂነሩ - ከሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች በስተጀርባ

#Ethiopia : ኢንጂነሩ ኅብር ኢትዮጵያ የተባለውን ፓርቲ የግል ንብረቱ አድርጎ እንዳሻው እየዘወረው ነው፡፡ ሰሞኑን ፓርቲውን እንደ ሽፋን በመጠቀም ከኢመደበኛ አደረጃጀት ጋር በድብቅም በግልፅም የሚያደርገው ግንኙነት ኢትዮጵያ በሽብር እንድትታመስ፤ አመፅ እንዲነሳ የልብ መሻት ያለው መሆኑን ያመላክታል። የአማራን ህዝብም “እየተጠቃህ ነው፤ ተነስ፤ ተዋጋ” በሚል ሀገር ተረጋግታ ወደ ልማት እንዳትገባ ፀብ ቀስቃሽ ሀሳብን በየአጋጣሚው ማንሳቱም ከበስተጀርባው ድብቅ ተልዕኮ እንዳለው እያሳበቀበት ይገኛል፡፡

የህብር ኢትዮጵያ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ስም እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም፤ የምርጫ ቦርድንና ሌሎችን የሀገሪቱን የሕግ ማዕቀፎች በሚጻጸር መልኩ በትጥቅ ትግልና በአመጽ መንግስት መቀየር ወይም የሽግግር መንግስት መመስረት ይገባል የሚል አመለካከት ከሚያራምዱ አካላት ጋር ሲመክርና ሲያሴር መገኘቱም አነጋጋሪ እየሆነ ነው፡፡

ኢንጂነሩ የትጥቅ ትግል አደረጃጀቶች ልሳን በሆኑና በስውር ለህወሓት በሚሰሩ ሚዲያዎች ላይ መንግሥት ፋኖን እያጠቃ መሆኑን በማወጅ ህዝቡ ወደ ጦርነት እንዲገባ ገፋፍቷል፡፡ ህዝብ ለአመፅና ለእምቢተኝነት እንዲነሳ ያልሆነውን ሆነ በማለት ግፊት ሲያደርግ፤ ምንም እንኳን የስልጣን ፍላጎቱ ከቁጥጥሩ ውጪ አድርጎት ህሊናው ባይወቅሰው እንኳን ህግ እንደሚጠይቀው ማወቅ ነበረበት።

የህብር ኢትዮጵያ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ምርጫ 2013 ከመካሄዱ በፊት ማይክ በጨበጠ፤ መድረክ ባገኘበት አጋጣሚ ሁሉ ለኢትዮጵያ ችግር ብቸኛው መፍትሄ የሽግግር መንግሥት መመስረት ነው፤ ምርጫው መካሄድ የለበትም በማለት ሲቃወም ከርሞ፤ በምርጫው በመሳተፉ የሚገኘውን የገንዘብ ትርፍ ሲያሰላው ግን ስላላስቻለው ግንባር ቀድም ተፎካካሪ መስሎ ለመታየት መሞከሩ ይታወሳል፡፡ ገንዘቡ እንደ ግል አካውንቱ በሚቆጥረው የፓርቲው አካውንት ሲገባ ደግሞ ያን የዛገና የሰለቸ የሽግግር መንግሥት አጀንዳ ከኋላ ኪሱ አውጥቶ በየመገናኛ ብዙሃን በራፍ ደጅ መጥናቱን ቀጥሎ ነበር፡፡

ኢንጂነሩ ዛሬ ዛሬ ለሽግግር መንግሥት አጀንዳው ማስፈጸሚያ በኢመደበኛ አደረጃጀቶች ጀርባ ተሸሽጎ መንቀሳቀሱን የመረጠ ይመስላል፡፡ ይህ አካሄድ ጸረ ኢትዮጵያ አቋም ባላቸው አካላት ከበስተጀርባ በገንዘብ እንደማይደገፍም በምርጫ ወቅት ከተስተዋለው የአፍቅሮተ ነዋይ ጉዳይ በመነሳት “በትንሽ ያልታመን ለትልቅ አይታጭም” እያስባለ ነው፡፡