Get Mystery Box with random crypto!

‘‘‹‹በሸኔ ቁጥጥር ስር የነበሩ ቦታዎች አልነበሩም ፤ ነጻ የሚወጡ ቦታዎችም የሉም››’’:- ኮሎኔ | Natnael Mekonnen

‘‘‹‹በሸኔ ቁጥጥር ስር የነበሩ ቦታዎች አልነበሩም ፤ ነጻ የሚወጡ ቦታዎችም የሉም››’’:- ኮሎኔል አበበ ገረሱ ኦሮሚያ አስተዳደርና ጸጥታ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

የክልሉ አስተዳደርና ጸጥታ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ለኢፕድ ሕብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እየወሰደ ባለው እርምጃ የሸኔ እንቅስቃሴ ለሀገር ስጋት በማይሆን ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል::

እንደ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ገለጻ ሸኔ በሚንቀሳቀስባቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች መንገድ በመዝጋት ና ከመኪና አውርዶ ሰውን በመግደል በተወሰነ መልኩ በሕዝቡ እንቅስቃሴ ላይ ፍርሃትና ስጋት እንዲፈጠር አድርጓል:: ሆኖም በድርጊቱ የተማረረው ሕዝብም ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ቡድኑ የሚንቀሳቀስባቸውን ቦታዎች በመከታተል እርምጃ እየወሰደበት ይገኛል::

እስከ አሁን ድረስ ሸኔ ላይ በተወሰደው እርምጃ የተገደሉና የተማረኩ መኖራቸውን ገልጸው በተገኘው ውጤት የሕዝብ እንቅስቃሴ ወደነበረበት ቦታ እየተመለሰ መሆኑን ገልጸዋል ::

እንደ ኃላፊው ገላጻ ሸኔ የታጠቁ የመንግሥት ኃይሎች በማይገኙበት ቦታ ጨለማን ተገን በማድረግ በጫካ ውስጥ እየተሽሎከለኩ ጥቃት ፈጽሞ ከመሸሽ ውጪ የመንግሥት አቅም አሸንፎ የተቆጣጠረው ቦታ የለውም :: ‹‹በሸኔ ቁጥጥር ስር የነበሩ ቦታዎች አልነበሩም ፤ ነጻ የሚወጡ ቦታዎችም የሉም›› ብለዋል። ሸኔ ፊት ለፊት ጦር ግንባር ላይ የሚደረግ ጦርነት የሚከተል ሳይሆን ሽምቅ ውጊያ ሥልት የሚከተል አጥፊ ቡድን ነው::

የሸኔ እንቅስቃሴ ለሀገር ስጋት አይሆንም ሲባል እንደተለመደው ተሸሽገው ህዝቡ ላይ ጥቃት አያደርሱም ማለት እንዳልሆነ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አመላክተዋል:: ሆኖም ይህንን የቡድኑን አጥፊ ድርጊት ለመከላከል መንግሥት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ኮሎኔል አበበ ገረሱ አብራርተዋል::