Get Mystery Box with random crypto!

በዚህ ሣምንት ከ10 ሺህ ቶን በላይ የምግብ እና የነፍሥ አድን አቅርቦቶች ትግራይ ክልል መድረሳቸው | Natnael Mekonnen

በዚህ ሣምንት ከ10 ሺህ ቶን በላይ የምግብ እና የነፍሥ አድን አቅርቦቶች ትግራይ ክልል መድረሳቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ፡፡

የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቶቹ በታጀቡ 163 የጭነት ተሽከርካሪዎች ሁለት ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዛቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም በመረጃው አመላክቷል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም አጋሮቹን አመስግኖ ከፈረንጆቹ ሐምሌ ወር 2021 ጀምሮ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ጭነው ከደረሱት የጭነት ተሽከርካሪዎች ከ100 በላይ የሚሆኑት አቅርቦቶቹን ወደ ክልሉ አድርሰው መመለሳቸውንም አስታውቋል፡፡