Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 173.42K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 384

2022-05-26 19:22:02 ድሮም ችግሩ ወያኔ ነበር እንጂ ይህ አብሮ የኖረ የተዋለደ ህዝብ ምንም ችግር አልነበረበትም ወያኔ ግን ለአግዛዝ እንዲመቸው ይህን ህዝብ ለ27 አመታት ሲያገዳድለው ኖሯል::

#Ethiopia : የአማራ ብሔር ተወላጅ ጓደኛዬ በአደራ የሰጡኝን ቤት አስረክቤያለሁ”- የቅማንት ማህበረሰብ ተወላጅ ከ2006 ጀምሮ በተከሰቱ ግጭቶች ከአይከል ከተማ ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል በአይከል ከተማና አካባቢው ተከስቶ የነበረው ግጭት ዳግም እንዳይነሳ የሚያስችል መግባባት ላይ ተደርሷል

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ጭልጋ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ፈለቀ የ55 ዓመት ጎልማሳ ሲሆኑ በአካባቢው በተደጋጋሚ የሚነሱት ግጭቶች ተረጋግተው እንዳይኖሩ ሲያደርጓቸው እንደቆዩ ይገልጻሉ።

በሌሎች ጊዜያት ከተነሱት ግጭቶች በላይ ባለፈው ዓመት ሚያዚያ 2013 ዓ.ም የተነሳው ግጭት አቶ ሀብታሙን ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል። ሚያዚያ 2013 ዓ.ም ግጭት ተነስቶ ንብረት ሲወድምና የሰው ህይወት ሲጠፋ አቶ ሀብታሙ አካባቢውን ለቀው ለመሄድ መነሳታቸውን ይናገራሉ።

አቶ ሀብታሙ የአማራ ብሔር ተወላጅ ሲሆኑ ቤት ንብረታቸውን ለቅማንት ብሔረሰብ ተወላጁ ጓደኛቸው አስረክበው ወደ ጎንደር ከተማ እንደመጡ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል።

ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በተደጋጋሚ ሲነሳ የነበረው ግጭት በማንነት ምክንያት ሆኖ ሳለ የአማራ ብሔር ተወላጅ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ቤት ንብረታቸውን እንዲጠብቁላቸው አደራ የሰጡት ግን ለቅማንት ማህበረሰብ ተወላጁ ሀብቱ በላይ እንደሆነ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል።

አል ዐይን አማርኛ፤ የጓደኛቸውን ቤት ላለፉት ወራት በአደራ መልክ ጠብቀው ያቆዩትና ትናንት ያስረከቡት አቶ ሀብቱ በላይ በስልክ አነጋግሯቸዋል። ላለፉት ወራት የጓደኛቸውን ቤት እንደራሳቸው አድርገው ከዘረፋና ከውድመት ሲጠብቁ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ግለሰቦች በዚህ ልክ አደራ የሚሰጣጡ ከሆነና የሚደማመጡ ከሆነ እንደት በሁለቱ ወገኖች መካከል ግጭት ተከሰተ ሲል አል ዐይን ላቀረበው ጥያቄ አቶ ሀብቱ “እኛ የምናውቀው ነገር ለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው፤ ቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቅዴፓ) የሚባል ቡድን የችግሩ ጠንሳሽ ነው” ሲሉ ነው የቅማንት ብሔረሰብ ተወላጁ የገለጹት።

ከስምንት ዓመት በፊት በማንነት ምክንያት እንደተነሱ በተገለጹ ግጭቶች አቶ ሀብታሙን ጨምሮ በርካቶች መፈናቀላቸው የሚታወስ ሲሆን ፤ከ 11 ሺህ በላይ የሚሆኑት ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል ተብሏል።

ነዋሪዎቹ ወደ አይከል ሲመለሱ የከተማው ነዋሪዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል። አቶ ሀብታሙ ከተፈናቀሉበት አካባቢ ወደ ቀድ መኖሪያቸው ከመመለሳቸውም በላይ በአደራ መልክ የሰጡት ቤታቸውን እንደነበረ መቀበላቸውን ገልጸዋል።

በግለሰብና በህዝብ መካከል ምንም ችግር እንደሌለ የእርሳቸውና የአቶ ሀብቱ ንግግርና አደራ ማክበር ብቻውን ማሳያ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ከአይከል ከተማ ተፈናቅለው የነበሩት ሌላኛው ግለሰብ አቶ ሽኩር መሐመድም ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል። ወደ ከተማ ሲመለሱም ቤትና ንብረታቸውን በሰላም እንዳገኙት ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል።

አማራ እና ቅማንት በሚል ሕዝቡ እንዲጋጭ የተደረገው “የቅማንት ኮሚቴ” ተብሎ በሚጠራው ቡድን እንጅ በሕዝብ መካከል እንዳልሆነም ነው አቶ ሽኩር ያነሱት።

ወደ ቀያቸው የተመለሱት ተፈናቃዮች ጊዜያዊ ድጋፍ እና ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ መንግስት ሊሰራ እንደሚገባ አንስተዋል።

የአይከል ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ መላኩ አለም አንተ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ በአካባቢው ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰቱ ግጭቶች ከአካባቢ ርቀው የነበሩ ዜጎች ዛሬ አይከል ከተማ መግባታቸውን ለአል ዐይን አማርኛ አረጋግጠዋል። አቶ መላኩ እንዳሉት ግጭቶቹ በተቀሰቀሱ ጊዜ አካባቢውን ለቀው ከተፈናቀሉ ዜጎች በተጨማሪም እጃቸው እንዳለበት የሚጠረጠሩም ወደ ከተማዋ መምጣታቸውን ተናግረዋል።

በግጭቶቹ እጃቸው እንዳበት የሚጠረጠሩ ዜጎች “መንግስት በሚጠይቀን ለመጠየቅ ዝግጁ ነን” በማለት እጃቸውን ለመንግስት እንደሰጡም ሃላፊው ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል።

ዜጎቹ ወደ አይከል ከተማ የተመለሱት አካባቢው ከግጭት ነጻ መሆኑ ለተፈናቃዮች በመገለጹ ሲሆን የከተማዋ ነዋሪዎችም የተፈናቀሉት ወገኖች እንዲመለሱ በመጠየቃቸው መሆኑ ተገልጿል።

በአማራ ብሔር እና በቅማንት ብሔረሰብ መካከል ግጭት እንዲነሳ ያደረገው ህወሃት መሆኑን አቶ መላኩ ገልጸዋል። አል ዐይን አማርኛ ግጭት ቀስቃሹ ህወሃት ስለመሆኑ ምን ማስረጃ እንዳላቸው የጠየቃቸው አቶ መላኩ፤ ለዚህ ማሳያ መኖሩን ገልጸው ዝርዝሩ ግን ለህግ የሚቀርብ እንደሆነ ገልጸዋል።

“የቅማንት ኮሚቴ” በሚል ይጠራ የነበረው ቡድን ከህወሃት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደነበረው ያነሱት ሃላፊው፣ የኮሚቴ አባላት ነን ያሉ አካላት ለህክምና በሚል ወደ ትግራይ መሄዳቸው መረጋገጡን አንስተዋል።

የኮሚቴው አባላት ህክምና መሄድ አስፈልጓቸው ከነበረ ቅርብ ወዳሉ የአማራ ክልል የጤና ተቋማት መሄድ ይችሉ እንደነበር የገለጹት አቶ መላኩ ወደ ትግራይ መሄዳቸው ከህወሃት ጋር ግንኑነት እንዳላቸው ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

የአይከል ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ መላኩ አለም አንተ “የቅማንት ኮሚቴ” የሚባለው ቡድን ዓላማው ግጭት መፍጠር ነበር ያሉ ሲሆን፤ አሁን ግን በራሱ ጊዜ መፍረሱን ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት የቅማንት ብሔረሰብ ተወካይ እንደሆኑ ገልጸው የነበሩ አካላት ቀበሌዎችን እንዲያስተዳድሩ ጥያቄ አቅርበው የክልሉ መንግስት 42 ቀበሌዎችን እንዲያስተዳድሩ የፈቀደ ቢሆንም ተቃውሞ በመነሳቱ ምክንያት መጨረሻ ላይ 69 ቀበሌዎችን እንዲያስተዳድሩ ተፈቅዶ ነበር። ይሁንና ግጭቱ በዚህም ባለመቋጨቱ ላለፉት 8 ዓመታት ግጭት ሲከሰት ቆይቷል።

የክልል፣ ዞንና ከተማ አስተዳደር የሥራ ሃላፊዎች ከዚህ በኋላ ግጭቱ ዳግም እንዳይነሳ እየተሰራ መሆኑን ደጋግመው ገልጸው የነበረ ቢሆንም ችግሩ ግን ሳይፈታ ቆይቷል። የአይከል ከተማ አስተዳደር ዛሬ እንዳለው ከሆነ ከዚህ በኋላ በአካባቢው ግጭት እንዳከሰት ሕዝቡና የጸጥታ አካላት ከጠዋት እስከ ማታ፣ ከማታ እስከ ጠዋት ስምሪት አድርገው ይጠብቃሉ ብሏል።

የአማራ ክልል መንግስት በጭልጋና አካባቢው ከሚነሱት ግጭቶች ጀርባ ህወሃት እንዳለበት በተደጋጋሚ ቢገልጽም፤ ህወሃት ግን በአማራ ክልል በሚነሱ ግጭቶች ላይ ግን ምንም ተሳትፎ እንደሌለው ይገልጻል።
29.6K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 19:21:59
ለመኪናዎ ደህንነት ጉዳይ እንቅልፍ ማጣት ቀረ ATLANTA GPS ለዚህ መፍትሄ ይዞ መጥቷል እኛ ጋ በመምጣቶ ከሚያገኙት ጥቅሞች በጥቂቱ በእጅ ስልኮ መኪናዎን መቆጣጠር ፣ከርሶ ዉጪ መኪናዎን ማንም እንዳያስነሳ መቆጣጠር። ሌባ መኪናዎን ለመስርቅ ቢሞክርና ጂ ፒ ኤሱን መንቀል ቢችል እንኳን መኪናዎ እንዳይነሳ የሚያደርግ። ካሉበት ቦታ ሆነዉ በእጅ ስልኮ ብቻ በመጠቀም የመኪናዎን ሞተር ማጥፋት መቻል።

መኪናዎ መንቀሳቀስሲጀምር/ሲነሳ በስልኮ የማስጠንቀቂያ መልክት የሚልክ። እነዚን እና ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ከ1 አመት ዋስትና ጋር እንሰጣለን አድራሻችን ፡-ወሎሰፈር ከ ቴሌ ፊትለፊት kt 12 ህንጻ 1 ፎቅ ለተጨማሪ መረጃ 0947925678 Instagram @atlanta_gps
TikTok @atlantagps
Facebook @atlantagps
Email @ atlantagpsdivice@gmail.com
Phone@+251947925678@0911909181

•ንብረቶን በእጆ
26.0K viewsedited  16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 17:17:03
33 የሸኔ አባላትን ጨምሮ 145 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዞን አስታወቀ፡፡
በኦሮሞ ብሄረሰብ አሥተዳደር እየተካሄደ ባለው ህግ የማስከበር እርምጃ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸውን ዋና አስተዳዳሪው አቶ አህመድ አሊ ገልጸዋል፡፡
ዋና አስተዳዳሪው በሰጡት መግለጫ ÷ኅብረተሰቡ የህግ የበላይነት አልተከበርም የሚል ጥያቄ ሲያነሳ መቆየቱን ገልጸው፤ በሳምንት ውስጥ በተከናወነው ስራ 33 የኦነግ ሸኔ አባላትን ጨምሮ 145 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር  ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡
ተጠርጣሪዎችን ለይቶ ለህግ ለማቅረብ ከኅብረተሰቡ ጋር በጋራ እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው÷ በዚህም በዞኑ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነው የጠቆሙት።
በህግ ማስከበር ዘመቻው ንፁሃን ያለአግባብ እንዳይያዙ በጥንቃቄ እየተሰራ እንደሚገኝም ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።
የተጀመረው የህግ ማስከበር ተግባር ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ከአጎራባች ዞኖችና ክልሎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ መናገራቸውንም አሚኮ ዘግቧል፡፡
31.2K views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 16:26:55 ቻይና “ለአሜሪካ ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው” ያለችውን ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን አቅራቢያ አደረገች

ቻይና በቅርቡ በታይዋን አቅራቢያ ጠንከር ያለ ወታደራዊ ልምምድ አድርጋለች። አሜሪካ፤ ታይዋንን ከቻይና ወረራ ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል አስታውቃለች።
https://am.al-ain.com/article/military-drills-near-taiwan-are-solemn-warning-to-washington-beijing
32.6K views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 16:18:05
ይህ ደግሞ የህወሓቱ ምግበ መኖሪያ ቤት ነው አዲስ አበባ
31.8K views13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 15:59:23
#Ethiopia : የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ የኦንላይን አገልግሎቶችን በመጠቀም ጉዞዎን ቀላል እና ቀልጣፋ እንዲያደርጉ ይጋብዝዎታል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
31.8K views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 15:08:23
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ማላቦ ገቡ

#Ethiopia : ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት ኢኳቶሪያል ጊኒ ርእሰ ከተማ ማላቦ ገብተዋል፡፡ በናይጄሪያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፥ ጉብኝቱን አጠናቀው በአፍሪካ ሕብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ነው ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ማላቦ የገቡት፡፡

በቆይታቸውም በሰብዓዊ እርዳታ ፣ ፀረ ሽብር ጉዳዮች ላይ እና ኢ-ሕገመንግሥታዊ በሆነ መንገድ ሥልጣን ለመያዝ የሚደረጉ ጥረቶችን መከላከል ላይ በሚያተኩረው በሕብረቱ ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እንደ ኢቢሲ ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማላቦ ሲደርሱ በአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
33.8K views12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 14:48:55
#Ethiopia : በቀድሞ የቦሌ ክፍለ ከተማ በአሁኑ ለሚ ኩራ የአባይ ጸሀዬና ቤተሰቡ ህንጻዎችና ቤቶችን ይመልከቱ!
32.3K views11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 14:22:48
#NewsAlert

በአዲስ አበባ በሽብር እና በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ 349 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!!

#Ethiopia : በአዲስ አበባ በሽብር እና በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ 349 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ሲል በፌደራል እና በአዲስ አበባ ፖሊስ የተቋቋመ ግብረ ኃይል አስታወቀ።

በከተማዋ የተፈፀሙ ወንጀሎች ሀገሪቱን 580 ሚሊዮን ብር በላይ አሳጥቷታል ተብሏል። ሽብርተኝነት፣ የተደራጀ ዘረፋ፣ ሙስና እና የተለያዩ ወንጀሎች በከተማዋ ሲፈፅሙ እና ለመፈፀም የተዘጋጁ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ተነስቷል።

አልሻባብ የተለያዩ ግለሰቦችን መርጦ አዲስ አበባ ያሰረጋቸውና የሽብር ድርጊት ሊፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ተብሏል።አሸባሪው ሸኔ በህዕቡ ተደራጅቶ አዲስ አበባ ላይ ሽብር ለመፍጠር የሚያደርገውን እንቅስቃሴም በምርመራ ላይ መሆኑ በመግለጫው ተነስቷል።

በአዲስ አበባ ለሽብር እና ለተለያዩ ወንጀሎች ሀሰተኛ መታወቂያን ስነምግባር የጎደላቸው የወረዳ ሰራተኞችን በመደለል 47 መታወቂያ የወሰዱ መኖራቸው ተገልጿል። በከተማዋ የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ብሄርን ከብሄር፣ ህዝብን ከመንግስት ለማጋጨት እና በከተማዋ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ የሚሰሩ ተጠርጣሪዎች ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ተብሏል።
32.0K views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 14:22:14
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለፀጥታ አካላት በተዘጋጀው የእውቅና መርሃ ግብር ለመታደም አሶሳ ገቡ።

#Ethiopia : የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሰላምና ፀጥታን ለማስከበር ለሠሩ የፀጥታ አካላት በተዘጋጀው የእውቅና መርሃ ግብር ለመታደም አሶሳ ከተማ ገብተዋል፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ወደ ከተማዋ ሲገቡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የካቢኔ አባላት አቀባበል ማድረጋቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በመርሃ ግብሩ ለመከላከያ ሰራዊትና ለሌሎች የፀጥታ ኀይሎችና ተቋማት እውቅና እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
28.6K views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ