Get Mystery Box with random crypto!

✞ ሚካኤል ይለ'ይብኛል ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ ይለ' ይብኛል ሚ | መዝሙረ ዳዊት

✞ ሚካኤል ይለ'ይብኛል

ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለ' ይብኛል ሚካኤል ይለ' ይብኛል
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል(2×)


አያምርብኝ ብዘነጋው ታሪኬን
ሚካኤል ነው ያስጌጠኝ ሕይወቴን
አልረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን
ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን
ሚካኤል ያን ሁሉ ዘመን የታገስከኝ
ሚካኤል ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ
ሚካኤል የከፍታዬ መሰላል
ሚካኤል መነሻዬ ሆነሃል

አዝ____

እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳላፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ከአጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል
ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል አሳምረው ፍጻሜዬን

አዝ____

ውድቅ አረገው የጠላቴን ክፉ እቅድ
አራመደኝ በከፍታዬ መንገድ
ሊያስቀረኝ አልቻለም ሚጎትተኝ ባለጋራ
ተጥሎ ስላለ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ
ሚካኤል እሳታዊ ነህ ነበልባል
ሚካኤል ጠላቴ ፊትህ ይቀልጣል
ሚካኤል ለኔ ኃይሌ ነው መከታዬ
ሚካኤል የዘለዓለም ጠባቂዬ

አዝ____

እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳላፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ከአጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል
ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል አሳምረው ፍጻሜዬን

ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

          @mezmurochh
          @mezmurochh
          @mezmurochh     

   ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥