Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ዳዊት

የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የሰርጥ አድራሻ: @mezmurochh
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 43.70K
የሰርጥ መግለጫ

🔔🔔🔔 መዝሙረ-ዳዊት 🔔🔔🔔

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉ
☞ @mezmurochh
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
☞ @Mezmuredawit_bot ላይ ያገኙናል

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 33

2022-11-20 12:58:22
ትላን ከተነሳ ሳሊተ ምህረት
2.9K views••●◉ Estifanos ◉●••, 09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 22:33:21 ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ

ትርጉሙም

ለመንግሥቱ ፍፃሜ የለውም
  ጸሎት ሃይማኖት ወሠለስቱ ምዕተ ወጉባኤ ኒቅያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለአበው ቅዱሳን ወ318ቱ ሊቃውንት አው ጉባኤ ኒቅያ ዓመታዊ በዓል በስላም አደረሳችሁ አደረስን

ህዳር ፱(9) ይስሐቅ ሊቀ ጳጳስት ዘእስክንድርያ ወጉባኤሆሙ ለ፫፻፲ወ፰ ርቱዓነ ሃይማኖት በኒቅያ ለእለእስክድሮስ ሊቅ  ወአትናቴዎስ ሐዋርያዊ

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

ንጉሥ ለይትፌሣሕ በእግዚአብሔር
ወይከብር ኩሉ ዘይምሕል ኪያሁ
እስመ ይትፈጸም አፍ ዘይነብብ ዐመፃ

✤ ትርጉም ✤

ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል
በእርሱ በሚምል ሁሉ ይከበራል
ሐሰትንም የሚናገር አፍ ይዘጋል
            መዝ ፷፪-፲፩
                   62   11

✤ ወንጌል ✤

ማቴ ም ፲፰ ቁ ፲፪-፳፫
           18     12  23

የቅዳሴ ምንባባት

ቆላ ም ፪ ቁ ፭-፲፫
፪ ዮሐ ም ፩ ቁ ፮-፲፪
ግብ.ሐዋ ም ፲፭ ቁ ፳፪-፴

❖ ምስባክ ❖

ወነበቡ ዓመፃ ውስተ ዓርያም
ወአንበሩ ውስተ ሰማይ አፉሆሙ
ወአንሶሰወ ውስተ ምድር ልሳኖሙ

ትርጉም

ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ
አፋቸውን በሰማይ አኖሩ
አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ

             መዝ ፸፪-፰
                    72  8

❖ ወንጌል ❖

ዮሐ ም ፲ ቁ ፳፭-ፍ.ም
         10     25  ፍፃሜው

❖ ቅዳሴ ❖

ዘ፫፻(ግሩም) ሠለስቱ ምዕተ

" የተቀበል እኛ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ነን፤ሃይማኖትን ያቀናን ሙሽራዋ አምላካችን እግዚአብሔር የሆነ የቅድስት ቤተክርስቲያንን ህግ የሠራን "
     ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕተ
              ም ፩ ቁ ፻፵፬
                  1     144

በዓሉን በዓለ ምህረት በዓለ ፀጋ ያድርግልን ቸሩ አምላክ ዘላለም ሥላሴ በቸርነቱ ይማረን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምልጇዋ ትጠብቅ ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን ታሳደርብን በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ይጠብቅን ቤተክርስቲያን ቅድስት በረድኤት ይጠብቅልን ከ 318ቱ ሊቃውንት በረከታቸው ይደርብን ጉባኤ ሊቃውንት ጉባኤ የተቀበለ የኛንም ፆም ፀሎት ምሕላ ይቀበልልን በቅዱሳኑ በሰማዕታት ፀሎት ይማረን ከሊቁ ከአባታችን ከለእለእስክድሮስ ቅዱስ አትናቴዎስ ሀዋርያው በረከታቸው ይደርብን የእነሱ ሃይማኖት ያፀና የእኛም በሃይማኖት በምግባር ያጸናን አምላክ ቅዱሳን ለሃገራችን ስላም ለህዝባችን አንድነት ይስጥልን ለሃገራችን ለቤተክርስቲያን እንፀልይ ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን የአበው በረከት በሁላችንም ላይ ያሳደርብን አቤቱ ባሪያ የሚሆነውን ሳዕለ ሥላሴ አስበው ለመሪዎች ሁሉ አስተዋይ ልቡና ይስጥልን ለተዋህዶ ልጆች በሙሉ የቂም እና የፀብ ጊዜ አይደለም ሁላችንም የሚሆን የሚበጅው ፍቅር ስላም አንድነት ነው ፍቅር ስላም ያድለን ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ የቃል ኪዳን ምድር ጠብቅ አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ አባታችን ሆይ ሃገራችን አቤቱ ጠብቅልን ከሚታየው ሁሉ ነገር ጠብቀን ደም ሰማዕታት የተቀበለ አምላክ ስለ ቀናች ሃይማኖት ራሳቸውን የሰጡት ሁሉ ደማቸውን ጸናታቸው ለሁላችንም ሰጠን አምላክ ሰማዕታት ሁላችንም የዳዊት መዝሙር መዝሙር ፹፬(84) ሁላችንም እንፀልይ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
5.3K views••●◉ Estifanos ◉●••, 19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-16 20:31:31
ዛሬ ካነሳውት / ፒያሳ/ ቅዱስ ጊዮርጊስ
6.2K views••●◉ Estifanos ◉●••, 17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-16 08:58:23
መንፈሳዊ ጉዞ ወደ እመጓ እና ሰረርኩላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

የጎዞው መነሻ ቀን ህዳር 11 12 ቅዱስ ሚካኤልን አንግሰን በ 13 መመለሻ

የጎዞ ዋጋ 900 ብር መስተንግዶን ማረፊያን ጨምሮ

መነሻ ሰአት 11 እሁድ

መነሻ ቦታ መስቀል አደባባይ
               መገናኛ
               አያት አደባባይ

በዚህ ስልክ ደውለው መመዝገብ ይችላሉ 0991324844
6.2K views••●◉ Estifanos ◉●••, 05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 21:30:51
ዛሬ ካነሳውት ቃሊቲ ቊስቋም ማርያም ቤ/ክ

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥@teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
6.6K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 21:27:03 ተመየጢ ተመየጢ ሱላማጢስ ተመየጢ ወንርአይ ብኪ ሰላም

ትርጉሙም

አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ

   መኃ ም ፯ ቁ ፩
              7     1

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ የቅዳሴ ቤት ዓመታዊ በዓል በስላም አደረሳችሁ አደረስን

ህዳር ፯(7) ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ ወአባ ሚናስ ወቅዳሴ ቤቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ልዳዊ ወዘኖቢስ ወዘኖብያ መርቆሬዎስ ወአኁሁ ዮሐንስ ዘተመትረ ርእሱ

✥ ዘነግህ ምስባክ ✥

መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁ
አምላክ እስራኤል ውእቱ ይሁብ ኀይለ ወጽንዐ ለህዝቡ
ወይትባረክ እግዚአብሔር

✥ ትርጉም ✥

እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ድንቅ ነው
የእስራኤል አምላክ እርሱ በኃይልህ ብርታትንም ለህዝቡ ይሰጣል
እግዚአብሔርም ይመስገን

            መዝ ፷፯-፴፭
                   67   35

✥ ወንጌል ✥

ዮሐ ም ፲፬ ቁ ፩-፲፭
           14    1   15

የቅዳሴ ምንባባት

ኤፌ ም ፭ ቁ ፳፫-፳፰
ዓዲ
፩ ቆሮ ም ፯ ቁ ፳፭-ፍ.ም
፩ ጴጥ ም ፬ ቁ ፲፪-ፍ.ም
ግብ.ሐዋ ም ፳፰ ቁ ፩-፲፩
              ም ፳፯ ቁ ፳፩-፳፯

❖ ምስባክ ❖

ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ
በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ
ይባዕ ቅድሜከ ገዓሮሙ ለመቁሓን

ትርጉም

የፈሰሰውንና የባሮችህን ደም በቀል
በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ
የባሮችህንም ጭንቀት ወደፊትህ ይግባ

           መዝ ፸፰-፲
                 78   10

❖ ወንጌል ❖

ማቴ ም ፲ ቁ ፲፮-ፍ.ም
          10    16   ፍፃሜው

❖ ቅዳሴ ❖

ዘባስልዮስ

" በልቡናው ስለ አብያተ ክርስቲያናትህ ተናገር እኛ በዕረፍትህ በጸጥታ እንኖር ዘንድ ስጠው፤በአንተ ቸርነት ሁሉ ትዕዛዛህን ለመጠበቅ የበቃን ሁነን እንገኝ ዘንድ "
         ቅዳሴ ባስልዮስ
                ም ፩ ቁ ፷፯
                    1     67

በዓሉ በዓለ ምህረት በዓለ በረከት ያድርግልን ቸሩ መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይማረን ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ምልጇዋ ይጠብቅ በዕፅ መስቀሉ ይባረክን ቅድስት ቤተክርስቲያን በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን በቅዱሳኑ ፀሎት ይማረን ከሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በረከቷ ይደብርን በቃልኪዳኑ ሃገራችን ይጠብቅልን ለሃገራችን ለህዝባችን ፍፁም ስላም ይሰጣልን አምላክ ቅዱሳን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን ምህላ ነቢያት ወሐዋርያት የተቀበለ የኛንም ፀሎት ምህላ ይቀበልልን እመ አምላክ ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን ታሳደርብን ለብርሃነ ልደቱ በስላም ያድርሰን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
5.7K views••●◉ Estifanos ◉●••, 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 11:38:17
እንደምን ዋላችሁ

ለእመጓ ቅዱስ ዑራኤል ፀበልተኞች አሉ እባካችሁ የምትችሉትን እናድርግ ብዬ በጠየኩት መሰረት የእመቤታችን ማህበርተኞች ሰብስባችሁ ለሰጣችሁኝ ለንፅህና መጠበቂያ የሚሆን ሞዴስ እንዲሁም ልብስ ስኮር ማድረሳችንን እናሳውቃለን ባልኳችሁ መሰረት ይሀው አድርሰን ፎቶውን ሰተናል ላደረጋችሁት ትብብር እመቤቴ ማህበራችሁን ታስፋላችሁ ተሰብስበው ነበረ ተበተኑ ዘምረው ነበረ ዘፈኑ ቆርበው ነበር አፈረሱ ከሚል የምቀኛ የተንኮለኛ ወሬ እመቤታችን ትጠብቃችሁ ያው እንደሚታወቀው እሁድ 11/03/15 ወደ እመጓ ጉዞ አዘጋጅተናል አላማውንም ታቃላችሁ ለመሄድ የደወላችሁልን የተመዘገባችሁ ስትመጡ አንድ እንድ ነገር ። በሶ ፣ ቆሎ፣ ስኮር ፣ ሞዴስ ፣ ልብስ ካላችሁ ይዛችሁ መቲችሁ በድጋሚ እንድንሰጥ በአምላከ ቅዱስ ሚካኤል ስም እንጠይቃለን ስለምታደርጉት ነገር በሙሉ ምስጋናችን የበዛ ነው።
መንፈሳዊ ጉዞ ወደ እመጓ እና ሰረርኩላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

የጎዞው መነሻ ቀን ህዳር 11 12 ቅዱስ ሚካኤልን አንግሰን በ 13 መመለሻ

የጎዞ ዋጋ 900 ብር መስተንግዶን ማረፊያን ጨምሮ

መነሻ ሰአት 11 እሁድ

መነሻ ቦታ መስቀል አደባባይ
               መገናኛ
               አያት አደባባይ

በዚህ ስልክ ደውለው መመዝገብ ይችላሉ 0991324844 ጥያቄ ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ በውስጥ መስመር @Estifo_17 ያናግሩን።
6.4K views••●◉ Estifanos ◉●••, 08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 07:51:48 #ኅዳር_6

#ደብረ_ቁስቋም

ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡

አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡

ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡

ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡

ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡

ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡

እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡

ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡

(ስንክሳር ዘተዋህዶ እና #ገድላት_አንደበት)
5.6K views••●◉ Estifanos ◉●••, 04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-14 19:50:06 ➢ ተማኀፀንኩ በዘባንኪ ዘአግመረ ርስነ መለኮታዌ እሙነ ሐውጽኒ ድንግል ወናዝዝኒ ፍጡነ ➢

  ሰቆቃወ ድንግል ዘደረሰ አባ ገብረኢየሱስ ዘደብረ መጓዬና

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

➢ እንኳን ከ፴፫ቱ ከእመቤታችን በዓላት አንዱ ከስደት ያረፈችበት በዓለ ቊስቋም ማርያም በዓል በሰላም አደረሳችሁ ➢

  ኀዳር ፮ ቦእ እግዚእነ ውስተ ደብረ ቊስቋም ወፊልክስ ሊቀ ጳጳሳት ወተዝካሩ ለአባ ፍሞስ ወለንዲዎስ ወይላጥስ ወማርትሮስ ወኢላስዎስ ወቆርናልዮስ ወሱኪሮስ ወናውኔኖስ ወሊባዲቆ ወሲላስዮስ ወ፪ቱ ፻ወ፸ወ፪ቱ ማኀበረ ኤስድሮስ ሰማዕት

➢ ዘነግህ ምስባክ ➢

ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ
ወማዕነቅኒ ኀበ ታነብር እጐሊሃ
ምሥዋዒከ እግዚአ ኃይላን ንጉሥየኒ ወአምላኪየኒ

ርግብ ለርስዋ ቤት አገኘች
ዋልያም ጫጩቶችዋን የምትኖርበት ቤት አገኘች
የሠራዊት አምላክ ንጉሤም አምላኬ ሆይ እርሱም መሠዊያህ ነው

       መዝ ፹፫ - ፫

➣ ወንጌል ➣

ሉቃ ም ፳፪ ቁ ፲፬ - ፳፬

የቅዳሴ ምንባባት

፪ ቆሮ ም ፰ ቁ ፩ - ፲፮
፪ ዮሐ ም ፩ ቁ ፱ - ፍፃሜው
ግብ.ሐዋ ም ፩ ቁ ፲፪ - ፲፭

ምስባክ

ርኢክዎ ለኃጥእ ዐብየ ወተለዐለ ከመ አርዘ ሊባኖስ
ወሶበ እገብእ ኀጣእክዎ
ኀሠሥኩ ወኢረከብኩ መካኖ

➢ ትርጉም ➢

ኃጥአን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ልምልሞ አየሁት
ስመለስ አንዱም ብመለስ ግን አጣሁት
ፈለግሁትን ቦታውን አላገኘሁም

     መዝ ፴፮ - ፴፭

➣ ወንጌል ➣

ማቴ ም ፪ ቁ ፲፪ - ፍፃሜው

ቅዳሴ

ዘእግዚእነ

" ዓለሙን የምታሳረፈው ሆይ በመስቀል ላይ የተሠወረ ምሥጢርን ያሳየህ አንተ ነህ እንዳንተ ያለ ይቅር ባይና ቅዱስ ማነው "

    ቅዳሴ እግዚእነ

በዓሉን በዓለ በረከት በዓለ ሐሴት ያድርግልን ቸሩ መድኀኔ ዓለም በቸርነቱ ይማረን ከበዓለ ሚጠታ በረከት ትክፈለን በዕፅ መስቀሉ ይጠብቅን ለቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ለቅድስት ሰሎሜ ለቅዱስ ጊጋር መስፍነ ሶርያዊ ለአባ ጽጌ ድንግል ለአባ ገብረኢየሱስ ለአባ ጊዮርጊስ ለቅዱስ ያሬድ ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ለእቴጌ ምንትዋብ የተለመነች ለኛም ትለመነን ቸሪቱ እመ አምላክ ፍቅሯ ይደርብን ለሃገራቸው ፍፁም ሰላም ይስጥልን ሰናይ የበረከት በዓል ያድርግልን በዓልን ተከትሎ ከሚመጣ መቅሠፍት አምላክ ቅዱስ ዮሴፍ ይሰውረን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
5.4K views••●◉ Estifanos ◉●••, 16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-14 15:53:46 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

መዝሙረ ዳዊት

ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
✧ ገሊላ እተዊ ✧

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
@mezmurochh
@mezmurochh
@mezmurochh
|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
4.9K views••●◉ Estifanos ◉●••, 12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ