Get Mystery Box with random crypto!

ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሲሚንቶ ቸርቻሪዎችን ተክተው ሊሠሩ ነው! የሲሚንቶ ቸርቻሪ ነጋዴዎችን ሙሉ | Natnael Mekonnen

ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሲሚንቶ ቸርቻሪዎችን ተክተው ሊሠሩ ነው!

የሲሚንቶ ቸርቻሪ ነጋዴዎችን ሙሉ በሙሉ ከስርዓቱ እንዲወጡ በማድረግ በየክልሉ ያሉ የሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተክተው እንዲሠሩ ለማስቻል እየተሠራ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በአሁን ወቅት በገበያው ላይ በቂ የሲሚንቶ ምርት ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ በገበያ ላይ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በአማካይ እስከ አንድ ሺሕ አንድ መቶ ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሆነ እና መንግሥት ሲያደርግ የነበረው የቁጥጥር ሥራ መነሳቱም እየታየ ላለው ችግር አባባሽ ሆኖ እንደተገኘ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ቁምነገር እሸቱ አስታውቀዋል።