Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 173.42K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 383

2022-05-27 15:01:50
An African inspiration, Bravo Ethiopian Airlines.

Must Watch : ይህ ሁሉ የሚሆነው በራሳችን ሃገር በራሳችን ዜጎች እንዲሁም በራሳችን ሃገር ምርቶች ነው:: የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ኩራት!
26.8K views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 14:14:25
መንግሥት እየወሰደ ባለው ሕግ የማስከበር እርምጃ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከ500 በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ጥላ ሥር መኾናቸውን ዞኑ አስታውቋል።

በሕግ ማስከበር እርምጃው በቁጥጥር ሥር የዋሉት በነፍስ ግድያ፣ በሕገወጥ የመሳሪያ ዝውውርና በዝርፊያ ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው ተብሏል፡፡ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ አቶ መንበሩ ዘውዴ በዞኑ በቡድንና በተናጠል የተደራጁ ኀይሎች የኅብረተሰቡን መደበኛ እንቅስቃሴ በማስተጓጎል ሕዝቡ በመንግሥት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው ሲሠሩ መቆየታቸውንም ተናግረዋል።

የሕግ የበላይነት እንዲከበር ከኅብረተሰቡ በተነሳው ብርቱ ጥያቄና በመንግሥት በተወሰደ እርምጃ እስካሁን 527 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል ያሉት ምክትል አሥተዳዳሪው ሕዝቡ ተጠርጣሪዎችን በመጠቆምና ለፀጥታ አካላት አሳልፎ በመስጠት እየደገፈ መኾኑንም አንስተዋል።

በዞኑ በተካሄደው የሕግ ማስከበር እርምጃ ተጠርጣሪዎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ ከየአካበቢው የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ጥረት መደረጉን ተናግረዋል።

በሕግ ጥላ ሥር የሚገኙ ኹሉም ተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ መብታቸው ተጠብቆ ተገቢውን የፍርድ ውሳኔ እንዲያገኙ በየደረጃው ከሚገኙ አካላት ጋር እየተሠራ መኾኑንም አመላክተዋል።

የሕግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ ከተጀመረ በኋላ በዞኑ ውስጥ በስፋት ይስተዋሉ የነበሩ ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ ሥርቆት እና ሕገወጥ የጥይት ተኩስ መቀነሱንም አቶ መንበሩ ገልጸዋል።

በዞኑ ከሕግ ማስከበር እንቅስቃሴው በተጓዳኝ ሕዝቡ የልማት ተግባራት እንዲያከናውን በትከረት እየተሠራ ነው ብለዋል።

የዜጎችን ሰላም ለማረጋገጥ እየተወሰደ ያለው ሕግን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት አቶ መንበሩ ሕዝቡ ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ ለመስጠት ያሳየው ተነሳሽነትም አበረታች ነው ብለዋል።
29.0K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 14:01:17
ሩሲያን ለመነጠል እየሞከሩ ያሉ ሃገራት የራሳቸውን ኢኮኖሚ እያዳከሙ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ። ፑቲን በእስያ አውሮፓ የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ሩሲያን ማግለልና መነጠል የማይቻል መሆኑን አስረድተዋል።

አያይዘውም ይህን ለማድረግ የሚሞክሩና በሩሲያ ላይ የሚያሴሩ ሃገራት እራሳቸውን ይጎዳሉም ነው ያሉት።

“ዓለም ላይ ጠንካራ ኢኮኖሚ ያላቸው ሃገራት አሁን ላይ ከባድ የዋጋ ግሽበትና ከፍተኛ የሆነ የስራ አጥ ዜጎች ቁጥር እያስተናገዱ” መሆኑንም አመላክተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ዓለም አቀፉ ቀውስ እጅግ ተባብሷል ማለታቸውን ሺንዋ በዘገባው አመላክቷል።

“ይህም መላው የኢኮኖሚ ስርአትና ፖለቲካዊ ግንኙነቶች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ ጉዳይ” መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሃገራትን ለማዳከም በማሰብ የሚጣሉ ማዕቀቦችና ገደቦችም እርባና ቢስና ጠቀሜታ የሌላቸው ናቸው ብለዋል ፑቲን በንግግራቸው።
29.1K views11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 12:49:42
በምዕራብ ጎጃም ዞን በተለያዩ ህገ-ወጥ የወንጀል ድርጊቶች የተጠረጠሩ 595 የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።

#Ethiopia : የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ በሰጡት መግለጫ በህግ ማስከበር እንቅስቃሴው ውስጥ በማናቸውም ዓይነት ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ የሚጠረጠር ሰው ያለ ምንም ልዩነት በእኩል ወደ ህግ እንዲቀርብ የማድረግ ስራ በመሰራት ላይ ነው ብለዋል። በዚህም በዞኑ እስካሁን በድምሩ 595 የሚሆኑ ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመዋል።

በህግ ማስከበር ስራው አንዳንድ ያጋጠሙ መስተጓጉሎች እንደተጠበቁ ሆነው ከሞላ ጎደል በሰላማዊ መንገድ በመፈፀም ላይ ነው ብለዋል ሀላፊው።

ይህም ሊሆን የቻለው በዋናነት ህግ አክባሪና ጨዋ በሆነው ህዝብ ተባባሪነትና መሪ ተዋናይነት እንደሆነ ተናግረዋል።

ህግ ማስከበር ስራው ህጋዊና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሚያረጋግጥ መንገድ መፈፀም የሚገባው በመሆኑ በተለያዩ ምክንያቶች የተሰሩ ስህተቶች በተገቢውና በአጭር ጊዜ ፈጥነው እንዲፈቱ ይሰራል ብለዋል።

በየደረጃው ያለው የህብረተሰብ ክፍል የተጀመረው የህግ ማስከበር ስራ እንዲሳካ እንደ እስከዛሬው ሁሉ በቀጣይ ስራዎች አንድነትና ትብብርን አጠናክሮ እንዲቀጥል መነገሩን ከአማራ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
30.6K views09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 12:34:06
"ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!" በሚል ቁጭት ነው ኢትዮጵያን የሚመጥን የመከላከያ ኃይል ለመገንባት እየሠራን ያለነው።

የጦር ኃይሎች ም/ጠ/ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ
28.9K views09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 12:26:48
በትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ ትናንት ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ገለጸ።በአደጋው በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንና የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን የኤጀንሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የእናትና ልጅ ህይወት ማለፉን የጣርማ በር ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። አደጋው አስፍቸው ቀበሌ ልዩ ቦታው ጭራሜዳ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የደረሰ መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ሸዋታጠቅ ኃይለስላሴ ተናግረዋል።

ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ባቲ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ አምቡላንስ ተሽከርካሪ መንገድ ዳር መኪና በመጠበቅ ላይ የነበሩ እናትና ልጅ ገጭቶ ህይወታቸው ማለፉንም ነው የተናገሩት። ዋና ኢንስፔክተሩ አያይዘውም በአደጋው ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል አደጋ ደርሷል ብለዋል፡፡ አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ በህግ ከለላ ውስጥ እንደሚገኝና የአደጋው መንስዔ እየተጣራ መሆኑን የጣርማ በር ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።
28.4K views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 00:28:26
#Ethiopia : እኔ የኤርሚያስና ሃብታሙ አይገርመኝም የብሩክ ይባስ እንጂ ኤርሚያስም ሆነ ሀብታሙም መረጃን ከኪሳቸው እንደሚስቡ የታወቀ ነው የብሩክ ግን እንዲህ መሆን ሁሌም ድንቅ ነው የሚለኝ! እውነት ግን በዚህ ደረጃ ህዝብን መዋሸት ለምን አስፈለጋቸው?
6.1K views21:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 00:00:12
አቡኪ አንተ ለኔም ጭምር ኡስታዜ ነህ!
8.0K views21:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 22:57:50
በሬ ወለደ ተረት… ለምን አላማ?

በማህበራዊ ገፆች እና በአንዳንድ ዩቲዩቦች "የሶማሌ ክልል ሚሊሻ ወደ አማራ ክልል ሊሰማራ ነው" የሚል ሀሰተኛ የበሬ ወለደና ሆን ተብሎ የተቀናበረ ውዥንብር እየተሰራጨ ይገኛል።

ይህ በሬ ወለደ የቅዠት ወሬ እየተሰራጨ የሚገኘው ከያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮ የክልሉን ፖሊስ ለማጠናከር ቀደም ብሎ በተያዘ እቅድ መሰረት ከተለያዩ የዞኑ አከባቢዎች የተመረጡ 500 የሚደርሱ የሚሊሻ አባላት የመደበኛ ፖሊስ ስልጠናን በመውሰድ እንዲቀላቀሉ መጠራታቸውን ተከትሎ መሆኑን ከክልሉ ፀጥታ ቢሮ ያገኘውት መረጃ ያሳያል።

ይህን እውነታ በመካድ "የሶማሌ ክልል ሚሊሻ ወደ አማራ ክልል ሊሄድ ነው "የሚል በሬ ወለደ የሀሰት መረጃን የሚያናፍሱ አካላት አላማ ሆን ተብሎ የታቀደና ምድር ላይ ያለውን እውነታ ለራሳቸው እና ለላካቸው ቡድን በሚመች መልኩ በማጣመም ውዥንብር ለመፍጠር ያለመ እንደሆነና ወደ አማራም ሆነ ወደ ሌላ ክልል የሚላክ ሃይል እንደሌለ ከክልሉ የፀጥታ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል።
13.3K views19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 19:22:14
29.9K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ