Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ዳዊት

የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የሰርጥ አድራሻ: @mezmurochh
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.22K
የሰርጥ መግለጫ

🔔🔔🔔 መዝሙረ-ዳዊት 🔔🔔🔔

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉ
☞ @mezmurochh
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
☞ @Mezmuredawit_bot ላይ ያገኙናል

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 32

2022-11-24 10:58:28
2.9K views••●◉ Estifanos ◉●••, 07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 10:58:18
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የበረከት ልጆች የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች እንደምን ዋላችሁ እንደምን ቆያችሁኝ።

ታላቅ ገዳም ላስተዋውቃችሁ ተአምሩን ልነግራችሁ ዛሬ መጥቻለው ቻናላችን መዝሙረ ዳዊት 43600 ከዚውስጥ ቅዱስ ሚካኤል በእረዴቱ በበረከቱ የደረሰለት ቢን 5000 አላጣም በትንሹ እባካቹ እናግዛቸው እንድረስላቸው ገዳም ከአዲሰ አበባ  ባህርዳር ከባህር ልዩ ቦታው ጉሀላ ለወረዳው ከዛም 5 ሰአት የሚ ነሳ መኪና ለገዳሙ መገንጠያ ጋር ወርዳችሁ 30 ደቂቃ የእግር መንገድ ከተጎዛችሁ ቡሀላ ይገኛል። ተሪካዊ ጥንታዊ ገዳም ሲሆን በዚ ሰአት ድንቅ ድንቅ ገቢረ ተአምራትን በመስራት የብዙወችን ችግር ፈቷል በ video ለይ ሰላለው ነገር በደንገብ ተነግሯል በተቻላችሁ አቅእንዴትም አውርዶችሁ ስሙት እዮት ማውረድ ያልቻላችሁ ደም voice ብቻ በ እለቅላቹሀለው እንድትሰሙት በቻላችሁት አቅ ወንድም እህቶቼ አባት እናቶች መነኳሳትን እናግዝ ተቸግረዋል እንደዚህ ብዬ ማብራራት ውስጥ አልገባም video ስትመለከቱ ታገኙታለችሁ መርዳት ቦታውላይ ለመሄድ ምትፈልጉ ሰወች ስልክ ቁጥር የገዳሙን ባንክ አካውንት አስቀምጥላቹሀለው ጥያቄ ካላችሁ በዚህ ስልክ ቁጥር +251918077957 ደውላችሁ በደንብ ስለቦታው ብጠይቁ ይነግሯቹሀል መርዳት ማገዝ የምት ፈልጉ 1000442598391 ሙት አንሳ ማሩ ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ብላችሁ። በመላክ አግዟቸው። ወንድም እህቶቼ እመቤቴ የልባችሁን ትሙላ ተጨማሪ video ምትፈልጉ ማየት በውስጥ መስመር አናግሩኝ አባ የላኩልኝ video እልክላቹሀለው በደንብ ተአምሩን ታደንቃላችሁ @Asrasebat_17 ያናግሩኝ መልካም ቀን።
2.8K views••●◉ Estifanos ◉●••, 07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 18:29:36 ✞ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ለጾመ_ነቢያት


እግዚአብሔር አምላካችን ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ መልበሱን፣ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ወደ ግብጽ ግብር መሰደዱን፣ በባሕረ ዮርዳኖስ መጠመቁን፣ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ማብራቱን፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል ልዩ ልዩ ዓይነት መከራ መቀበሉን፣ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም ለፍርድ የሚመጣ መኾኑን በአጠቃላይ የማዳን ሥራውን በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አስቀደመው በትንቢት ተናግረዋል፡፡ ትንቢቱ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው ኾኖ ዓለምን የሚያድንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎትም በእግዚአብሔር ሰው መኾን ፍጻሜ አግኝቷል፡፡

ይህን ምሥጢር በማሰብ በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋይዜማ ድረስ እንድንጾም አባቶቻችን መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርተውልናል፡፡ ይህ ጾም፣ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ሲኾን፣ በስያሜም #ጾመ_ነቢያት (የነቢያት ጾም) እየተባለ ይጠራል፡፡ ወቅቱ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ የተፈጸመበት ስለ ኾነም #ጾመ_አዳም (የአዳም ጾም) ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም #ጾመ_ስብከት (የስብከት ጾም) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ #ጾመ_ልደት (የልደት ጾም) በመባል ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም #ጾመ_ሐዋርያት እየተባለ ይጠራል፤ ምክንያቱም ቅዱሳን ሐዋርያት "በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?" በማለት ነቢያት በጾሙበት ማለት ከልደተ ክርስቶስ በፊት ባለው ወቅት ጾመዋልና፡፡

በሌላ አጠራር ይኸው ጾመ ነቢያት #ጾመ_ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም) በመባል ይታወቃል፤ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያ እና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ተሰወረባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ በዓት ዘግተው፣ ሱባዔ ገብተው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ቢለምኑት ልመናቸውን ተቀብሎ ሱባዔ በያዙ በ፫ኛው ቀን የቅዱስ ፊልጶስን ሥጋ (በድን) መልሶላቸው በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት 'ጾመ ፊልጶስ' እየተባለ ይጠራል፡፡

ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው፣ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካበሠራት በኋላ "ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?" በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ እመቤታችን ጾማዋለችና ይህ ጾም #ጾመ_ማርያም በመባልም ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ በጾመ ነቢያት፣ ነቢያትም ሐዋርያትም፣ ቀደምት አባቶቻችንም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባናል፡፡

      ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ ጾመ መድኃኒት ያድርግል!

ምንጭ፡–
-ማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ
ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥  @mezmurochh ✥
   ✥  @mezmurochh ✥
   ✥  @mezmurochh ✥
  ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
4.2K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 09:03:37
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥@teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
1.9K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 09:03:24 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

    ገብረ-ዮሐንስ ገብረ-ጻድቅ 

          ◦ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል ◦

  ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
          @mezmurochh    
          @mezmurochh    
          @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
1.8K views••●◉ Estifanos ◉●••, 06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 09:03:24 ✞ በሰማያት ላይ

በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል
ክብርህም በምድር ይነገራል
ዘመን የሚዋጅ አለን ምስጋና
መድኃኔዓለም ስምህ ገናና (×2)

እልፋ አላፍ መላእክት
ቢቆሙ ካንተ ፊት
አያርፉም ይተጋሉ
ስሉስ ቅዱስ እያሉ

«ያለና የሚኖር»(×2)
አንተ ነህ እግዚአብሄር

አዝ_

ሊቃናት ይጮሀሉ
በጉ ድል ነሳ እያሉ
የወርቅ ፅና የያዙ
ምስጋናህን አበዙ

«ያለና የሚኖር»(×2)
አንተ ነህ እግዚአብሄር

አዝ_

በደምህ የታተሙ
ኃይልህን ተሸክሙ
የቅኔ ዑደት ሆነ
ክብርህ በአለም ገነነ

«ያለና የሚኖር»(×2)
አንተ ነህ እግዚአብሄር

አዝ_

በዙፋኑ ስር ካሉት
ከሰባቱ መናፍስት
ከታመነው ምስክር
አዲስ ውዳሴ መዝሙር

«ያለና የሚኖር»(×2)
አንተ ነህ እግዚአብሄር

                    ዘማሪ
     ገብረ-ዮሐንስ ገብረ-ጻድቅ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

      ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
    ✥     @mezmurochh    ✥
    ✥     @mezmurochh    ✥
    ✥     @mezmurochh    ✥
       ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

      ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
1.7K views••●◉ Estifanos ◉●••, 06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 11:03:22
ዛሬ የተነሳ ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥@teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
2.1K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 11:01:59 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

መዝሙረ ዳዊት

◉ መና አውርዶ ◉

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
@mezmurochh
@mezmurochh
@mezmurochh
|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
2.0K views••●◉ Estifanos ◉●••, 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 11:01:58 ✞ መና አውርዶ

መና አውርዶ እሳት አብርዶ
ሚካኤል መራን ደመና ጋርዶ

ነፀብራቃዊዉ ሚካኤል
አምደ ብርሃን ሚካኤል
ነፃ ያወጣ ሚካኤል
ህዝበ እስራኤልን ሚካኤል

ሌሊቱን ብርሃን እያደረክ
ምራን እኛንም ወደ አምላክ

አዝ________________

እሩሩ መላዕክ ሚካኤል
ያፎምያ አባት ሚካኤል
ፈጥነህ የምደርስ ሚካኤል
በጭንቀት ላሉ ሚካኤል

ጠላት ዳቢሎስ እንዳይጥለን
ቅዱስ ሚካኤል አትለየን

አዝ________________

የሚቃወሙን ሚካኤል
በእሱ እራቁልን ሚካኤል
ጠላቶቻችን ሚካኤል
ተሸነፉልን ሚካኤል

የማንችለውን እያስቻለን
ለዚህ አበቃን እየረዳን

አዝ________________

ወደ ሞት ሲሄድ ሚካኤል
ደብዳቤ ይዞ ሚካኤል
ደጉ ባህራን ሚካኤል
ከንጉስ ታዞ ሚካኤል

ቅዱስ ሚካኤል በረድሄት
ሞቱን በህይወት ለወጠለት

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
1.8K views••●◉ Estifanos ◉●••, 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 21:39:33 ➣ አንተኑ ሚካኤል ዘአውረድከ መና ➢

    ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለሊቀ መላዕክት ለቅዱስ ሚካኤል ተአምራት በዓሉ አው ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በስላም አደረሳችሁ አደረሰን

✤ ህዳር ፲፪(12) ሚካኤል ወአስተርእዮተ ዮሐንስ መጥምቅ ውስተ ደብረ ማኀው ወፊላታዎስ ሊቀ ጳጳስት ወበእደ ማርያም ንጉሥ ዘኢትዮጵያ ✤

✤ ዘነግህ ምስባክ

እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ
ወብዙኀ ይትሐሠይ በአድኀኖትከ
ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ

✤ ትርጉም ✤

አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል
በማዳንህ እጅግ ሐሤትንና ያደርጋል
የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው

            መዝ ፳-፩
                 20   1

✤ ወንጌል ✤

ሉቃ ም ፲፱ ቁ ፲፩-፳፰
           19    11  28

የቅዳሴ ምንባባት

ሮሜ ም ፱ ቁ ፲፯-፳፬
ይሁዳ ም ፩ ቁ ፱-፲፬
ግብ.ሐዋ ም ፳ ቁ ፳፰-፴፩

❖ ምስባክ ❖

ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ
ለእለ ይፈርህዎ ወያድኀኖሙ
ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር

ትርጉም

የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሰፍራል ያድናቸውማል
እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቅመሱ እዩም

              መዝ ፴፫-፯
                     33   7

❖ ወንጌል ❖

ማቴ ም ፲፰ ቁ ፲፭-፳፩
            18     15  21

❖ ቅዳሴ ❖

ያዕቆብ ዘሥሩግ አው ባስልዮስ

" አቤቱ የሚያረጅ የሚጠፋ ይህ ተስፋ ዓለም ለእኛ ለክርስቲያን ወገኖችህ አይደለም፤የሚመጣውን ተስፋ እናደርጋለን ደጅም እንጠናለን እንጂ "
     ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ
              ም ፩ ቁ ፹፯
                  1      87

በዓሉ በዓለ ምህረት በዓለ ፀጋ በዓለ በረከት ያድርግልን ቸሩ መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይማረን እመ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምልጇዋ ትጠብቅ በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ቅድስት ቤተክርስቲያን በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን ከሊቀ መላዕክቱ ከቅዱስ ሚካኤል በረከት ይክፈልን በቅዱሳኑ ፀሎት ሁላችንም ይማረን ለቅዱሳኑ ሁሉ የተለመነች እመቤታችን ማርያም ለሁላችንም በረከት በምህረት ትለመነን ለሃገራችን ለህዝባችን ስላም ይስጥልን ደም ሰማዕታት ቅዳሴ መላዕክት ዝማሬ ዳዊት የተቀበለ አምላክ ቅዱሳን የኛንም ፆም ፀሎት ምሕላ ምስጋና ይቀበልልን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን ለሁላችንም ልቦና ይስጥልን ለመሪዎች ሁሉ  አስተዋይ ልቦና ይስጥልን ፍቅር እግዚአብሔር ፈሪሀ እግዚአብሔር ያድለን መዝሙር ዳዊት መዝሙር ፹፬(84) ሁላችንም እንፀልይ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
1.3K views••●◉ Estifanos ◉●••, 18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ