Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ዳዊት

የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የሰርጥ አድራሻ: @mezmurochh
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.22K
የሰርጥ መግለጫ

🔔🔔🔔 መዝሙረ-ዳዊት 🔔🔔🔔

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉ
☞ @mezmurochh
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
☞ @Mezmuredawit_bot ላይ ያገኙናል

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 25

2023-02-04 18:14:54 ✞ ኢትዮጵያ እጅሽን ዘርጊ

ኢትዮጵያ እጅሽን ዘርጊ
ወደ አምላክ ወደ አዶናይ
ሕዝብሽን ከሞት የሚያድን
ይውጣልሽ የምህረት ፀሐይ

ሕጻናት ወላጆች አተው በሜዳ ሲበታተኑ
ልጆችሽ ወጣቶች አልቀው የአፈር ሲሳይ ሲሆኑ
የሞት መላክ ተልኮብሽ መሬትሽ አጣ ጸጥታ
ቁጣውን እንዲመልሰው ለምኚ ለሰማይ ጌታ

አዝ____________

ታማሚው እያጣጣረ ጤነኛው ቆሞ ሲፈራ
አምላክሽ ይቅር ይበልሽ ይለፍሽ ይህን መከራ
አበውን ይዘሽ ተነሺ ጸሎትሽን ቆመሽ አድርሽ
ያብርደው እሳት ንዳዱን በምልጃሽ በልመናሽ

አዝ___________

ልጃችሽ ቅጣት ገብቷቸው እንዲያዩ ወደ አምላካቸው
መከራው ትምህርት ሆኖአቸው ይመለስ ታካች ልባቸው
የበደልነውን ታግሶ ቁጣውን እርሱ መልሶ
ይማረን ይቅር ይበለን ጽኑ ምህረቱን አስታውሶ

አዝ__________

አሕዛብ ተነጋገሩ አምላክሽ እረሳሽ ብለው
ልጆችሽ ሞት ሲፈጃቸው እያዩ እጅግ ተገርመው
ጉልበትሽ እንዳይሰበር ጉልበትሽ እሱ ነውና
ደዌ ቸነፈሩን ያርቅ አቅርቢ ጽኑ ልመና

አዝ___________

በስደት ከቅፍሽ ወተው በሜዳ ወድቀው ለቀሩት
አበዉን ይዘሽ ፀልይ መሪር ነው ከፍቷል ሀዘኑ
ደራሽም አይዞህ ባይ ላጡ መድረሻም ቦታም የላቸው
እግዚኦ እግዚኦ እንበል ይታወስ ንፁህ ልባቸው


ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ

፤ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
መዝ 67(68)÷31

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
1.6K views••●◉ Estifanos ◉●••, 15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 16:10:44 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

መዝሙረ ዳዊት

✤ ሊቀ-መዘምራን ይልማ ኃይሉ ✤

✣ ሰማዕታት መስተጋድላን ✣

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
@mezmurochh
@mezmurochh
@mezmurochh
|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
2.1K views••●◉ Estifanos ◉●••, 13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 16:10:44 ✞ሰማዕታት መስተጋድላን

ሰዓሉ ለነ ሰዕማታት መስተጋድላን/2/
ከዋክብት ለቤተ-ክርስቲያን /4/

በምድር ሊቪያ ተጣራ እየሱስ
በተዋህዶ ልጆች ስሙ እንዲ ቀደስ
እየሱስ አምላክ ነው እያሉ በፅናት
መንግስተ ሰማይን ህፃናት ተሻሟት /2/
ከዋክብት ለቤተክርስቲያን /4/

በመከራ ጊዜ ሚዛን ላይ ወታቹ
በክርስቶስ ፀጋ እንደ እንቁ አበራቹ
እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰይፍን ሳትፈሩ
እግዚአብሔር ይመስገን በቃቹ ለክብሩ /2/
ሰዓሉ ለነ ሰዕማታት መስተጋድላን/2/

እዮ ሲያንገላቱ ሲያዳፉት ጨክነው
ምንም አልቀመሰም ወንድሜ ፆሙን ነው
ግን እንደ ሰርገኛ በደስታ ይጓዛል
በሰይፍ ፊት ቆሞ ለወንጌሉ ታምንዋል
መከራውን ንቆ ለወንጌሉ ታምንዋል
ሰዓሉ ለነ ሰዕማታት መስተጋድላን/4/

ግርፋቱን ይስሙ መታረዱን ደግሞ
ከክርስቶስ ፍቅር እኛ የሚለየን
ያመለክ ነው አምላክ የእውነት ስለሆነ
ለክብር ተፋጠኑ ልባቸው ጨከነ /2/
ከዋክብት ለቤተ-ክርስቲያን/4/


የዋልዮሽ ታስረው እንደ በግ ሲነዱ
ይመስሉ ነበረ ለሰርግ የሚሄዱ
በጉድጓድ ተከተው ለቀናት ቢራብ
በውሃ ጥም ዝለው አልተለዋውሱም/2
ሰዓሉ ለነ ሰማዕታት መስተጋድላን/2/
ከዋክብት ለቤተ-ክርስቲያን/4/


ገዳይወች ድል ሆኑ ሙታን ሆኑ እነሱ
የተዋህዶ ልጆች በድል ገሰገሱ
በደማቸው ፀዳል አለምን ቀየሩ
የኢትዮጵያ ከዋክብት በሊቪያ አበሩ
የኢትዮጵያ ከዋክብት በዓለም አበሩ
ከዋክብት ለቤተ-ክርስትያን/2/

ዘማሪ
ሊቀ-መዘምራን ይልማ ሃይሉ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
2.2K views••●◉ Estifanos ◉●••, 13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 22:30:53
1.6K views••●◉ Estifanos ◉●••, 19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 22:29:22 ጾመ ሰብአ ነነዌ

✞ ጾመ ነነዌ ከአዋጅ አጽዋማት አንዱ ሲሆን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ቀን ደግሞ ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር 17 ቀን ድረስ ነው፡፡ ሲወጣ ወይም ወደፊት ሲገፉ ደግሞ እስከ የካቲት 21 ድረስ ነው፡፡ በእነዚህ 35 ቀናት/ዕለታት/ ስትመላለስ ትኖራለች፡፡ ከተጠቀሱት ዕለታት አይወርድም አይወጣም ማለት ነው፡፡

✞የሦስት ቀኑን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች ሲሆኑ ከተማዋ በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ መሥራቿም ናሞሩድ ነው፡፡ ዘፍ.10፥11-12 ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የሆነ ከተማ እጅግ ሰፊና ያማረ ፤ የከተማው ቅጥር ርዝመት አሥራ ሁለት ኪሎ ሜትር ነበር፡፡ ሰናክሬም ብዙ ሕንፃዎችንም ሠርቶበት ነበር፡፡ /ዮናስ. 4፥11/

✞የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ በኃጢአታቸው ምክንያት ሊጠፉ ሲሉ ቸርነትና ምህረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር ነቢዩ ዮናስ መክሮ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ወደ ነነዌ ሕዝብ ሂድ አለው፡፡ ሉቃ.11፥30 ዮናስ የስሙ ትርጉም “ርግብ” ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ትንቢትን ተናግሯል፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል ፡፡ 2ነገ14፥25፣ ት.ዮና1፥1

✞እግዚአብሔርም “ሄደህ በነነዌ ላይ ስበክ” ባለው ጊዜ “አልሄድም” አለ፡፡ “አንተ መሀሪ ነህ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ስትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ፡፡” ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔር ግን ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧበማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩት ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባህሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ “በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባህር ጣሉኝ” ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነሱም “የሰው ደም በእጃችን እንይሆንብን አይሆንም” አሉት፡፡ ዕጣም ቢጣጣሉ ዮናስ ላይ ወጣ፡፡ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያው የእግዚአብሔር የማዳን መልእክት ዮናስ እንዲያደርስ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ነነዌ አደረሰው፡፡ ዮናስም ከእግዚአብሔር መኮብለል አለመቻሉን ሲረዳና ነነዌ መሬት ላይ መድረሱ ሲነገረው ለነነዌ ሰዎች “ንስሐ ግቡ” ብሎ መስበክ ጀመረ ዮናስ 1እና2 ፡፡ የነነዌ ሰዎች ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ማራቸው /ዮና.3/

✞ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስህተት መሆኑን እግዚአብሔር ቅልን ምሳሌ በማድረግ አስረዳው፡፡ /ዮና.4/ ነቢየ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል፡፡ በስንክሳር ታኅሣሥ 5 እንደሚነግረን ፤ወበልዓ አሐደ ኀምለ ይላል ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር አጥፍቶአል፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የስራጵታ መበለት ሕፃን ዮናስ እንደሆነ /1ነገሥ.17፥19/ ሲያስረዳን ፤ክርስቶስ የዮናስን ከዓሣ ሆድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎታል፡፡ /ማቴ.12፥19-42/ ሉቃ.11፥30-32/፡፡

✞ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፡፡ ይሄውም አስቴር አስቀድማ ሦስት ቀን ጾማ ጸልያ በእሥራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች ኢሳ.4፥15-16፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ልጇ ሕፃኑ ኢየሱስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ እንዳገኘችው ሁሉ ሉቃ.2፥46 ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መሆኑን ገልጿል ሉቃ.13፥32፡፡

✞የነነዌ ሰዎች የተነሳህየን ምሳሌ ናቸው ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺህ በላይ ሕዝቦችና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለሆኑ ያሳዝኑኛል ያለው፡፡

✞ዛሬ ዓለማችን በኃጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለበት ወቅት እኛም ብንመለስ እና ንስሐ በንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለሆነ “ወደኔ ተመለሱ እኔም ይቅር እላችኋለሁ ”ብሎ አስተምሯል፡፡ ቀደምት አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ለምሳሌ ጾመ ነነዌ የሚከተሉትን ምሳለዎች እናገኝባታለን ታሪኩን በማስታወስ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሀሪነት የምናስታውስበት ነው፡፡ ይኸውም ፍጥረቶቹ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርጋል፡፡ ዮናስ ፈቃደኛ ባይሆን እንኳ በተለየ ጥበቡ እንዲሄድ አድርጎታል፡፡ ሌላ ነቢይ አጥቶም አይደለም እሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለፈለገ እንጂ፡፡

✞በዮናስ አማካይነት የተደረጉ ተአምራትን መገንዘብና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመሆኑን ተገንዝበን ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሃይማኖት አባቶች አና ለወላጆች መታዘዝን እንማርበታለን፡፡ እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን ጸልየን ከኃጢአታችን እንድንነፃ ነው፡፡ ብንጾም እራሳችን፣ ሃገራችንን፣ እጽዋቱንና እንስሳቱም ሳይቀር በኛ በደል ምክንያት በድርቅ በቸነፈር እንዳይጠፋ እግዚአብሔር ይቅር ስለሚል ነው፡፡

✞ እግዚአብሔር የበረከት፣ ሀጥያታችን የሚሰረይበት፣ ፀሎታችን ቅድመ እግዚአብሔር የሚደርስበት ጾም ያድርግልን። ለሁላችሁም እንኳን አደረሳችው።

ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

ለመቀላቀል
      ┏━━° •❈• ° ━━┓
      @mezmurochh
@mezmurochh
@mezmurochh
      ┗━━° •❈• ° ━━┛

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን
1.7K views••●◉ Estifanos ◉●••, 19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 20:31:05
✞ #አንድ_ሲኖዶስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
#አንድ_መንበር
መንበረ ተክለሃይማኖት
#አንድ_ፓትሪያርክ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
2.9K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 00:21:26
ምህረትን ከአምላክ ለምንልን ቅዱስ መርቆሬውስ ሰማዕት ለባስልዮስ ወጎርጎርዮስ አንደደረስክ ከፊት ለምመጣው ነገር በጸሊም ፈረስክ ደርሰክ ሀገሬን ጠብቃት።



ባስልዮስ ጎርጎሪወስ ሰምሯል ልመናቸው
ስዕሉ ዘለለ ታምራት አያችሁ
እናንተን የረዳ መጥቶ በፈረስ
ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆሬዎስ


╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
3.2K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  21:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 00:20:59 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

መዝሙረ ዳዊት

✧ የኢቲሳ-አንበሳ ✦

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
@mezmurochh
@mezmurochh
@mezmurochh
|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
2.9K views••●◉ Estifanos ◉●••, 21:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 00:20:59 ✞ የኢቲሳ አንበሳ

የኢቲሳ አንበሳ ተክልዬ ተነሳ
ወገንክን ታደገው ከኃጥያት አበሳ
ተኩላው ለምድ ለብሶ በእርግጥ መጥቷአልና
ጴጥሮስ ሆይ ዝም አትበል እንደ ጥንቱ ቅና
ዮሐንስ ዝም አትበል እንደ ጥንቱ ቅና
ሉቃስ ዝም አትበል እንደ ጥንቱ ቅና
ማርቆስ ዝም አትበል እንደ ጥንቱ ቅና
ጳውሎስ ዝም አትበል እንደ ጥንቱ ቅና

አዝ______________

የዓለም ምናምንቴ የተባልከው ቅዱስ
የዋሁ መነኩሴ አባ ሕርያቆስ
ቅዳሴ ማርያምን ናና ዛሬም ቀድስ
በዕጣኑ መዐዛ ድውያንን ፈውስ(2)

አዝ______________

የወንጌል አንበሣ ጎርጎርዮስ ፍጠን
ምሶሶው ሳይወድቅ መንጋው ሳይበተን
መብረቁ አትናቴዎስ ሞገዱን ገስፀው
አፈ ጉባያችን በመስቀልህ ዳኘው(2)

አዝ______________

መርከቧን የሚያውክ ነፋስ መጥቷልና
አምላካችን ፈጥነህ አድነን ቶሎና
ጴጥሮስ ሆይ ቀስቅሰው ልንጠፋነው ብለህ
ሞገዱ እያየለ ዝም እንዳይል ጌታ(2)

አዝ______________

ከሣቴ ብርሃን ሰላማ ቶሎና
ኖላዊ እረኛ ያስፈልጋልና
ሥጋውን የጎዳ ነፍሱን የጠቀመ
ነቅ ጉድፍ የሌለው ግብሩ የታረመ(2)

መዝሙር
ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
2.8K views••●◉ Estifanos ◉●••, 21:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 20:48:44
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
4.4K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ