Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ዳዊት

የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የሰርጥ አድራሻ: @mezmurochh
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.22K
የሰርጥ መግለጫ

🔔🔔🔔 መዝሙረ-ዳዊት 🔔🔔🔔

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉ
☞ @mezmurochh
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
☞ @Mezmuredawit_bot ላይ ያገኙናል

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 26

2023-01-31 19:37:01 ስላም ለሰኮናከ ዘተሴሬ በደም አመ እግርከ ተሰብረ በብዙኃ ቀዊም ተክለሃይማኖት ኢዮብ ዘትዕግስትከ ኢዮብ ዘትዕግሥትከ ፍጹም ለደቂቅከ እለ ውስተ ኵሉ ዓለም ከመ ባረኮሙ ኖኀ ለያፌት ወሴም

መልክአ ተክለሃይማኖት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለሐዲስ ሐዋርያ ለመምህረ ትሩፋት አባታችን ለአቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ አደረስን


ጥር ፳፬(24) ወስብረተ እግሩ ለአቡነ ተክለሃይማኖት ማርያም እስክንድራዊት ወአባ አብሳዲ ወሲፉ ሰማዕት ወአባ መርሐ ክርስቶስ

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

እስመ መምህር ህግ ይሁብ በረከተ
ወየሁውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያሰተርኢ አምላክ አማልክት በጽዮን

✤ ትርጉም

የህግ መምህር በረከትን ይሰጣልና
ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ
የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል

መዝ ፹፫-፮
83 6

✤ ወንጌል ✤

ማቴ ም ፭ ቁ ፩-፲፯
5 1 17

የቅዳሴ ምንባባት

ቲቶ ም ፪ ቁ ፩-፱
፩ ጴጥ ም ፫ ቁ ፩-፭
ግብ.ሐዋ ም ፳ ቁ ፳፰-፴፩

❖ ምስባክ ❖

ካህናቲከ ይለበሱ ጽድቁ
ወጻድቃኒከ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑ
በእንተ ዳዊት ገብርከ

ትርጉም

ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ
ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው
ስለ ዳዊት ስለ ባርያህ

መዝ ፻፴፩-፱
131 9

❖ ወንጌል ❖

ሉቃ ም ፲፰ ቁ ፩-፱
18 1 9

❖ ቅዳሴ

ዘባስልዮስ

" አቤቱ ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና ያልታሰበውን ቅዱስ ስምህን ለሚወዱ ያዘጋጀህ አምላክ ምን ትደንቅ "
ቅዳሴ ባስልዮስ
ም ፩ ቁ ፻፴፪
1 132

❖ ማሳሰቢያ የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ጥር ፳፬ ቀን የሚከበረው የአንድ እግራቸው አገዳ ከመቆም ብዛትና የተሰበረበት ቀን አንድ እግራቸው አገዳ የተሰበረው ጥር ፬ ቀን ነው ግን አባቶች በሠሩት ሥርዓት በዓላቸው በሚከበሩበት ዕለት በ፳፬ እንዲሆን በማድረጋቸው ጥር ፳፬ ቀን ይከበራል



በዓሉን በዓለ ምህረት በዓለ በረከት በዓለ ፀጋ ያድርግልን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ ይማረን እናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ አትለየን በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ይጠብቅን ቤተክርስቲያን በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክትን አያሳጣን ከአባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት በረከታቸው ይደርብን በቅዱሳኑ ፀሎት ይማረን ዝማሬ ዳዊት ቅዳሴ መላዕክት ዕጣነ አሮን መልክአ ተክለሃይማኖት የተቀበለ የኛንም ፆም ፀሎት ምስጋና ምጽዋት በብሩህ ገጽ ይቀበልልን ለአበው ቅዱሳን ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ለአባ ሕርያቆስ ለቅዱስ ያሬድ ለአባ ጊዮርጊስ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት ለቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ ለቅዱስ ደቅስዮስ ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ለቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለአባ ኪሮስ ለአቡነ አቢብ ለአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ለአባ ሳሙኤል ዘቀልሞን ለገብረክርቶስ መርዓዊ ለአቡነ ሃብተማርያም ለቅዱስ ላሊበላ ለአባ ጽጌድንግል ለአባ ገብረማርያም ዘደብረ ሐንታ ለአባ ገብረኢየሱስ ዘመጓዬና ለቅዱስ ቴዎድጦስ ዘእንቆራ ለአቡነ ተክለሃይማኖት ለአበው ቅዱሳን ሁሉ የተለመነች እመ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምህረት ትለመነን ለሃገራችን ስላም ለህዝባችን አንድነት ይስጥልን ሁላችንም ለንስሐ ያብቃን አቤቱ ባሪያህ የሚሆነው ሳዕለ ሥላሴን አስበው ወጣትነታችን አምላክ መርቆሬዎስ ይጠብቅልን ክህነት ያላችሁን አምላክ ተክለሃይማኖት ክህነታችሁን ይጠብቅላችሁ ውዳሴዋን ቅዳሴዋን አይሳታጎልብን ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
4.6K views••●◉ Estifanos ◉●••, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 20:21:18 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

መዝሙረ ዳዊት

✤➫ በሊቀ-መዘምራን ዲ/ን ቴድሮስ ዮሴፍ


✣ ድንግል ትንሳኤሽን ✣

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
@mezmurochh
@mezmurochh
@mezmurochh
|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
6.0K views••●◉ Estifanos ◉●••, 17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 20:18:56 ✞ ​​ድንግል ትንሳኤሽን

ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ
ገብተናል ሱባኤ በአንድነት በመንፈስ
ለእኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት
አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምህረት /2/

ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው
ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው
የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል
ትንሳኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን አይተናል

ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል /2/

አዝ_______

ልናየው ወደድን የቶማስን ክብር
ለምን ተስወረን የትንሳኤሽ ምስጢር
በራችንን ዘግተን በፀሎት ወድቀናል
ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል

ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል/2/

አዝ________

መዝሙረኛ አባትሽ ዳዊት ጽፎልናል
ሞትን የማያይ ስው ማን አለ ብሎናል
ይህ እውነት በዘመን አንቺ ላይ ቢደርስም
በሞት ተሽንፏል መቃብር አይኖርም

ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል /2/

አዝ_________

ቶማስ ከደመናው ወርዶ ሲያናግረን
ስለ ሆነው ነገር እጅጉን ተመሰጥን
እኛም ይህን ክብር ተመኘን ለማየት
ድንግል አሳስቢልን ኪዳነ ምህረት

ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል/2/

መዝሙር
በሊቀ መዘምራን ዲ/ን ቴድሮስ ዮሴፍ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

@mezmurochh
@mezmurochh
@mezmurochh


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
5.7K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 13:47:36
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ"
ቅዱስ ያሬድ

እንኳን ለቤዛዊተ ዓለም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ።

መልካም በዓል ይሁንልን
6.5K views••●◉ Estifanos ◉●••, 10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 23:28:47
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
6.3K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 23:25:15 ስላም ለፀአተ ለነፍስኪ እንበለ ፃዕር ወፃማ ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ ማርያም ድንግል ክልልተ ሞገስ ወግርማ አጽንዒ በረድኤትኪ ለህይወትየ ድካማ እምሕይወት ኄራን አበው ኢታሕጽጺ ዐቅማ

መልክአ ማርያም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ቅዱሳን እግዝእትነ ማርያም ድንግል በዓለ ዕረፍት ዓመታዊ በዓል በስላም አደረሳችሁ አደረስን

ጥር ፳፩(21) በዓለ ዕረፍታ ለእግዝእትነ ወኢላርያ ቅድስት ወጎርጎርዮስ ወኤርምያስ ወጳውሎስ መኰንን ወሲላስ ካህን ወቀውስጦስ ወዮሐንስ ወአባ እስክንድርያ ወአስተርእዮተ እግዝእትነ ማኀው ምስለ ዮሐንስ

✤ ዘነግህ ምስባክ

ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር
ወስብሐዮ ለአምላክኪ ጽዮን
እስመ አጽንዐ መናግሥተ ኆኃትኪ

✤ ትርጉም

ኢየሩሳሌም ሆይ እግዚአብሔር አመስግኚ
ጽዮንንም ለአምላክሽ እልል በዪ
የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና

መዝ ፻፵፮-፩
146 1

✤ ወንጌል ✤

ሉቃ ም ፩ ቁ ፷፯-ፍ.ም
1 67 ፍፃሜው

የቅዳሴ ምንባባት

ገላትያ ም ፬ ቁ ፩-፲፪
፪ ዮሐ ም ፩ ቁ ፩-፯
ግብ.ሐዋ ም ፯ ቁ ፴-፴፭

❖ ምስባክ ❖

በከመ ሰማዕነ ከማሁ ርኢነ
በሀገረ እግዚአ ኃይላን በሀገር አምላክነ
እግዚአብሔር ሣረራ ለዓለም

ትርጉም


እንደ ስማን እንዲሁ አየን
በሠራዊት ጌታ አገር በአምላካችን ከተማ
እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናታል

መዝ ፵፯-፰
47 8

❖ ወንጌል

ሉቃ ም ፩ ቁ ፵፯-፶፯
1 47 57

❖ ቅዳሴ ❖

ዘእግዝእትነ

" እናንተ የክርስቲያን ወገኖች ሆይ በዚህች ቀን እንደ ተሰብስባችሁ እንዲሁ ክብርት በምትሆን በደብረ ጽዮንና በሰማይ ባለች ነፃ በምታወጣ በኢየሩሳሌም ይሰብስባችሁ "
ቅዳሴ ማርያም
ም ፩ ቁ ፻፶፮
1 156

በዓሉን በዓለ ምህረት በዓለ በረከት ያድርግልን በብርሃነ ጥምቀቱ ለሁላችንም ይገለጽልን ቸሩ አምላካችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቸርነቱ ይማረን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ በምልጃዋ አትለየን ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን ታሳድርብን በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ይጠብቅን ቤተክርስቲያን ቅድስት በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን በቅዱሳት ፀሎት ይማረን ከታላቁ ሊቅ ከቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ በረከቱ ይደርብን በዓልን ተከትሎ ከሚመጣ መቅሠፍት አምላክ አቡነ ቀውስጦስ ይሰውረን ይጠብቅን ለሃገራችን ስላም ለህዝባችን አንድነት ይስጥልን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን አቤቱ ባሪያህ የሚሆነውን ሳዕለ ሥላሴን አስበው ድንግል ማርያም ስንል ፍቅሯን ታሳድርብን አቤቱ ለበላይሰብ የተለመነች ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ለቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ለአባ ጊዮርጊስ ለአባ ሕርያቆስ ለቅዱስ ያሬድ ለቅዱሳኑ ሁሉ የተለመነች ሶልያና ቅድስት ድንግል ማርያም በቸርነት ትለመነን ሶልያና ማለት የበራች ጨረቃ ማለት ነው አለምን ያበራው ወልደ እግዚአብሔር የወለደች ድንግል ማርያም የልባችንን መሻት ትፈጽምለን አቤቱ ውዳሴዋን ቅዳሴዋን አያሳጎልብን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
6.3K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 08:19:51
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም  ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
9.3K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 08:19:26 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

መዝሙረ ዳዊት

✤ዘማሪ በርሱፍቃድ እንዳርጋቸው ✤

✣ ሰላም ለኢትዮጵያ ✣

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
@mezmurochh
@mezmurochh
@mezmurochh
|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
7.7K views••●◉ Estifanos ◉●••, 05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 08:19:14 ✞ ሰላም ለኢትዮጵያ

ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሀገራችን/2/
ይላክልን/3/ ቸሩ አምላካችን

ኢትዮጵያ ታበፅ ነበር ያዝማሬ
አቅጣጫውን ስቷል ስርዓትዋ ዛሬ
አቅናት ፈጣሪዋ ስራት እንደገና
የሰቀለችውን ታውርድ ያን በገና

አዝ______________

ያቺ የዳቦ ምድር ያዘለች አዝመራ
እንዴት ስለችግር ስለእርሀብ ታውራ
ተመልከታት አምላክ ምህረትህ ይድረሳት
ጩኸቷ ተሰምቶ በረከት አርሳት

አዝ______________

የገዛ ዋችንን በዋጋ ገዝተናል
በራሳችን ምድር ባእዳን ሆነናል
ቱፊት ታሪካችን ባህሉም ተረሳ
የሰዶምን ሀጢያት ምድራችን ተላብሳ

አዝ______________

እነሆ እግሮቻችን ለስደት ተነሱ
የናቡቴን ርስቶች በደም ተወረሱ
አንተ ብቻ አብሰው ያይናችንን ለቅሶ
ወድቀናል ከደጅህ ሀዘናችን በዝቶ

አዝ______________

ያቺ የዳቦ ምድር ያዘለች አዝመራ
እንዴት ስለችግር ስለእርሀብ ታውራ
አምላክ ተመልከታት ምህረትህ ይድረሳት
ጩኸቷ ተሰምቶ በረከት አርሳት


መዝሙር
ዘማሪ በርሱፍቃድ እንዳርጋቸው

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
7.3K views••●◉ Estifanos ◉●••, 05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 21:20:48 ከመ ፀበል ዘነፋስ ዘረውም ደብረ ይድራስ

ትርጉሙም

እንደ ነፋስ በይድራስ ተራራ በተኑት
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን


እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዝርወተ አፅም ለስባራ አፅሙ ዓመታዊ በዓል በስላም አደረሳችሁ አደረስን

ጥር ፲፰(18) ዝርወተ አፅሙ ለጊዮርጊስ ወያዕቆብ ዘንጽቢን ዘአፃዕደው ሥዕርቶየን ለአንስት ወተዝካሮ ለማርያ ወማርታ ወቅዱስ ባኮስ ኢትዮጵያዊ

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

እስመ ኀልቀ ከመ ጢስ መዋዕልየ
ወነቅጻ ከመ ሣዕር አዕፅምትየ
ተቀሠፍኩ ወየብስ ከመ ሣዕር

✤ ትርጉም ✤

ዘመኔን እንደ ጢስ አልቃለችና
አጥንቶቼም እንደ መቃጠያ ተቃጥለዋልና
ተቀሠፍሁ ልቤም እንደ ሣር ደረቀ

መዝ ፻፩-፫
101 3

✤ ወንጌል ✤

ዮሐ ም ፲፩ ቁ ፲፱-፴፫
11 19 33

የቅዳሴ ምንባባት

ሮሜ ም ፰ ቁ ፴፭-ፍ.ም
፩ ጴጥ ም ፫ ቁ ፩-፯
ግብ.ሐዋ ም ፲፯ ቁ ፴-ፍ.ም

❖ ምስባክ ❖

ወእምኵሉ ያድኀኖሙ እግዚአብሔር
እግዚአብሔር የዐቅብ ኵሉ አዕፅምቲሆሙ
ወኢይትቀጠቀጥ አሐዱ እምውስቴቶሙ

ትርጉም

እግዚአብሄርም ከሁሉ ያድናቸዋል
እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል
ከእርሱም አንድ አይሰበርም

መዝ ፴፫-፲፱
33 19

❖ ወንጌል ❖

ማቴ ም ፭ ቁ ፵፪-ፍ.ም
5 42 ፍፃሜው

❖ ቅዳሴ

ዘወልደ ነጎድጓድ

" በጦር ስለ ተገደሉና ስለተማረኩም ሰዎች ሁሉ፤ለድሆችና ስለ ችጋረኞችም ስለ ባልቴቶች ስለ ድሀ አደጎች "
ቅዳሴ ዮሐንስ ዘወልደ ነጎድጓድ
ም ፩ ቁ ፷፭
1 65

በዓሉን በዓለ በረከት በዓለ ፀጋ ያድርግልን ከዘመነ አስተርእዮ በረከት ይክፈልን የቸሩ አምላካችን ዘላለም ሥላሴ በቸርነቱ ይማረን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ እግዝእትነ በምልጃዋ አትለየን ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን ታሳደርብን በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ይጠብቅን ቤተክርስቲያን ቅድስት በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን ከሊቀ ሰማዕታት ከቅዱስ ጊዮርጊስ በረከቱ ይደርብን በቅዱሳኑ ፀሎት ይማረን ከቅዱሳት ደናግል ማርያ ወማርታ ለቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢ ከቅዱስ ባኮስ ኢትዮጵያዊ በረከታቸው ይደርብን በዓልን ተከትሎ ከሚመጣ መቅሠፍት አምላክ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይሰውረን ይጠብቅን ፀሎት ሙሴ ዕጣነ አሮን ዝማሬ ዳዊት ቅዳሴ መላዕክት የተቀበለ አምላክ የኛንም ፆም ፀሎት ምስጋና ስግደት በብሩህ ገጽ ይቀበልልን ለአበው ቅዱሳነ ሁሉ የተለመነች እመ አምላክ እግዝእትነ ማርያም ለኛም በምህረት ትለመነን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን ለሃገራችን ስላም ለህዝባችን ለአንድነት ይስጥልን አቤቱ ባሪያህ የሚሆን ሳዕለ ሥላሴን አስበው ለሁላችንም ፍቅር ይስጥን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
8.7K views••●◉ Estifanos ◉●••, 18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ