Get Mystery Box with random crypto!

ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ ትርጉሙም ለመንግሥቱ ፍፃሜ የለውም   ጸሎት ሃይማኖት ወሠ | መዝሙረ ዳዊት

ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ

ትርጉሙም

ለመንግሥቱ ፍፃሜ የለውም
  ጸሎት ሃይማኖት ወሠለስቱ ምዕተ ወጉባኤ ኒቅያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለአበው ቅዱሳን ወ318ቱ ሊቃውንት አው ጉባኤ ኒቅያ ዓመታዊ በዓል በስላም አደረሳችሁ አደረስን

ህዳር ፱(9) ይስሐቅ ሊቀ ጳጳስት ዘእስክንድርያ ወጉባኤሆሙ ለ፫፻፲ወ፰ ርቱዓነ ሃይማኖት በኒቅያ ለእለእስክድሮስ ሊቅ  ወአትናቴዎስ ሐዋርያዊ

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

ንጉሥ ለይትፌሣሕ በእግዚአብሔር
ወይከብር ኩሉ ዘይምሕል ኪያሁ
እስመ ይትፈጸም አፍ ዘይነብብ ዐመፃ

✤ ትርጉም ✤

ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል
በእርሱ በሚምል ሁሉ ይከበራል
ሐሰትንም የሚናገር አፍ ይዘጋል
            መዝ ፷፪-፲፩
                   62   11

✤ ወንጌል ✤

ማቴ ም ፲፰ ቁ ፲፪-፳፫
           18     12  23

የቅዳሴ ምንባባት

ቆላ ም ፪ ቁ ፭-፲፫
፪ ዮሐ ም ፩ ቁ ፮-፲፪
ግብ.ሐዋ ም ፲፭ ቁ ፳፪-፴

❖ ምስባክ ❖

ወነበቡ ዓመፃ ውስተ ዓርያም
ወአንበሩ ውስተ ሰማይ አፉሆሙ
ወአንሶሰወ ውስተ ምድር ልሳኖሙ

ትርጉም

ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ
አፋቸውን በሰማይ አኖሩ
አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ

             መዝ ፸፪-፰
                    72  8

❖ ወንጌል ❖

ዮሐ ም ፲ ቁ ፳፭-ፍ.ም
         10     25  ፍፃሜው

❖ ቅዳሴ ❖

ዘ፫፻(ግሩም) ሠለስቱ ምዕተ

" የተቀበል እኛ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ነን፤ሃይማኖትን ያቀናን ሙሽራዋ አምላካችን እግዚአብሔር የሆነ የቅድስት ቤተክርስቲያንን ህግ የሠራን "
     ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕተ
              ም ፩ ቁ ፻፵፬
                  1     144

በዓሉን በዓለ ምህረት በዓለ ፀጋ ያድርግልን ቸሩ አምላክ ዘላለም ሥላሴ በቸርነቱ ይማረን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምልጇዋ ትጠብቅ ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን ታሳደርብን በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ይጠብቅን ቤተክርስቲያን ቅድስት በረድኤት ይጠብቅልን ከ 318ቱ ሊቃውንት በረከታቸው ይደርብን ጉባኤ ሊቃውንት ጉባኤ የተቀበለ የኛንም ፆም ፀሎት ምሕላ ይቀበልልን በቅዱሳኑ በሰማዕታት ፀሎት ይማረን ከሊቁ ከአባታችን ከለእለእስክድሮስ ቅዱስ አትናቴዎስ ሀዋርያው በረከታቸው ይደርብን የእነሱ ሃይማኖት ያፀና የእኛም በሃይማኖት በምግባር ያጸናን አምላክ ቅዱሳን ለሃገራችን ስላም ለህዝባችን አንድነት ይስጥልን ለሃገራችን ለቤተክርስቲያን እንፀልይ ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን የአበው በረከት በሁላችንም ላይ ያሳደርብን አቤቱ ባሪያ የሚሆነውን ሳዕለ ሥላሴ አስበው ለመሪዎች ሁሉ አስተዋይ ልቡና ይስጥልን ለተዋህዶ ልጆች በሙሉ የቂም እና የፀብ ጊዜ አይደለም ሁላችንም የሚሆን የሚበጅው ፍቅር ስላም አንድነት ነው ፍቅር ስላም ያድለን ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ የቃል ኪዳን ምድር ጠብቅ አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ አባታችን ሆይ ሃገራችን አቤቱ ጠብቅልን ከሚታየው ሁሉ ነገር ጠብቀን ደም ሰማዕታት የተቀበለ አምላክ ስለ ቀናች ሃይማኖት ራሳቸውን የሰጡት ሁሉ ደማቸውን ጸናታቸው ለሁላችንም ሰጠን አምላክ ሰማዕታት ሁላችንም የዳዊት መዝሙር መዝሙር ፹፬(84) ሁላችንም እንፀልይ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥