Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 174.28K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 385

2022-05-23 14:09:18 #Ethiopia : መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊሰማው የሚገባ! ይህን ፕሮግራም ለአደማመጥ እንዲመች ብዬ ቆራርጨ ላቀርበው አስቤ ነበር ግን ምኑን ከምኑ ልቁረጠው?! አንዳችም የሚቆራረጥ ነገር የለውምና 49 ደቂቃ ነች ግዜ ሰታችሁ አድምጡት!

37.3K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 14:08:56 ከድባጤ እና በቂዶ ሚሊሻዎች ጋር በመተባበር የአሸባሪው ህወሓት ተላላኪዎችን መደምሰሱን የመተከል ኮማንድ ፖስት አስታወቀ

በመተከል ዞን በድባጤ እና በቂዶ ወረዳዎች የሚገኙ የጉሙዝ የሚሊሻ አባላት ከመከላከያ ሰራዊት ጎን ተሰልፈው ለአሸባሪ ቡድኖች የሚላላኩ ሽፍታዎችን መደምሰሳቸውን የመተከል ኮማንድ ፖስት የተቀናጀ ግብረ ኃይል ተወካይ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ዋለልኝ ታደሰ ተናገሩ፡፡

ብርጋዴር ጀኔራል ዋለልኝ ታደሰ እንደተናገሩት፥ የሚሊሻ አባላቱን ከግል ፍላጎት ወደ ቡድን አንድነት አደረጃጀት በመቀየር በአጭር ጊዜ ውስጥ የአሸባሪው ህወሓት ተላላኪ ሽፍታዎች በመደምሰስ እና የጦር መሳሪያዎችን በመማረክ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን በተግባር አረጋግጠዋል።

የሚሊሻ አባላቱ ቡድን መሪ ብድኡከም በታሐኒ እንደገለጹት÷ የአሸባሪው ህወሓት ተልዕኮ አስፈፃሚዎችን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ እና ሕዝቡን ከጥፋት ቡድኖች ለመታደግ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ተቀናጅተን እንሠራለን ብለዋል፡፡

ሌሎች የሚሊሻ አባላት በበኩላቸው÷ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ሰላም ለማደፍረስ ቀን ከሌሊት የሚደክሙ የአሸባሪ ኃይሎች ላይ አስፈላጊውን የኃይል እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅተናል ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
34.7K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 14:08:07 ‘‘‹‹በሸኔ ቁጥጥር ስር የነበሩ ቦታዎች አልነበሩም ፤ ነጻ የሚወጡ ቦታዎችም የሉም››’’:- ኮሎኔል አበበ ገረሱ ኦሮሚያ አስተዳደርና ጸጥታ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

የክልሉ አስተዳደርና ጸጥታ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ለኢፕድ ሕብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እየወሰደ ባለው እርምጃ የሸኔ እንቅስቃሴ ለሀገር ስጋት በማይሆን ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል::

እንደ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ገለጻ ሸኔ በሚንቀሳቀስባቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች መንገድ በመዝጋት ና ከመኪና አውርዶ ሰውን በመግደል በተወሰነ መልኩ በሕዝቡ እንቅስቃሴ ላይ ፍርሃትና ስጋት እንዲፈጠር አድርጓል:: ሆኖም በድርጊቱ የተማረረው ሕዝብም ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ቡድኑ የሚንቀሳቀስባቸውን ቦታዎች በመከታተል እርምጃ እየወሰደበት ይገኛል::

እስከ አሁን ድረስ ሸኔ ላይ በተወሰደው እርምጃ የተገደሉና የተማረኩ መኖራቸውን ገልጸው በተገኘው ውጤት የሕዝብ እንቅስቃሴ ወደነበረበት ቦታ እየተመለሰ መሆኑን ገልጸዋል ::

እንደ ኃላፊው ገላጻ ሸኔ የታጠቁ የመንግሥት ኃይሎች በማይገኙበት ቦታ ጨለማን ተገን በማድረግ በጫካ ውስጥ እየተሽሎከለኩ ጥቃት ፈጽሞ ከመሸሽ ውጪ የመንግሥት አቅም አሸንፎ የተቆጣጠረው ቦታ የለውም :: ‹‹በሸኔ ቁጥጥር ስር የነበሩ ቦታዎች አልነበሩም ፤ ነጻ የሚወጡ ቦታዎችም የሉም›› ብለዋል። ሸኔ ፊት ለፊት ጦር ግንባር ላይ የሚደረግ ጦርነት የሚከተል ሳይሆን ሽምቅ ውጊያ ሥልት የሚከተል አጥፊ ቡድን ነው::

የሸኔ እንቅስቃሴ ለሀገር ስጋት አይሆንም ሲባል እንደተለመደው ተሸሽገው ህዝቡ ላይ ጥቃት አያደርሱም ማለት እንዳልሆነ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አመላክተዋል:: ሆኖም ይህንን የቡድኑን አጥፊ ድርጊት ለመከላከል መንግሥት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ኮሎኔል አበበ ገረሱ አብራርተዋል::
31.5K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 14:07:25
የሊንኮቹን ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+kpVVJnBHB5ZhZjI0
28.5K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 14:07:07
ናሽ የጥርስ እና የዓይን ህክምና ክሊኒክ
        Nash Dental and Optometry Clinic
 
ናሽ የጥርስ እና የዓይን ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስና የአይን ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢  
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
 
➢ የረዥም እርቀት፤ የአጭር እርቀት እና ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የቅርብ እይታ መቀነስ ምርመራ እና ህክምና
➢ ሁለት ዓይኖች ተቀናጅተው ያለመስራት ችግር ምርመራ እና ህክምና
➢ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት የእይታ መቀነስ ችግርን ምርመራና ህክምና
➢ የህፃናት የአይን ምርመራና ህክምና
➢ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የአይን መነጽሮች የሎው ቪዥን ድጋፍ መስጫ የቪዥን ቴራፒ መሳሪያዎች መለካት ማስተካከል እና ማዘዝ
 
 
በሁሉም የህክምና አይነቶች ቅናሽ አድርገናል
      አድራሻ: ቁጥር 1 ሜክሲኮ ገነት ሆቴል ፊት ለፊት ካሳ ግራንድ ሞል 4ኛ ፎቅ
                       ቁጥር 2 ሰሚት ሳፋሪ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት ገሊላ ፕላዛ
                       Tel: 0905262626, 0913858561
31.1K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 11:21:26 #Ethiopia : የአማራ ክልል መንግሥት የክልሉን ዘላቂ ሰላም የማስጠበቅ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም የአማራ ክልል ጸጥታና ሰላም ቢሮ ኃላፊው በመግለጫቸው ገልጸው ትክክለኛውን የፋኖ ስም የማይወክሉ፣ በፋኖ ስም ተደራጅተው በሕዝብ ላይ የተለያዩ ሕገ ወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ ቡድኖችን መንግሥት እንደማይታገስም አቶ ደሳለኝ ገልጸዋል። ትክክለኛ የፋኖ አባላትን በመንግሥት መዋቅር ሥር በማድረግ እንዲሠሩ እየተደረገ መሆኑንም ኃላፊው አስታውቀዋል::
35.6K views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 11:15:43
ሰሞኑን በተካሄደ የሕግ ማስከበር ዘመቻ በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮው የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። የቢሮው ኃላፊ አቶ ዳሳለኝ ጣሰው በሰጡት መግለጫ÷ መንግሥት የክልሉን ዘላቂ ሰላም የማስጠበቅ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
እስካሁን ድረስ በተሰራው የህግ ማስከበር ሥራ በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ነው ያሉት።

ከዚህ ውስጥ ከ40 በላይ የሚሆኑት በፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው የነበሩ እንደሆኑ ጠቅሰው፥ 210 በነፍስ ግድያ የተጠረጠሩ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ አሁን ላይ ሕገ ወጦችን ለመያዝ ከሚደረግ ሥራ ውጭ ክልሉ አስተማማኝ ሰላም ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። መንግሥት የክልሉን ዘላቂ ሰላም የማስጠበቅ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኃላፊው በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡ ትክክለኛውን የፋኖ ስም የማይወክሉ፣ በፋኖ ስም ተደራጅተው በሕዝብ ላይ የተለያዩ ሕገ ወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ ቡድኖችን መንግሥት እንደማይታገስም አቶ ደሳለኝ ገልጸዋል። ትክክለኛ የፋኖ አባላትን በመንግሥት መዋቅር ሥር በማድረግ እንዲሠሩ እየተደረገ መሆኑንም ኃላፊው አስታውቀዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡
36.2K views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 10:54:13
በዚህ ሣምንት ከ10 ሺህ ቶን በላይ የምግብ እና የነፍሥ አድን አቅርቦቶች ትግራይ ክልል መድረሳቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ፡፡

የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቶቹ በታጀቡ 163 የጭነት ተሽከርካሪዎች ሁለት ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዛቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም በመረጃው አመላክቷል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም አጋሮቹን አመስግኖ ከፈረንጆቹ ሐምሌ ወር 2021 ጀምሮ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ጭነው ከደረሱት የጭነት ተሽከርካሪዎች ከ100 በላይ የሚሆኑት አቅርቦቶቹን ወደ ክልሉ አድርሰው መመለሳቸውንም አስታውቋል፡፡
35.8K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 07:56:07 ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት ዳያስፖራዉ እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ፡

የትምህርት ሚኒስቴር የጀመራቸውን ሪፎርም ስራዎችና በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት በውጪ ሀገር ነዋሪ የሆነው ኢትዮጵያዊና ትዉልደ ኢትዮጵያዊ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ጥሪ አቀረበ ፡፡

በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች ጋር በተካሄደ ውይይት ላይ የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንደተናገሩት በሁሉም የትምህርት ርከን እየተካሄደ ያለው ሪፎርም ለመጪው የኢትዮጵያ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል፡፡

የሕወሓት ቡድን በፈጸመው ወረራ ምክንያት የወደሙ አጅግ በርካታ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት በትምህርት ሚኒስቴር የግንባታ እቅዶች መቅረባቸውን የገለጹት ፕሮፌሰር ብርሀኑ እነዚህን የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት በውጪ ሀገር ነዋሪ የሆነው ዳያስፖራ ተሳታፊ እንዲሆን ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

በትምህርት ስርአቱ ላይ እየታየ ያለው የጥራት ፣ የብቃትና ሁለንተናዊ ክህሎት ያለው ዜጋን ከማፍራት አንጻር ያለው ችግር ስር የሰደደ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የትምህርት ጥራትና ብቃት ላይ ስርነቀል የሆኑ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ከታችኛው የትምህርት ርከን እስከ ከፍተኛ ትምህርት ድረስ ያለው ችግር ሀገርን ለመገንባት መሰረታዊ ለውጥ የሚያስፈልገው መሆኑን የገለጹት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ለዚህ ስኬታማነት በውጪ ሀገር ያለው ኢትዮጵያዊና ትዉልደ ኢትዮጵያዊ የከፍተኛ ትምህርት ባለሙያና ተመራማሪ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተለይም ሁለተኛ ትውልድ የሆነው ዳያስፖራ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት መሰረታዊ ችግር ባለበት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ በመሳተፍና የእንግሊዝኛ ቋንቋን በማስተማር የትምህርት ስርአቱን የማስተማሪያ ቋንቋ ለመቀየር በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች ያላቸውን ትርፍ ጊዜ ጭምር በመጠቀም በከፍተኛ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፣ በከፍተኛ ትምህርት አመራር ፣ በጥናትና ምርምር ስራዎች ፣ ከሁለተኛ ዲግሪ በላይ እየተማሩ ያሉ ተማሪዎችን የማማከርና የማስተማር ዘርፍ ላይ ቢሰማሩ ለትምህርት ሪፎርሙ ስኬታማነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ መጪው ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን የሚገነባበት እድል ይፈጥራሉ ብለዋል፡፡


በለንደን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈሪ መለሰ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም ከግብ ለማድረስ በዩናይትድ ኪንግደም ነዋሪ የሆኑ ዳያስፖራ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች በአለም አቀፍ ደረጃ በሚቋቋመው የትምህርት ባለሙያዎች የዬኬ ቻፕተር ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ኤምባሲው አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ማለታቸዉን ከኤምባሲዉ ያገኘነዉ መረጃ አመልቷል፡፡
39.3K viewsedited  04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 21:14:52 ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሲሚንቶ ቸርቻሪዎችን ተክተው ሊሠሩ ነው!

የሲሚንቶ ቸርቻሪ ነጋዴዎችን ሙሉ በሙሉ ከስርዓቱ እንዲወጡ በማድረግ በየክልሉ ያሉ የሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተክተው እንዲሠሩ ለማስቻል እየተሠራ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በአሁን ወቅት በገበያው ላይ በቂ የሲሚንቶ ምርት ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ በገበያ ላይ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በአማካይ እስከ አንድ ሺሕ አንድ መቶ ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሆነ እና መንግሥት ሲያደርግ የነበረው የቁጥጥር ሥራ መነሳቱም እየታየ ላለው ችግር አባባሽ ሆኖ እንደተገኘ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ቁምነገር እሸቱ አስታውቀዋል።
22.5K views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ