Get Mystery Box with random crypto!

ልብወለድ Ethio_Fiction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_fiction
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.31K
የሰርጥ መግለጫ

#ለሃሳብ_አስተያየት

Admins:- @sam_lizu

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-25 15:53:13
የባህል ህክምና እና ፈውስ
                0931088319
          
✿መምጣት የማትችሉ በእ/ር ስም መዳኒቱን እናደርስልዎታለን
       ስ.ቁ:- 0931088319 ይደዉሉ
የምንሰጥባቸዉ የአገልግሎት አይነቶች
   *ሞአንበሳ ዘይምነ ገዳ ቀለበት
   *መዳብ
   *በተለያዩ የእፅዋት ቅመማዎች /ተቀፅላ/
   *በዉቅራት /በንቅሳት/
   *በእንስሳት ቆዳና ክታበ ስጋ
   *በጥፈት
   *በተለያዩ ሚስጢር በሆኑ ነገሮች
የምንሰጣቸዉ አገልግሎቶች
      1,ለመፍትሄ ስራይ
      2,ለቡዳ
      3,ለቁራኛ
      4,ለመጠብቅ(ከጠላት፡ከሚላክ ሟርት
      5,ለግርማ ሞገስ
      6,ለጥይት(መሳሪያ የማያስነካ)
      7,ለብትር(ዱላ የማያስነካ)
      8,ለጋኔን
      9,ለማንኛዉም አይነት የሰዉነት ክፍል በሽታ
   11,ለእቁብ
   13,ለመስተሳልም
   14,ትቶን የሄደን ሰዉ ለማስመለስ(ለፍቅረኛ)
   15,ለስንፈተ ወሲብ
   16,ዘኢያወርድ(ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ጊዜ የዘር ፍሬ ቶሎ እንዳይፈስ
   17,ለመፍትሄ ሀብት(በማንኛዉም ስራ ገንዘብ፡ሀብት እንዲኖረን
   18,ለገበያ
   19,ለወር አበባ ችግር
   20,ለአይነ ጥላ(የፍርሃት መንፈስ ማስለቀቂያ)
   21,ለመስተሀድር(ንብረት ቢጠፋን በእጃችን ዉስጥ ማግኘት የሚያስችል
   23,ለሙግት
   24,ለመፍዝዝ (ጠላት ሊጎዳን ሲሞክር ሰዉነቱን አሳስሮ የሚያስቀምጥ፡የሚያፈዝ
    25,ህገ ጠብቅ (የትዳር አጋራችን ወደ ሌላ ሰዉእዳይሄድ፡ እንዳያመነዝር)
    26,ለመሠዉር (ችግር ሲደርስብን ከዚያ ችግር በማይታወቅ ሁኔታ ለመዉጣት)
    27,ለቀለም (ለትምህርት)
ስልክ
  0931088319
ቴሌግራም @merigeta2112
619 viewsሀለወ እግዚአብሔር, 12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-25 13:22:46
መርጌታ ፀጋ የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል።
በሰለሞን በኩል ከእግዚአብሔር የተሰጠንን ጥበብ ተጠቅመን ለመልካም ነገር በማዋል  ላይ እንገኛለን።
ከስራዎቼ በጥቂቱ ለመጥቀስ ያክል

1, ለኪንታሮት
2, ለጉበት
3, ለጨንጓራ
4,  ለአስም
5, ለካንሰር
6, ለሌሊት ወፍ በሽታ
7, ለሚጥል በሽታ ላለበት
8, በመተት ለተያዘ
9, ሀብት አልያዝ ላለው
እና ሌሎችም መፍትሔ አለን
ይምጡ ይጎብኙን ይፈወሱ።
ማሳሰቢያ፡ ሁሉም መድሐኒቶች ሙሉ በሙሉ ከእፅዋት እና ከመጻህፍት ትዕዛዝ ብቻ ይሰራሉ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የላቸውም።
ለጥያቄዎ ስልክ 0931088319
ቴሌግራም @merigeta2112
750 viewsሳ² lizu, 10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 22:34:42 አንቀጽ 6 እና 7 ተደጋግሞ በመፃፉ ይቅርታ አድርጉልኝ
2.2K viewsሳ² lizu, 19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 22:25:59 ልብወለድ Ethio_Fiction pinned a photo
19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 22:12:29 #የቀጠለ
በዐይን ቋንቋ ተነጋግሮ ትኩረት ለመሳብ የሸበላዉ ዐይኖች ወደ እኔ የሚወረወሩበትን አጋጣሚ በቋፍ እየጠበቅሁ ነዉ፡፡ በተቃራኒዉ፣ ሸበላዉ ዐይኑን ሄለን ላይ ተክሏል፡፡ ቀልቡ ሳይወዳት አልቀረም፡፡ እዚህ ቡና ቤት ከምንሠራዉ ጋለሞቶች ብዙ ደንበኛ ያላት ሄለን ናት፡፡ ሄለን ከእኔ የባሰች ጋግርታም ብትሆንም በሰዉ የመወደድ ፀጋን የታደለች የጠይም ቆንጆ ናት፡፡ ቀዝቃዛነቷ ስትፈጠር ጀምሮ የተጣባት ይሁን ዘግይቶ የተከሰተ በዉል አይታወቅም፡፡ ዉበቷ ነዉ ድብርቷን ሸፍኖ ዓለም መኖሯን እንዳይዘነጋ የረዳት፡፡ ብዙ ጊዜ እኛ ሥራ አጥተን ጦማችንን ስናድር እሷ ወንድ አማርጣ ትወጣለች፡፡ ሄለን ሐሜት ልብሷ ነዉ፤ ቡና ቤቱ ዉስጥ የእሷ ስም ሳይብጠለጠል ቀርቶ አያዉቅም፡፡
ሸበላዉ ዐይኖቹን ከሄለን ላይ ነቅሎ ወደ እኔ ሲወረዉር ዐይን ለዐይን ተጋጨን፣ ተሽኮርምሜ ዐይኖቼን ሰበርኩ፡፡ እንደገና ባልኮኒዉ ዙሪያ የጦፈዉን ሁካታ የምከታተል መስዬ በስላቺ ስሰልለዉ አሁንም ዐይኖቹን እኔ ላይ እንደሰፋ ነዉ፡፡ ሸበላዉ ሴት አዉል ይመስላል፡፡

የባልኮኒዉን ትዕይንት መታዘብ ትቼ ወደ ሸበላዉ ሳማትር አዜብ ፊቱ ተገትራለች፣ እነዛን አንደ ኮርማ በሬ ቀንድ ከርቀት የሚታዩትን ጡቶቿን ወድራ፡፡ ያለ ወትሮዋ ደርሳ አስተናጋጅ መሆኗ ደንቆኛል፡፡          ጎኔ ካለዉ ጠረጴዛ (በግራዬ በኩል) ጥንዶች ተቀምጠዋል፡፡ ወንድየዉ ፀጉሩን ድሬድ ሎክ ተሠርቷል፡፡ ሙሉ ቀልቡን አብራዉ ካለችዉ ሴት ጋር ያደረገ ቢመስልም በአይኑ ቂጥ እኔን ሰርቆ ማየቱን አላቆመም፡፡                        
ሸበላዉን እየሰረቅሁ መመልከቴን ቀጥያለሁ፡፡ ቢራ የተሞላ ብርጭቆዉን አንስቶ ወገቡ ድረስ ተጎነጨና ሲጋራዉን ምጎ ጭሱን አየር ላይ ተፍቶ ቡሹን ሲጋራ መተርኮሻዉ ላይ ደፈጠጠ፡፡ አዜብ ቢራ ካቀረበችለት በኋላ እንኳ ከሦስቴ በላይ ወደ እሱ ተመላለሰች፡፡ ቀልቡ ሳይጠላት አልቀረም፤ እንጂማ ወንበር እንድትጋራዉ ጠይቆ ቢራ ይጋብዛት ነበር፡፡ ከስፒከሩ የፍራንክ ሴናትራ መረዋ ድምፅ መንቆርቆሩን ቀጥሏል፡፡
ሸበላዉ ዐይኖቹን ዳንስ ወለሉ ላይ ተክሏል፡፡ የእነ ማሕሌት ዳንስ የመሰጠዉ ይመስላል፡፡ ዐይኖቹን ከዳንስ ወለሉ ላይ ትዕይንት ላይ ሳይነቅል ሁለተኛ ሲጋራዉን አቀጣጠለ፡፡ ጎኔ የተቀመጡት ጥንዶች የጦፈ ወግ አለሁበት ድረስ ጎልቶ ይሰማል፣ ጆሮዬን ጥዬ የሚሰልቁትን ወግ ማዳመጥ ጀመርኩ፡  

“ኧረ እባክህ! በጣም ይገርማል! ምን አፋታቸዉ?” ሴቷ፡፡
“ምን እባክሽ፣ እሱ መች ይረባል፡፡ ያቺን የመሰለች ልጅ …” ወንዱ፡፡ ከፊል የፊቱ ገፅ ብቻ ነዉ የሚታየኝ፡፡ ትከሻ ሰፊ ነዉ፡፡ 
 “እንዴት አወቅክ አንተ?”  
 “የድሮ ወዳጄ አልነበር እንዴ?”
“ዉሻ ነዉ ለካ አንተ?”
“እየነገርኩሽ! እሱ አመሉ ነዉ፣ በአንድ አይረጋም፡፡ ዛሬ ከአንዷ ጋር አይተሽዉ ከሆነ ነገ ከሌላዋ ጋር ታገኝዋለሽ፡፡ እሚገርምሽ እኮ ከበፊቷ አንድ ወልዷል፡፡”
“ይገርማል! ግን እኮ አንደዛ አይነት ሰዉ አይመስልም፡፡”  
“ቢራ ይጨመራ? ጠጪ እንጂ!” አጨብጭቦ አስተናጋጇን ጠራ፡፡
“እንዴ ይብቃን! ልታሰክረኝ ነዉ እንዴ አላማህ? በዚያ ላይ መሽቷል፡፡”
“እንጫወት እንጂ፣ ገና እኮ ነዉ?”
“ምን ማለትህ ነዉ? ባለትዳር መሆኔን ረሳኸዉ? አንተን ብዬ እንጂ …?”
“ተይ እንዲህ አትበይ፡፡ ምንም ቢሆን የመጀመሪያሽ እኮ እኔ ነኝ፡፡”
“እኔስ አንተን ብዬ መስሎኝ ኃጢያት ዉስጥ የገባሁት፡፡ ተረዳኝ እንጂ!”      
ፊት ለፊቴ የተቀመጠዉ ሪዛም ሸበላ ዐይኖቹን ከነ ማሕሌት ላይ አሽሽቶ ወደ እኔ ሲዞር ለሁለተኛ ጊዜ ዐይን ለዐይን ተጋጨን፣ ቀድሜ ዐይኖቼን ሰበርኩ፡፡ ከጎኔ ያሉት ጥንዶች የሚቀዱት ተባራሪ ወሬ አሁንም በጆሮዬ መስረጉን ቀጥሏል፡፡
“ማመን ይከብዳል! እዉነትህን ነዉ? እሷስ እንዴት እሽ አለች?” ሴቷ፡፡
“አንቺ ደግሞ፣ ሰዉየዉ እኮ ዮናስ ነዉ፡፡ ምን ነካሽ?” ወንዱ፡፡
“ኧረ እባክህ? አሳምኗት ነዉ አየህ?”
“ምላሱ ጤፍ ይቆላል ስልሽ!”

“ኧረ እባክህ! በጣም ይገርማል! ምን አፋታቸዉ?” ሴቷ፡፡
“ምን እባክሽ፣ እሱ መች ይረባል፡፡ ያቺን የመሰለች ልጅ …” ወንዱ፡፡ ከፊል የፊቱ ገፅ ብቻ ነዉ የሚታየኝ፡፡ ትከሻ ሰፊ ነዉ፡፡ 
 “እንዴት አወቅክ አንተ?”  
 “የድሮ ወዳጄ አልነበር እንዴ?”
“ዉሻ ነዉ ለካ አንተ?”
“እየነገርኩሽ! እሱ አመሉ ነዉ፣ በአንድ አይረጋም፡፡ ዛሬ ከአንዷ ጋር አይተሽዉ ከሆነ ነገ ከሌላዋ ጋር ታገኝዋለሽ፡፡ እሚገርምሽ እኮ ከበፊቷ አንድ ወልዷል፡፡”
“ይገርማል! ግን እኮ አንደዛ አይነት ሰዉ አይመስልም፡፡”  
“ቢራ ይጨመራ? ጠጪ እንጂ!” አጨብጭቦ አስተናጋጇን ጠራ፡፡
“እንዴ ይብቃን! ልታሰክረኝ ነዉ እንዴ አላማህ? በዚያ ላይ መሽቷል፡፡”
“እንጫወት እንጂ፣ ገና እኮ ነዉ?”
“ምን ማለትህ ነዉ? ባለትዳር መሆኔን ረሳኸዉ? አንተን ብዬ እንጂ …?”
“ተይ እንዲህ አትበይ፡፡ ምንም ቢሆን የመጀመሪያሽ እኮ እኔ ነኝ፡፡”
“እኔስ አንተን ብዬ መስሎኝ ኃጢያት ዉስጥ የገባሁት፡፡ ተረዳኝ እንጂ!”      

ፊት ለፊቴ የተቀመጠዉ ሪዛም ሸበላ ዐይኖቹን ከነ ማሕሌት ላይ አሽሽቶ ወደ እኔ ሲዞር ለሁለተኛ ጊዜ ዐይን ለዐይን ተጋጨን፣ ቀድሜ ዐይኖቼን ሰበርኩ፡፡ ከጎኔ ያሉት ጥንዶች የሚቀዱት ተባራሪ ወሬ አሁንም በጆሮዬ መስረጉን ቀጥሏል፡፡
“ማመን ይከብዳል! እዉነትህን ነዉ? እሷስ እንዴት እሽ አለች?” ሴቷ፡፡
“አንቺ ደግሞ፣ ሰዉየዉ እኮ ዮናስ ነዉ፡፡ ምን ነካሽ?” ወንዱ፡፡
“ኧረ እባክህ? አሳምኗት ነዉ አየህ?”
“ምላሱ ጤፍ ይቆላል ስልሽ!”
ማሕሌት እና አበራ አዲስ የተከፈተዉን ዘፈን ምት ተከትለዉ ተቃቅፈዉ መደነሱን ቀጥለዋል፡፡ የማሕሌት ቁመት ከአበራ ስላጠረ ጎበጥ ብሎ ሊያቅፋት ተገዷል፡፡

#Inbox @Faraw_sam

#share @ethio_fiction
2.0K viewsፋራው, 19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 22:11:22
#አጭር_ልብወለድ

#"እሽሩሩ_መዉደድ---_እሽሩሩ ፍቅር"

#ክፍል.....2

ማሕሌት እና ባልኮኒዉ ጋ ተቀምጦ ቢራ ሲጠጣ የነበረዉ ቋሚ ደንበኛዋ አበራ ዳንስ ወለሉ ላይ ወጥተዉ በባህር ማዶ ዘፈን ተቃቅፈዉ መደነስ  ጀምረዋል፡፡ ማሕሌት ያን ታላቅ ዳሌዋን እያዉረገረገች፡፡ የሁሉም ሰዉ ዐይን እነሱ ላይ ነዉ፡፡
    
ከዉጪ ሪዛሙ ሸበላ ገብቶ ፊት ለፊቴ ከሚገኘዉ ቦታ ላይ ተቀመጠ፡፡ ረጅም ነዉ፣ መልከ መልካም፡፡ የቀይ ፊቱን ሰፊ ወሰን የሸፈነዉ ሪዙ መጀመሪያ ቀን መጥቶ ካየሁት ጥቂት በመጎፈሩ ሳይሆን አይቀርም ግርማዉን አግንኖታል፡፡ የተቀመጠዉ ከባልኮኒዉ ጥቂት ራቅ ብሎ ካለዉ ቦታ ነዉ፡፡ የሆነ ገፅታዉ ከቀድሞ ፍቅረኛዬ ጋር ይመሳሰላል፣ አፍንጫዉ፣ የትከሻዉ ስፋት፣ የከናፍሩ ስስነት ምናምን፡፡
1.7K viewsፋራው, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 21:51:52 #የቀጠለ በእዛ ቀን የለበስኩት ጥቁር ነበር፡፡ ሸበላዉ ምናልባት ዛሬ ይመጣ ይሆናል፡፡ ጥቂት ተስተናጋጆች ናቸዉ ቡና ቤቱ ውስጥ ያሉት፡፡ አዜብ (ቅፅል ስሟ ሩት፡፡ ሁላችንም የሥራ ቦታ ቅፅል ስም አለን) ከእኔ ተቃራኒ ካለዉ ወንበር ላይ ተቀምጣ ቦርሳ ዉስጥ በምትያዝ ትንሽዬ የፊት መስታወት ላይ አተኩራ ፊቷን በማስዋብ ተግባር ላይ ተጠምዳለች፡፡ የምሸሸዉን ትዝታ የሚጎትት የኩኩ ሰብስቤ ዘፈን ግድግዳው ላይ…
2.3K viewsፋራው, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 20:33:29 #የቀጠለ
በእዛ ቀን የለበስኩት ጥቁር ነበር፡፡ ሸበላዉ ምናልባት ዛሬ ይመጣ ይሆናል፡፡
ጥቂት ተስተናጋጆች ናቸዉ ቡና ቤቱ ውስጥ ያሉት፡፡ አዜብ (ቅፅል ስሟ ሩት፡፡ ሁላችንም የሥራ ቦታ ቅፅል ስም አለን) ከእኔ ተቃራኒ ካለዉ ወንበር ላይ ተቀምጣ ቦርሳ ዉስጥ በምትያዝ ትንሽዬ የፊት መስታወት ላይ አተኩራ ፊቷን በማስዋብ ተግባር ላይ ተጠምዳለች፡፡ የምሸሸዉን ትዝታ የሚጎትት የኩኩ ሰብስቤ ዘፈን ግድግዳው ላይ በተሰቀሉት ስፒከሮች በኩል ጐላ ብሎ ይንቆረቆራል፡
 የሰማዩ ዝናብ ከዳመናዉ መጣ
 ከዐይኔ የሚመነጨዉ ኧረ ከየት መጣ?
ተመራምሬያለሁ እኔ ግን በሐሳቤ
ዕንባዬ የመጣዉ ነዉ እኮ ከልቤ
ክረምት አልፎ በጋ ሁሌ አይቀርም ሲባል
የእኔ ዕንባ አላባራም ገና ነዉ ይዘንባል
ከአንጀቴ ከሆነ ዕንባዬ የሚፈሰዉ
ምክንያቱ አንተ ነህ አላዉቅም ሌላ ሰዉ
እኔ እወድሃለሁ ፍቅሬ አስብሃለሁ
ይወቴ በሙሉ ያንተ ነዉ ብያለሁ።

ሲጋራዬን እያቦነንኩ ዘፈኑን ተከትዬ በትዝታ እየተብሰከሰኩ ሳለ ከእኔ እኩል እዚህ ቡና ቤት ግልሙትና የጀመረችዉ መክሊት (ቅፅል ስሟ ሮዛ) በቡና ቤቱ የጀርባ በር በኩል ዘልቃ እየተጣደፈች መጥታ ጉንጬን ሳመችና ባልኮኒዉ አጠገብ ተሰብስበዉ ለሚያወጉት ሴቶች ለስንብት እጇን አዉለብልባ ቤቱን ለቃ ተሰወረች፡፡ አጠገቤ መጥታ ሳለ ነስንሳዉ የሄደችዉ ስርንን የሚበጥሰዉ ርካሽ ሽቶዋ ጠረን ገና በአየር ተጠርጎ ስላልተወሰደ ምቾቴን አጓድሎታል፡፡ መክሊት እዚህ ቡና ቤት ሥራ የጀመረችዉ ከእኔ ቀድማ ነዉ፡፡ በቀለም ትምህርት እስከ ኮሌጅ ገፍታለች እየተባለ ስለሚወራ ‘ምሁሯ’ የሚል የአግቦ ስም ሰጥተናታል፡፡ ከእሷ በቀር እዚህ ቡና ቤት የምንሠራ ብዙዎቻችን ከሃይስኩል አልዘለቅንም፡፡

ደግሞስ ቀለም ለሴት ልጅ ምን ይፈይዳል? ሴት ልጅ ቁንጅና ይኑራት ብቻ፡፡ መልክ ካለ ሁሉ አለ፡፡
ይህን ብሽቅ ሥራ እየሠራሁ ረብጣ ገንዘብ አፍሳለሁ፤ ግን ይህ ነዉ የሚባል የአፈራሁት ጥሪት የለም፡፡ የዘወትር ጥረቴ የዕለት ቀዳዳዬን ከመሙላት ዘሎ አያዉቅም፡፡ ማለቴ የወደፊት ዕጣዬን በቀቢፀ ተስፋ የምጠብቅ ሰዉ ነኝ፡፡ ደግሞስ የወደፊቱን ጊዜ አስረግጦ መተንበይ የሚችል ማን ነዉ? ሰዉ በዕጣ ፈንታዉ እግረ ሙቅ የተጠፈረ ፍጡር ነዉ፡፡ ማለቴ ሕይወት ከሰዉ ልጅ ትልም አፈንግጦ በዘፈቀደ በራሱ ቅያስ የሚነጉድ ነዉ፡፡ እናም የሰዉ ድካም ከንቱ ነዉ፡፡ እነሆ ለምሳሌ፣ ከቀናት በፊት የምሠራበት ቡና ቤት ባለቤት ወይዘሮ ሮማን ብቸኛ ልጅ በሠርጓ ዋዜማ እንደ ሸክላ ተሰበረች፣ ገና በለጋ ዕድሜዋ፡፡ ያ ሁሉ ልፋቷ  በሞት ተደመደመ፡፡

አሁን እንደዉ ያን ዉብ ገላ ምስጥ ይበላዋል? የሰዉነት ፋይዳ ምንድን ነዉ? ሰዉ ከትቢያ የሚልቅ ዋጋ አለዉን? ሰዉ ከጉንዳን፣ ከድንጋይ፣ ከአሸዋ፣ ከአፈር በምን ሚዛን ይልቃል? ሕይወት ፋይዳ ቢስ አይደለምን? በየትኛዉም ቅፅበት እንዳልነበር የሚሆን ወረት፡፡   
 የእኔ የኑሮ ርዕዮተ ዓለም የአሳማ ነዉ፡፡ ሀፍተ ሥጋ ወዳድ ነኝ፡፡ ለነገሩ የእኔ ኑሮ ሥጋ ለሥጋ አይነት ነዉ፡፡ እናም በልቼ እንዳድር ያበቃኝን ሥጋዬን ማዋደዴ የሚያስደንቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ዉበቴ እስካልረገፈ ድረስ በልቼ ማደር እችላለሁ፡፡ የሕይወት ርዕዮተ ዓለሜን ሌሎች አያዉቁትም፡፡ ቢያዉቁት ምናልባት ይሳለቁብኝ ይሆናል፡፡ እኔ ግን ለለግጣቸዉ ቁብም የለኝ፡፡ ስለ ነገ ለምን ልጨነቅ? ደግሞስ በሰቀቀን የተቀበልነዉ ትናንት እንደ ጥላ እንደዘበት ሲያልፍ አልታዘብንም? ታዲያ ነገ ምኑ ያጓጓል? ከድካም በቀር ከትናንት ኑረት ምን አተረፍኩ? መጪዉ ጊዜ ከኖርኩት ትናንት የተለዬ ሊሆን ይችላል?  

ባልኮኒዉን ከበዉ ቢራ የሚጨልጡት ጋለሞታ የሥራ ባልደረቦቼ ሳቅና ንትርክ አለሁበት ድረስ ይሰማል፡፡ ያዉ እንደ ለመዱት ሰዉ እያሙ ይሆናል፡፡ የቡና ቤት ሴት እንደ ሀሜት ከልቧ የምትወደዉ ነገር የለም፡፡ አብዛኛዉ የቡና ቤት ወሬ በግለሰቦች ታሪክ ላይ የሚሽከረከር ነዉ፡፡ መነሻዉም መድረሻዉም የሌሎች የተሸሸገ ጀርባ ነዉ፡፡ የሌሎችን የተሸሸገ የጀርባ ታሪክ የመቅደዱ ሂደት ተወዳጅ የሆነዉ ሁሉም የወሬ ኤክስፐርት፣ የወሬ ፕሮፌሰር የገዛ ሕይወቱን በከፊልም ቢሆን ተፅፎ ስለሚያገኝበት ነዉ፤ ስለሌሎች ማዉራት ስለራስ መስማትም ጭምር በመሆኑ ነዉ፡፡
ማኅበራዊ መስተጋብሬ ሰፊ ቢሆንም አንደበተ ቁጥብ ነኝ፡፡ በእዚህም ምክንያት አንዳንዶች ጋግርታም ናት ይሉኛል፡፡ ዝምታዬ ማንነቴን የጋረድኩበት ጭንብል ነዉ፡፡ ምስጢሬን በልቤ እቀብራለሁ እንጂ ለሌሎች አልነዛም፣ ወዳጆቼ እንኳ ልቤን አያዉቁትም፡፡ ጭንብሌ ቢገፈፍ የሚገለጠዉ ግብዝነቴ፣ ቂመኛነቴ፣ ከሀዲነቴ፣ ራስ ወዳድነቴ፣ ቅናቴ፣ ሀኬተኛነቴ፣ ጨካኝነቴ እና ሴሰኛነቴ ነዉ፡፡ አንደበተ ቁጥብነቴ ስሜ በሌሎች እንዳይጠለሽ የጋረደ ግምጃዬ ነዉ፣ በሐሜት ከመብጠልጠል የሚተርፍ ሰዉ ባይኖርም፡፡ ክፉም ሆንክ ደግ በሌለህበት እንደ ሙዳ ሥጋ ትቦጨቃለህ፣ እንደ ቋንጣ ትዘለዘላለህ፡፡ ቢሆንም ግን ቁጥብነትን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ወዳጅ አገኘሁ ብሎ ለባዕድ ገመናን ገልጦ መንዛት አይገባም፡፡ ቀንደኛ ጠላቶቻችን ትናንት አብረዉን የበሉ አይደሉምን? መቃብራችንን ለመማስ የሚማስኑት የአሟሟታችንን መንገድ ስለሚያዉቁት አይደለምን? የዉድቀታችንን ፈለግ? የዛሬ ወዳጆቻችን ነገ ሲክዱን ጠልፈዉ የሚጥሉን በሽንቁራችን ገብተዉ ነዉ፡፡ 

ቡና ቤቱ ዉስጥ ከሚሠሩ ሴቶች በንፅፅር ያልጠለሸ ስም ያለኝ እኔ ነኝ፣ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ቢሆንም፡፡ ላይ ላዩን ሐሜትን የምፀየፍ ልምሰል እንጂ የሰዎችን ጀርባ መበርበር እወዳለሁ፡፡ አንዱ የሌላዉን ምስጢር እንዲዘከዝክልኝ ማድረጉም ለእኔ ተራ ተክህኖ ነዉ፡፡ የሌሎችን ጀርባ የማወቅ ጉጉት የሌለኝ ዳተኛ መስዬ ብታይም፣ ማን ምን እንደሆነ፣ ምን እንዳደረገ፣ ምን እንደሚፈልግ ልቅም አድርጌ አዉቃለሁ፡፡ ለምሳሌ፣ አዜብ ለጋስ ብትሆንም ከእኔ የባሰች በካና ናት፡፡ ቂልነቷ የበዛ ነዉ፣ ወርቅ ላበደረ ወርቅ የምትል ናት፡፡ ማሕሌት (ቅፅል ስሟ ቲና) የታወቀች ሐሜተኛ ናት፡፡ መክሊት የረባ ያልረባዉ ነገር ቶሎ የሚያስከፋት ሆደባሻ ናት፤ የመከዳት ታሪኳን ምሬት ጆሮ ለሰጣት ሁሉ በመዘክዘክ የምታሰለች ችኮ፡፡ ባመነዉ ያልተከዳ ማን ነዉ? ሄለን (ቅፅል ስሟ ሊሊ) አዱኛ አምላኪ ናት፣ ወዳጅነትን የምትሰፍረዉ በጥቅም ሚዛን ነዉ፡፡ ርዕዮቷ የተገነባዉ “ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ” በሚለዉ ብሂል ነዉ፡፡

#Inbox @Faraw_sam

#share @ethio_fiction
2.4K viewsፋራው, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 20:33:16
#አጭር ልብወለድ

"እሽሩሩ መዉደድ--- እሽሩሩ ፍቅር"

ክፍል.....1

ሳባ እባላለሁ፡፡ ቅፅል ስሜ ጁሊ፡፡ እነሆ ዕጣ ፈንታ ካዛንቺስ የተባለ ሲኦል መንደር ወርዉሮኝ አበሳ የበዛበት የቡና ቤት ኑሮን መግፋት ከጀመርኩ ዓመታት አለፉ፡፡ የመከኑ ግን ታሪኬ ሲተረተር አብረዉ የሚወሱ (እኔ ለሌሎች ስተርክ ሳንሱር አድርጌ የምዘላቸዉ) ድፍን ሦስት ዓመታት፡፡ እዚህ ሮማን ቡና ቤት አብረዉኝ ከሚሠሩት ሴቶች ተገንጥዬ ጥጌን ይዤ ቢራ እየጨለጥኩ ተጎልቻለሁ፣ ግንባሬ ጎትቶ የሚያመጣልኝን ወንድ በቋፍ እየጠበቅኩ፡፡ እንደ ሁልጊዜዉ ጥቁር አጭር ቀሚስ ነዉ የለበስኩት፡፡ አብዛኛዉ ልብሴ ጥቁር ነዉ፡፡ ጥቁር ጨርቅ የጠይም ገላዬን ዉበት እንደሚያጎላዉ አዉቃለሁ፡፡ ከሁለት ቀን በፊት ብቅ ብሎ የነበረዉ ረጅም ሪዛም ሸበላ (ቀልቤን ሰርቆ የሄደዉ ሸበላ) ዐይኑን እንዲሁ ገላዬ ላይ ሲያንከራት አመሸ፣ ቤቱን ያ ሁሉ ቆንጆ ሴት ሞልቶት ሳለ፡፡
2.4K viewsፋራው, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 22:27:57
ለ60 አመታት እንቅልፍ በአይኔ አልዞረም የሚሉት የ80 አመት አዛውንት
ቬትናማዊው ታይ ንጎክ በ20 አመታቸው ከገጠማቸው ከባድ ህመም በኋላ ከእንቅልፍ ጋር መለያየታቸውን ይናገራሉ

የህክምና ባለሙያዎች ግን አዛውንቱ ምናልባት ስለማይሰማቸው እንጂ በቀን ውስጥ የተወሰኑ ስአታት መተኛታቸው አይቀርም ባይ ናቸው
የሰው ልጅ አይደለም ለአመታት ለጥቂት ቀናት የእንቅልፍ መዛባት ከገጠመው በጤናው ላይ ምን ይዞ እንደሚመጣ መገመት አይከብድም።

ከወደ ቬትናም የተሰማው ዜና ግን ለአመታት መነጋገሪያ ሆኖ ዘልቋል።
በዚህ አመት 80ኛ አመታቸውን የያዙት ታይ ንጎክ፥ ላለፉት ስድስት አስርት አመታት እንቅልፍ ይዞኝ አያውቅም ይላሉ።

ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው እና ጎረቤቶቻቸውም ጭምር ንጎክ ተኝተው አይተዋቸው እንደማያውቁ ነው የሚገልጹት።

አዛውንቱ በፈረንጆቹ 1962 (የ20 አመት ወጣት እያሉ) ከገጠማቸው ህመም ወዲህ ከእንቅልፍ ጋር ተሰነባብተዋል።

#ዘገባው - የአል-ዐይን ነው

#Inbox - @Faraw_sam
#share - @ethio_fiction
1.7K viewsፋራው, 19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ