Get Mystery Box with random crypto!

✞ ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሀገራችን/2/ ይላክልን/3/ ቸሩ አምላካችን ኢትዮ | መዝሙረ ዳዊት

✞ ሰላም ለኢትዮጵያ

ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሀገራችን/2/
ይላክልን/3/ ቸሩ አምላካችን

ኢትዮጵያ ታበፅ ነበር ያዝማሬ
አቅጣጫውን ስቷል ስርዓትዋ ዛሬ
አቅናት ፈጣሪዋ ስራት እንደገና
የሰቀለችውን ታውርድ ያን በገና

አዝ______________

ያቺ የዳቦ ምድር ያዘለች አዝመራ
እንዴት ስለችግር ስለእርሀብ ታውራ
ተመልከታት አምላክ ምህረትህ ይድረሳት
ጩኸቷ ተሰምቶ በረከት አርሳት

አዝ______________

የገዛ ዋችንን በዋጋ ገዝተናል
በራሳችን ምድር ባእዳን ሆነናል
ቱፊት ታሪካችን ባህሉም ተረሳ
የሰዶምን ሀጢያት ምድራችን ተላብሳ

አዝ______________

እነሆ እግሮቻችን ለስደት ተነሱ
የናቡቴን ርስቶች በደም ተወረሱ
አንተ ብቻ አብሰው ያይናችንን ለቅሶ
ወድቀናል ከደጅህ ሀዘናችን በዝቶ

አዝ______________

ያቺ የዳቦ ምድር ያዘለች አዝመራ
እንዴት ስለችግር ስለእርሀብ ታውራ
አምላክ ተመልከታት ምህረትህ ይድረሳት
ጩኸቷ ተሰምቶ በረከት አርሳት


መዝሙር
ዘማሪ በርሱፍቃድ እንዳርጋቸው

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥