Get Mystery Box with random crypto!

ከመ ፀበል ዘነፋስ ዘረውም ደብረ ይድራስ ትርጉሙም እንደ ነፋስ በይድራስ ተራራ በተኑት | መዝሙረ ዳዊት

ከመ ፀበል ዘነፋስ ዘረውም ደብረ ይድራስ

ትርጉሙም

እንደ ነፋስ በይድራስ ተራራ በተኑት
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን


እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዝርወተ አፅም ለስባራ አፅሙ ዓመታዊ በዓል በስላም አደረሳችሁ አደረስን

ጥር ፲፰(18) ዝርወተ አፅሙ ለጊዮርጊስ ወያዕቆብ ዘንጽቢን ዘአፃዕደው ሥዕርቶየን ለአንስት ወተዝካሮ ለማርያ ወማርታ ወቅዱስ ባኮስ ኢትዮጵያዊ

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

እስመ ኀልቀ ከመ ጢስ መዋዕልየ
ወነቅጻ ከመ ሣዕር አዕፅምትየ
ተቀሠፍኩ ወየብስ ከመ ሣዕር

✤ ትርጉም ✤

ዘመኔን እንደ ጢስ አልቃለችና
አጥንቶቼም እንደ መቃጠያ ተቃጥለዋልና
ተቀሠፍሁ ልቤም እንደ ሣር ደረቀ

መዝ ፻፩-፫
101 3

✤ ወንጌል ✤

ዮሐ ም ፲፩ ቁ ፲፱-፴፫
11 19 33

የቅዳሴ ምንባባት

ሮሜ ም ፰ ቁ ፴፭-ፍ.ም
፩ ጴጥ ም ፫ ቁ ፩-፯
ግብ.ሐዋ ም ፲፯ ቁ ፴-ፍ.ም

❖ ምስባክ ❖

ወእምኵሉ ያድኀኖሙ እግዚአብሔር
እግዚአብሔር የዐቅብ ኵሉ አዕፅምቲሆሙ
ወኢይትቀጠቀጥ አሐዱ እምውስቴቶሙ

ትርጉም

እግዚአብሄርም ከሁሉ ያድናቸዋል
እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል
ከእርሱም አንድ አይሰበርም

መዝ ፴፫-፲፱
33 19

❖ ወንጌል ❖

ማቴ ም ፭ ቁ ፵፪-ፍ.ም
5 42 ፍፃሜው

❖ ቅዳሴ

ዘወልደ ነጎድጓድ

" በጦር ስለ ተገደሉና ስለተማረኩም ሰዎች ሁሉ፤ለድሆችና ስለ ችጋረኞችም ስለ ባልቴቶች ስለ ድሀ አደጎች "
ቅዳሴ ዮሐንስ ዘወልደ ነጎድጓድ
ም ፩ ቁ ፷፭
1 65

በዓሉን በዓለ በረከት በዓለ ፀጋ ያድርግልን ከዘመነ አስተርእዮ በረከት ይክፈልን የቸሩ አምላካችን ዘላለም ሥላሴ በቸርነቱ ይማረን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ እግዝእትነ በምልጃዋ አትለየን ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን ታሳደርብን በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ይጠብቅን ቤተክርስቲያን ቅድስት በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን ከሊቀ ሰማዕታት ከቅዱስ ጊዮርጊስ በረከቱ ይደርብን በቅዱሳኑ ፀሎት ይማረን ከቅዱሳት ደናግል ማርያ ወማርታ ለቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢ ከቅዱስ ባኮስ ኢትዮጵያዊ በረከታቸው ይደርብን በዓልን ተከትሎ ከሚመጣ መቅሠፍት አምላክ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይሰውረን ይጠብቅን ፀሎት ሙሴ ዕጣነ አሮን ዝማሬ ዳዊት ቅዳሴ መላዕክት የተቀበለ አምላክ የኛንም ፆም ፀሎት ምስጋና ስግደት በብሩህ ገጽ ይቀበልልን ለአበው ቅዱሳነ ሁሉ የተለመነች እመ አምላክ እግዝእትነ ማርያም ለኛም በምህረት ትለመነን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን ለሃገራችን ስላም ለህዝባችን ለአንድነት ይስጥልን አቤቱ ባሪያህ የሚሆን ሳዕለ ሥላሴን አስበው ለሁላችንም ፍቅር ይስጥን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥