Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ዳዊት

የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የሰርጥ አድራሻ: @mezmurochh
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.22K
የሰርጥ መግለጫ

🔔🔔🔔 መዝሙረ-ዳዊት 🔔🔔🔔

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉ
☞ @mezmurochh
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
☞ @Mezmuredawit_bot ላይ ያገኙናል

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2022-12-11 12:26:38 ✞ ለመቤቴ ምስጋና አቀርባለው

ለመቤቴ ምስጋና አቀርባለው
ለስምሽም እምበረከካለው
የዳዊት ልጅ የእያቄም የሐና
ቅድስት ዘር የሒወቴ ዋስትና

እመቤቴ ____ ሁለተኛ ሄዋን
እመቤቴ ____ ዳግሚት ሰማይ
እመቤቴ ____ ምስራቀ ምስራቃት
እመቤቴ ____ እሙ ለአዶናይ
እመቤቴ ____ ብርሐንነት ያለው
እመቤቴ ____ ፋናን የተሸከምሽ
እመቤቴ ____ የወርቅ መቅረዛችን
እመቤቴ ____ ድንግል አንቺ እኮ ነሽ

አዝ__

እመቤቴ ____ የነቢያት ትንቢት
እመቤቴ ____ የሰማዕታት እናት
እመቤቴ ____ አክሊለ መላእክት
እመቤቴ ____ ስብከት የሐዋርያት
እመቤቴ ____ የእውራን ብርሐን
እመቤቴ ____ ለተጠሙ ወይን
እመቤቴ ____ ሰማያዊ ህብስት
እመቤቴ ____ ያስገኘሽ ጌታን

እዝ____

እመቤቴ ____ሐመረኖህ ድንግል
እመቤቴ ____ የማክሰኞ እርሻ
እመቤቴ ____ እርግብየ ስልሽ
እመቤቴ ____ ነይ የኔ መሸሻ
እመቤቴ ____ በምልጃሽ ጥላስር
እመቤቴ ____ አስጠልይኝ ድንግል
እመቤቴ ____ በመንግስተ ሰማይ
እመቤቴ ____ የከበርኩ እንድሆን

አዝ___

እመቤቴ ____ አማናዊት መቅደስ
እመቤቴ ____ መአዛሽ ያማረ
እመቤቴ ____ ንፁህ ፅጌሬዳ
እመቤቴ ____ ፍፁም የከበረው
እመቤቴ ____ ከጥማቸው እረኩ
እመቤቴ ____ የሲኦል ነብሳት
እመቤቴ ____ ስምሽ መጠጥ ሆኖ
እመቤቴ ____ ኪዳነ-ምህረት

መላከ ሰላም
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
1.5K views••●◉ Estifanos ◉●••, 09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 11:27:39
✣ ቅዱስ መርቆሬዎስ

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
1.0K views••●◉ Estifanos ◉●••, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 11:27:39 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

መዝሙረ ዳዊት

◉ መርቆሬዎስ ◉

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
@mezmurochh
@mezmurochh
@mezmurochh
|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
1.0K views••●◉ Estifanos ◉●••, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 11:27:39 ✞ መርቆሬዎስ

መርቆሬዎስ /2/
የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ
እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ

ባስልዮስ ጎርጎሪወቀስ ሰምሯል ልመናቸው
ስዕሉ ዘለለ ታምራት አያችሁ
እናንተን የረዳ መጥቶ በፈረስ
ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆሬዎስ

አዝ_____________

ዑልያኖስ ተገድሏል ሃይማኖት ይስፋፋል
ብሎ መሰከረ መርቆርዮስ ሃያል
ገፀ ከላባቱ ባህርይ ቀየሩ
እርሱን ለማገልገል ከእግሩ ስር አደሩ

አዝ_____________

ትካዜ ሀዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ
መርቆርዮስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ
በፀሊም ፈረሱ እየገሰገሰ
መርቆሬዎስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ

አዝ_____________

ስቃዩን ሊያረዝም ዳኪዎስ ወደደ
ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ
በጋለ ሹል ብረት መርቆሬዎስ ተወጋ
ስሙ ተሰየመ ከሰማዕት ጋ

አዝ_____________

አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር
መፍቅሬ አብ ካለ ያኘሎፓዴር
ቂሳርያ እስር ቤት መርቆሬዎስ ታሰረ
ወህኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
975 views••●◉ Estifanos ◉●••, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 10:49:16 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

መዝሙረ ዳዊት

በ ዘማሪ ገብረ-ዮሀንስ ገብረ-ጻድቅ
✣ የክብርን ዘውድ ጭኖ ✣

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
@mezmurochh
@mezmurochh
@mezmurochh
|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
2.5K views••●◉ Estifanos ◉●••, 07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 10:49:16 ✞ የክብርን ዘውድ ጭኖ

የክብርን ዘውድ ጭኖ ታየ ካህኑ
በወርቅ ማዕጠንት ሞልቶ ሲያርግ እጣኑ
እንደ ሱራፌል መልዐክ ደራርቦ አክናፍ
ቆመ ተክለሐይማኖት ከእሳቱ ደጃፍ

ነበልባል ከጋረደው ከሥላሴ ሰገነት
ባለ ግርማ ሞገስ ነው ሲሰየም ለአገልግሎት
ሀያ አራቱን ካህናት ተቀላቅሎ ተክልዬ
ህዝቤን ማርልኝ ይላል አክብርልኝ ጌታዬ

አዝ_____________

በትረመስቀሉን ተክሎ ከጭንጫው አመነጨ
ሰላም ለብሶ እንዲሄ ጸበሉን የተረጨ
በረገጠው ምድር ላይ ቃልኪዳኑ ፈሰሰ
የሰማዩን በረከት በእኛ ላይ ነሰነሰ

አዝ_____________

ተቀጣጠለ ዝናው ከአድማስ ማዶ ተሰማ
በጸሎቱ ዘለፈው ድፍንፍኑን ጨለማ
ከመናንያን ጋራ ይመንናል በፍቅር
አባ ተክለሐይማኖት የኢትሳው መምህር

አዝ____________

አለው ጥዑም መዓዛ የእጁ ጠረን ሽታ
ለተሳለመው ሁሉ ይሰጣል ልዩ ደስታ
ገና ከገድሉ መፃፍ ስንኞች ሲበተኑ
የቤልሆን ሰራዊት እንደ እንፋሎት ተነኑ


ዘማሪ
ገብረ-ዮሀንስ ገብረ-ጻድቅ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
2.6K views••●◉ Estifanos ◉●••, 07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 19:38:01
መንፈሳዊ ጉዞ እመጓ ቅዱስ ዑራኤል እና ሰረርኩላ ቅዱስ ሚካኤል 

እነዚ ገዳማት መንዝ ውስጥ የሚገኙ ናቸው ከዛውስጥ አንዱ  እመእጓል ቆጵሮስ ኢየሱስ ቅዱስ ዑራኤል ገዳም ሲሆን እሱም

ድንግል ማርያም ከልጅዋ ጋር በተሰደደች ግዜ የተቀመጠችበት ቦታ ነው

የቦታውን ስም እራሱ ጌታችን ነው ያወጣው /እመእጓል/ ብሎ እመእጓል ማለት የእናትና የልጅ ሀገር ማለት ነው።

በቦታው ተራራወች አሉ ከዛውስጣ ሁለቱ

1 ክሊና ተራራ ይባላል ይህ ተራራ ጌታችን ለ እመቤታች  ኢትዮጵያን አስራት ሀገርሽ ትሁን ብሎ የሰጠበት ቦታ ነው።

2 ቆጵሮስ ተራራ ነው ይህ ተራራ ቅዱስ ዑራኤል የጌታን ደም የረጨበትን ጽዋ መነሳነስ የሰወረበት ተራራ ነው።

ሰረርኩላ ቅዱስ ሚካኤል

በ3 ቅዱሳን ናኦድ እያቄም ናትናኤል የተመሰረተ ታላቅ ቅዱስ ስፍራ ነው  ቦታውን የረገጠ 12 ትውልድ ይማርለታል የበረከት የታሪክ ቦታ
ሲሆን በቦታውም ተገኝተን የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን በአምላከ ቅዱስ ሚካኤል ስም እንጠይቃለን።

የጎዞው መነሻ ቀን ታህሳስ 8 መመለሻ ታህሳስ 10

የጎዞ ዋጋ 1000 ብር መስተንግዶን ማረፊያን ጨምሮ

መነሻ ሰአት 11

መነሻ ቦታ መስቀል አደባባይ
               መገናኛ
               አያት አደባባይ

በዚህ ስልክ ደውለው መመዝገብ ይችላሉ
0991324844
0989094874
2.7K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 19:36:50 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

   ዘማሪ ሲስተር ልዲያ ታፈሰ

        ◦ እንወዳታለን ◦

  ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
          @mezmurochh    
          @mezmurochh    
          @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
2.2K views••●◉ Estifanos ◉●••, 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 19:36:50 ✞ እንወዳታለን 

የጨለማው ዘመን ማብቂያ ምልክት ናት
ለዚህ ነው ማርያምን እጅግ የምንወዳት
አይቀንስም ክብሯ ዓለም ምንም አለ
ቢያመሰግናት እንዴት በታደለ
ቢያመሰግናት እንዴት በታደለ 

በመገረም ተይዞ ዓለም በጨለማ
ድኅነት እየራበው ጽድቅ እየተጠማ
ከቁስል ለመዳን የመድኃኒቱ እናት
የሕይወት ምንጩን መች አመሰገናት
እኛ ግን ክብር አለን እኛ ግን ፍቅር አለን
ዓለም ምንም ይበል እንወዳታለን
 
አዝ___

በደሙ አክሞናል የእርሷ የሆድ ፍሬ
ዓለም ክብሯ ርቆት ይጠይቃል ዛሬ
ታላቁ እውነታ ምሥጢሩ ይሄ ነው
አምላክን ያየነው በእርሷ እናትነት ነው
 እኛ ግን ክብር አለን እኛ ግን ፍቅር አለን
ዓለም ምንም ይበል እንወዳታለን

አዝ___

ለእናቶች ቀን ሠጥቶ ዓለሙ ሲዘክር
እንዴት ይቃወማል የእርሷን ምስጋና ክብር
እግዚአብሔር ማስተዋል ጥበቡን ገልጦለት
የድንግሊቱን ፍቅር በልቡ ይሳልለት
እኛ ግን ክብር አለን እኛ ግን ፍቅር አለን
ዓለም ምንም ይበል እንወዳታለን

አዝ___

በቀኙ ምትቆም ማርያም ንግስቲቱ
ለክብሯ መዘመር ምኑ ነው ስሕተቱ
ከቅዱስ ከገብርኤል እንደ ሰማነው ቃል
መልካሙን ምስጋና ልባችን ያፈልቃል
እኛ ግን ክብር አለን እኛ ግን ፍቅር አለን
ዓለም ምንም ይበል እንወዳታለን

ዘማሪ ሲስተር ልዲያ ታፈሰ

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

          @mezmurochh
          @mezmurochh
          @mezmurochh     

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
2.3K views••●◉ Estifanos ◉●••, 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 07:19:06
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥@teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
3.2K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ