Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ዳዊት

የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የሰርጥ አድራሻ: @mezmurochh
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.22K
የሰርጥ መግለጫ

🔔🔔🔔 መዝሙረ-ዳዊት 🔔🔔🔔

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉ
☞ @mezmurochh
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
☞ @Mezmuredawit_bot ላይ ያገኙናል

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 31

2022-12-01 07:18:50 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

◎ ሊቀ-መዘምራን ዲ/ን ቴድሮስ ዮሴፍ

        ◉ እኔ አንት ፊት ◉

  ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
            @mezmurochh    
            @mezmurochh    
            @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
3.0K views••●◉ Estifanos ◉●••, 04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 07:18:50 ✞ እኔ አንተ ቤት

እኔ አንተ ቤት እኔ አንተ ፊት
የምቆም ሠው አይደለሁም
ግን ፍቅር ነህ ለዘለዓለም
የሚመስልህ ማንም የለም/2/


ፀሎቴ ቢሆን ለወረት ጎዶሎ ቢሆን የኔ እምነት
ባረከኝ እኔን ከሠማይ በደል ጥፋቴንም ሳታይ
ቀባኸኝ ጠርተኸኝ ከዱረ ሠጠኸኝ ከፍ ያለ ወንበር
ሳይኖረኝ አንድም በጎነት ባረከኝ በእጅህ በረከት

አዝ___

ቃልኪዳንህን አክባሪ ታማኝ ነህ ሁሌም መሀሪ
የማልከውንም መሀላ አትረሣም አትልም ችላ
መካሪ ድንቅ መምህሬ ላንተ ነው ዜማ መዝሙሬ
ፍቅር ነህ ከአባትም በላይ የሠማይ የምድር ሢሣይ

አዝ___

መሻቴን ብቻ ስላየህ ደካማ ልጅክን ጎበኘህ
ብቃቴ መቼ ሆነና ያቆመኝ ላንተ ምስጋና
አንኳኩ ስላልክ አንኳኳው ጠይቁ ስላልክ ጠየኩኝ
ከፍተሃል በርህን ለኔ የታተምኩብህ መድህኔ


                ሊቀ-መዘምራን
           ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥  @mezmurochh ✥
   ✥  @mezmurochh ✥
   ✥  @mezmurochh ✥
  ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
3.0K views••●◉ Estifanos ◉●••, 04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 21:42:08 እግዚኦ ኩነኔከ ሀቦ ለንጉሥ

ትርጉም

አቤቱ ፍርድህን ለንጉሥ ስጥ

       መዝ ፸፩-፩ 
              71  1

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለቅድስት ጽዮን ማርያም ድንግል ማኅደር አምላክ ዓመታዊ መታሰቢያ  በዓል በስላም አደረሳችሁ አደረስን

ህዳር ፳፩(21) ጽዮን ወተዝካረ በዓለ እግዝእትነ ማርያም ወጎርጎርዮስ ወቆዝማስ ሊቀ ጳጳስት ወዮሐንስ ወካልእን ሰማዕት ወጻድቃን ዘእስሙናይን ወዲቦራ

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ
ወተናገሩ በውስተ ማኀፈዲሃ
ደዩ ልበክሙ ውስተ ኀይላ

ትርጉም

ጽዮንን ክበቡዋት በዙሪያዋም ተመላለሱ
ግንቦችዋንም ቊጠሩ
በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ

             መዝ ፵፯-፲፪
                    47   12

✤ ወንጌል ✤

ማቴ ም ፳፫ ቁ ፩-ፍ.ም
           23     1   ፍፃሜ

የቅዳሴ ምንባባት

፪ ቆሮ ም ፮ ቁ ፲፪-ፍ.ም
፩ ጴጥ ም ፪ ቁ ፭-፲፩
ግብ.ሐዋ ም ፯ ቁ ፵፬-፶

❖ ምስባክ ❖

እስመ ኀረያ እግዚአብሔር ለጽዮን
ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኀደሮ
ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም

ትርጉም

እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦታልና
ማደርያውም ትሆነው ዘንድ ወዶአታልና እንዲህ ብሎ
ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት

        መዝ ፻፴፩-፲፫
               131  13

❖ ወንጌል ❖

ማቴ ም ፳፩ ቁ ፵፪-ፍ.ም
            21     42  ፍፃሜው

❖ ቅዳሴ ❖

ዘእግዝእትነ

" የሙሴ ጽላት ጳጦስ የተባለች የሲና ዕፅ በካህን አሮን ልብስ የነበረች ጽናጽል ዳግመኛም የበቀለችና ያበበች ያፈራችም በትረ አንቺ ነሽ "
         ቅዳሴ ማርያም
           ም ፩ ቁ ፴፫
                1     33

በዓሉ በዓል በረከት በዓለ ሐሴት በዓለ ፀጋ ያድርግልን ቸሩ አምላካችን ዘላለም ሥላሴ በቸርነቱ ይማረን ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ምልጇዋ ትጠብቅን ፍቅሯን በልባችን ጣዕሙን በአንደበታችን ታሳደርብን በዕፅ መስቀሉ ይባረክን ይጠብቅን ቤተክርስቲያን ቅድስት በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን በቅዱሳን ሰማዕታት ፀሎት ሁላችንም ይማረን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን ፆሙን ፆመ አኩቴት ያድርግልን ፆሙን ለማበርከት ያብቃን ጽላተ ሙሴ ጽላተ ኪዳን በሃገራችን በረድኤት ይጠብቅልን ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ የቃልኪዳን ሃገር እባክህ ጠብቅት እመ አምላክ ድንግል ማርያም ስለእኛ አይደለም በረሃ ውስጥ ስለህዝብ ብለው ዓለም ንቀው ስለገቡት ስለአባቶችን ስለእናቶችን ብለሽ የቃልኪዳን ምድርሽ ጠብቂያት አቤቱ ለሃገራችን ስላም ለህዝባችን ፍቅር አንድነትን አምላክ ቅዱሳን እባክህ ለሁላችንም ስጠን ጸሎተ ምናሴ ዕጣነ አሮን የተቀበለ አምላክ የኛንም ባሪያዎችህ ፆም ፀሎት ምጽዋት ንስሐ ስግደት ብሩህ ገጽ ይቀበልልን ደም ሰማዕታት ትንቢተ ነቢያት ስብከት ሐዋርያት ጉባኤ ሊቃውንት ያጸና አምላክ እኛንም በሃይማኖት በምግባር በትሩፋት ያፀናን አምላክ ቅዱስ ሳሙኤል አቤቱ ባሪያህ የሚሆነው ሳዕለሥላሴ በምህረት በቸርነት አስበው ሁላችንም መዝሙር ዳዊት መዝሙር ፹፬(84) እንፀልይ በዓል ተከተሎ ከሚመጣ መቅሰፍት አምላክ ቅዱሳን አምላክ ሰማዕታት ይሰውረን ይጠብቅን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
1.2K views••●◉ Estifanos ◉●••, 18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:43:57
መንፈሳዊ ጉዞ እመጓ ቅዱስ ዑራኤል እና ሰረርኩላ ቅዱስ ሚካኤል 

እነዚ ገዳማት መንዝ ውስጥ የሚገኙ ናቸው ከዛውስጥ አንዱ  እመእጓል ቆጵሮስ ኢየሱስ ቅዱስ ዑራኤል ገዳም ሲሆን እሱም

ድንግል ማርያም ከልጅዋ ጋር በተሰደደች ግዜ የተቀመጠችበት ቦታ ነው

የቦታውን ስም እራሱ ጌታችን ነው ያወጣው /እመእጓል/ ብሎ እመእጓል ማለት የእናትና የልጅ ሀገር ማለት ነው።

በቦታው ተራራወች አሉ ከዛውስጣ ሁለቱ

1 ክሊና ተራራ ይባላል ይህ ተራራ ጌታችን ለ እመቤታች  ኢትዮጵያን አስራት ሀገርሽ ትሁን ብሎ የሰጠበት ቦታ ነው።

2 ቆጵሮስ ተራራ ነው ይህ ተራራ ቅዱስ ዑራኤል የጌታን ደም የረጨበትን ጽዋ መነሳነስ የሰወረበት ተራራ ነው።

ሰረርኩላ ቅዱስ ሚካኤል

በ3 ቅዱሳን ናኦድ እያቄም ናትናኤል የተመሰረተ ታላቅ ቅዱስ ስፍራ ነው  ቦታውን የረገጠ 12 ትውልድ ይማርለታል የበረከት የታሪክ ቦታ
ሲሆን በቦታውም ተገኝተን የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን በአምላከ ቅዱስ ሚካኤል ስም እንጠይቃለን።

የጎዞው መነሻ ቀን ታህሳስ 8 መመለሻ ታህሳስ 10

የጎዞ ዋጋ 1000 ብር መስተንግዶን ማረፊያን ጨምሮ

መነሻ ሰአት 11

መነሻ ቦታ መስቀል አደባባይ
               መገናኛ
               አያት አደባባይ

በዚህ ስልክ ደውለው መመዝገብ ይችላሉ 0991324844
0989094874
844 views••●◉ Estifanos ◉●••, 11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 08:58:52
1.9K views••●◉ Estifanos ◉●••, 05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 14:01:26
ቅዱስ እስጢፋኖስ የደረሰለት በምልጃው በረዴቱ የደረሰለት በቤቱ ያደጋቹ ሁላችሁንም ጠርተናል
1.9K views••●◉ Estifanos ◉●••, 11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 20:03:32
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥@teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
2.2K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 19:53:59 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

   ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ

        ◦ ሚካኤል ይለይብኛል◦

  ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
          @mezmurochh    
          @mezmurochh    
          @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
2.4K views••●◉ Estifanos ◉●••, 16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 19:53:59 ✞ ሚካኤል ይለ'ይብኛል

ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለ' ይብኛል ሚካኤል ይለ' ይብኛል
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል(2×)


አያምርብኝ ብዘነጋው ታሪኬን
ሚካኤል ነው ያስጌጠኝ ሕይወቴን
አልረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን
ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን
ሚካኤል ያን ሁሉ ዘመን የታገስከኝ
ሚካኤል ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ
ሚካኤል የከፍታዬ መሰላል
ሚካኤል መነሻዬ ሆነሃል

አዝ____

እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳላፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ከአጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል
ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል አሳምረው ፍጻሜዬን

አዝ____

ውድቅ አረገው የጠላቴን ክፉ እቅድ
አራመደኝ በከፍታዬ መንገድ
ሊያስቀረኝ አልቻለም ሚጎትተኝ ባለጋራ
ተጥሎ ስላለ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ
ሚካኤል እሳታዊ ነህ ነበልባል
ሚካኤል ጠላቴ ፊትህ ይቀልጣል
ሚካኤል ለኔ ኃይሌ ነው መከታዬ
ሚካኤል የዘለዓለም ጠባቂዬ

አዝ____

እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳላፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ከአጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል
ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል አሳምረው ፍጻሜዬን

ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

          @mezmurochh
          @mezmurochh
          @mezmurochh     

   ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
23.9K views••●◉ Estifanos ◉●••, 16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ