Get Mystery Box with random crypto!

🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
የሰርጥ አድራሻ: @menfesawitsufoche
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.87K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ትምህርታዊ ጹሑፎችን፣ ብሂለ አበው፣ ከመጽሐፍት ዓለም እና ሌሎችም ''መንፍሳዊ ሥነ-ጹሑፎችን'' ያገኛሉ።
.
.
.
ሃሳብ አስተያየታቹን ወይም ቻናሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ስነ-ጹሑፎች ለመደገፍ @kal002 ላይ አድርሱን።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-03 20:17:47 መድሃኔዓለም ነው!


ከሰማያት ወርዶ
ከድንግል ተወልዶ
ክብሩን ሁሉ ትቶ
ያከበረኝ ሞቶ
የነፍሴ ቤዛዋ
ዘውድ ማአረጉዋ
የንጉሶች ንጉስ
የድኩማን ሞገስ
አምላኬ የምለው
መድሃኔዓለም ነው።
         ቃልኪዳን ተፈራ

➴ ➴ ➴ ➴ ➴
  @MENFESAWItsufoche
1.8K viewsKalkidan, edited  17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 09:49:35
የፅሞና ጊዜ አለክ?


@MENFESAWItsufoche
2.9K viewsKalkidan, edited  06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 20:00:48 እናቴ ስማፀን በስምሽ

ድንግል ማርያም ብዬ ስማፀን በስምሽ
በቅድመ እግዚአብሔር ልመናዬን አድርሽ
እኔ ደካማ ነን ኃጢአቴ የበዛ
እኔ ጎስቋላ ነኝ በደሌ የበዛ
ጊዜዬን ያባከንኩ በዋዛ ፈዛዛ
ጊዜዬን ያባከንኩ በከንቱ በዋዛ
እመብርሃን ስልሽ ፈጥነሽ ድረሽልኝ
ልመናዬን ሰምተሽ ቆመሽ ለምኝልኝ
ኃጢአቴ ቢበዛም ይዣለው አንችን
አስምረሻልና በላዔ ሰብን
አንገቴን ቢያስደፋኝ በዝቶብኝ ኃጢአቴ
ምልጃሽን ፈለኩኝ ድንግል ሆይ እናቴ
ያን ክፉ ጨለማ እንዳላይ አደራ
ድንግል ሆይ ከልይኝ ከዲያብሎስ ጭፍራ
እመብርሃን እያልኩ ቆሜ ከደጅሽ
በብርሃን እጆችሽ እንባዬን አብሽ
አለም አታላይ ነች ወደሷ ተሳብኩኝ
ታማልጅኝ ብዬ አንቺኑ ተራብኩኝ

ከእህተ ማርያም
➴ ➴ ➴ ➴ ➴ ➴
@MENFESAWItsufoche
4.0K viewsKalkidan, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 21:49:53 ዘማሪት ማኅሌት ታደሰ

@MENFESAWItsufoche
4.8K viewsKalkidan, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 19:51:05 *ማን እንዳቺ*
ማን እንደ አንቺ ፈጥኖ ደራሽ
ሰላማዊት ልብን አዳሽ
አረጋጊ እንባን አባሽ፡፡
ማን እንዳቺ አዛኝቱ
የአምላክ እናት ድንግሊቱ
አማላጅ ነሽ የፍጥረቱ
ሰውን መላሽ ከስህተቱ፡፡
ማን እንዳቺ የሚየፅናና
የሚያወጣ ከፈተና
ደግፎ ከቅፎ የሚያቀና
ማን እንዳቺ አስታራቂ
ሀጢአተኛን የማትንቂ
ጆሮ ዳባን የማታወቂ
መልካም ስራሽ አስደናቂ፡፡
ማን እንደ አንቺ መከለያ
ታማኝ እናት መጠለያ
ቀና መንገድ መታመኛ
የንስሀ በር መግቢያ፡፡
ማን እንደ አንቺ ተቆርቋሪ
የማታልፊ የሰው ጥሪ
አቤት ብለሽ አናጋሪ
ሰማያዊት ንግሰት የኛ አብሳሪ፡፡
ማን እንዳቺ ለወደቁት
አዛኝ አፅናኝ ንፁህ እንቁ
ሰው ረስቶአቸው ለተናቁት
በሀዘን መከራ ለወደቁት፡፡
ማን እንደ አንቺ የሚረዳ
የመትሞይ የሁሉን ጓዳ
እባክሽ አውጪን ከዓለም ፍዳ
ሁዋላ ጠፍተን እንዳንጎዳ፡፡
ፀበልሽ ፈዋሽ ያለዋጋ
ለእኛ እኮነሽ ባለ አደራ
እባክሽ አውጪን ከሐጢአት ተራ
እንድንኖር ከአንቺ ጋራ፡፡
መን እንደ አንቺ ያለው ለዛ
ንግግር የሚያዋዛ
በረከትን የሚያበዛ፡፡
ማን እንደ አንቺ ልዩ ስጦታ
አምላክ ያደለን የነፍስ እርካታ
ደስ አለን ዛሬ ዲያብሎስ ሲመታ
መግቢያ መውጪያ አጥቶ ሲሄድ በአንድ አፍታ
ስምሽ ግሩም ነው የህይወት ገበታ፡፡
ማን እንደ አንቺ ታምረኛ
የኔ ላሉሽ ምስጢረኛ
አማላጅ ነሽ እውነተኛ
ዛሬም እባክሽ ነይ ወደኛ
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
✞@MENFESAWItsufoche✞
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
6.3K viewsKalkidan, 16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 10:28:46 ባሕራን

ዐላማዬ ዕቅዴ፥ ቶሎ የምሮጥለት፤
በጉያዬ ይዤ፥ የምታትርለት፤
ለሕይወት እንደሆነ፥ አለዚያም ለሞት፤
ከመንገዴ ቆመህ፥ እስቲ አምጣ በለኝ፤
አንባቢ ነህና፥ ለእኔም አንብብልኝ፤
አንድ አፍታ እፍ ብለህ፥ ክፉን ሰርዝልኝ፤
እኔም ባሕራን ነኝ፥ ከዓለም ያወጣኸኝ፡፡

ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ

@MENFESAWItsufoche
6.4K viewsKalkidan, 07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 09:25:15 #እንኳን_ለሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል_ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ_አደረሰን

          #ጎጆ_ቀለስኩልህ

         (በሰመረ ፍስሃ)

በአውላላ ሜዳ በጠራራ ፀሐይ
ከአስፓልቱ አጠገብ ስኖር ጎዳና ላይ
የበጋውን ንፋስ በዙሪያዬ ከቦኝ
እንደ ዥዋዥዌ ወዲያ ሲወስደኝ፡፡
...................ወዲህ ሲመልሰኝ

ዝናቡ በተራው ጉዴን ተመልክቶ
...................ጉድፌን አፅድቶ
ይወደኝ ይመስል ልብሴን ያጥብልኛል
ጎጆዬን አፈራርሶ በብርድ ይገርፈኛል፡፡

ከዚህ የባሰ ግን ሰዉ ነው 'ሚገርመኝ
በነጋ በጠባ መተንፈሻ ያሳጣኝ፡፡

ስለተናገርኩኝ ማጣት መከፋቴ
የእውነት ስለኖርኩኝ ውሸትን ጠልቼ
አፋቸውን ሞልተው እብድ ነው ይሉኛል
አንዳንዴ ሲያሻቸውም ድሃ ነው ይሉኛል፡፡

የሆነው ሆነና ቅር አላለኝም
አጣሁኝ ብዬም አላማረርኩም
ጌታ እንዳስተማረኝ ለበጎ ነው ብዬ
የማይቻል የለም እኖራሎህ ችዬ፡፡

ይሄውልህ ግን ሚካኤል ሆይ...
የሰው ልጅ ሲሸሸኝ ማንነቴን አይቶ
ሰላምታ ሲነፍገኝ ኑሮዬን ተመልክቶ
አንተ ግን አንተ ነህ የአምላክ መልእክተኛ
ሁሌ  'ምትጠብቀኝ መቼም የማተኛ፡፡
ምንም ሳይገድብህ ከቤቴ ገብተሀል
ድሃዋን ጎጆዬ በፍቅር ጎብኝተሀል፡፡

እናም ሚካኤል ሆይ....
ከኔ እንዳትርቅ ስለሳሳሁልህ
በንፁህ ልቤ ውስጥም ጎጆ ቀለስኩልህ፡፡
❖==✿==❀==✞==❀==✿==❖
@MENFESAWItsufoche
✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧
6.3K viewsKalkidan, 06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 12:51:55 "#ሰማዕቷ #ቅድስት #አርሴማ"

ቅድስት አርሴማ እናታችን ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች፡፡ ቤተሰቦቿ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ ከከበሩ ካህናት ወገን እንደነበሩ የገድሏ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡
ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከቤተሰቦቿ በሚገባ የተማረች፤ የተማረችውንም በተግባር የተረጎመች፤ በጸሎት ሕይወት የምትተጋ ከቅዱሳት አንስት አንዷ ናት፡፡ ይቺ ታላቅ ሰማዕት በነበረችበት ዘመን በአርመን የነገሠው አረማዊ ንጉሥ ድርጣድስ ይባላል፡፡ ይህ ንጉሥ እግዚአብሔር አምላክ በሙሴ ላይ አድሮ “ቀልጠው የተሠሩትን የአማልክት ምስሎች ለአንተ አታድርግ” ብሎ የተናገረውን በመቃወም ለጣዖት የሚሰግድ ፀሐይንም ያመልክ ነበር /ዘጸ.34፥17/፡፡ በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖችን
“እኔ ለማመልከው “አምላክ” ወይም ጣዖት መስገድ አለባችሁ፤ ይህን የማታደርጉ ከሆነ ትእዛዜን ጥሳችኋልና መከራ ይጸናባችኋል”
የሚል ዐዋጅ በማውጣት መከራ ያደርስባቸዋል፡፡
ጨካኙ ንጉሥ ድርጣድስ ይህን ትእዛዙን ባለማክበራቸው መከራና ስቃይ ያደረሰባቸው ክርስቲያኖች ቁጥራቸው 27 ናቸው፡፡ “እኔን የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ ይከተለኝ” ያለውን የእግዚአብሔርን ሕግ የፈጸሙ ክርስቲያኖች እሱ ለሚያመልከው ለጣዖት አንሰግድም በማለታቸው ይደበድባቸውና ግፍና መከራ ያጸናባቸው ጀመር፡፡ ይህን ግፍና መከራ የተመለከተች እናታችን ቅድስት አርሴማ የተጋድሎ ሕይወትን እነሱን አብነት አድርጋ እንደ ጀመረች የሕይወት ታሪኳን የያዘው መጽሐፏ ይነግረናል፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ‘‘ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሳጧችኋል፤ በምኩራቦቻቸውም ይገርፏችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ! ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን ስለ እኔ ወደ ገዢዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ… አትጨነቁ! በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ የምትናገሩት እናንተ አይደላችሁም” /ማቴ.10፥16-20/፡፡ ብሎ የተናገረውን በማሰብ ቅድስት አርሴማ በሃያ ዓመቷ የንጉሡን እኩይ ግብሩን በመንቀፍ ስለ ክርስቶስ ከሚሰቃዩ ሰማዕታት ወገኖቿ ጋር በመሆን ስለ እግዚአብሔር አምላክነት ትመሰክር ነበር፡፡
የንጉሡም አገልጋይ በደም ግባቷና በንግግሯ ማማር ተደንቆ በዚች በፈቃዷ ሰማዕትነትን ልትቀበል በወደደች ሴት ምንም ሊያደርግባት ስላልወደደ ወደ ንጉሡ ወደ ድርጣድስ ከሃያ ሰባቱ ክርስቲያኖች ጋር ወሰዳት፡፡ ንጉሡም ብዙ የተነገረላትን ወጣት ሲያይ በውበቷና በንግግሯ ተማርኮ ለዓለማዊ ደስታውና ፍላጎቱ ተመኛት፡፡ ሚስት ትሆነው ዘንድ አብዝቶ ተማጸናት፡፡ እጅ መንሻና ማታለየ የዚህን ዓለም ወርቅና ብር አቀረበላት፡፡ ቅድስት አርሴማ ግን መልክ ረጋፊ፤ የዚህ ዓለም ሀብትም ከንቱ እንደሆነ ስለምታውቅ በዓላማዋ ጸናች! ንጉሡንም ‘‘እኔ የንጉሥ የክርስቶስ ሙሽራ እንጂ የዚህን ዓለም አላፊ ጠፊ የሆነውን ገንዘብና ደስታ የምሻ አይደለሁም፡፡’’ በማለት መለሰችለት፡፡
ንጉሡም ይህንን ከእርሷ በመስማቱ እጅግ ተቆጣ፤ እግዚአብሔር አምላኳን በማመኗ ተበሳጨ፤ አሽከሮቹንም ጠርቶ በቤተ መንግሥቱ የታሠሩትን አንበሶች እንዲለቀቅባቸው አዘዘ፡፡ አንበሶቹ ግን ይደሰቱ ነበር፡፡ በኋላም ፊታቸውን ወደ ንጉሡና አገልጋዮቹ በማዞር ሩጠው እስኪደበቁ ድረስ አሳደዷቸው፡፡
በቅድስት አርሴማ የገድል መጽሐፍ ላይ የሰፈረው ታሪክ በተመሳሳይ መልኩ በትንቢተ ዳንኤል ላይ ሲፈጸም እናያለን፡፡ ነቢዩ ዳንኤል ያለ በደሉ በክፉ ሰዎች ምክር የተራቡ አንበሶች ወዳሉበት ጉድጓድ በተጣለ ጊዜ አንበሶቹ ፈጽሞ ጉዳት አላደረሱበትም፣ እንኳን ሊበሉት የእግሩን ጥፍር እየላሱ ተገዝተውለታል፡፡ “በነጋውም ንጉሡ ማልዶ ተነሣ ፈጥኖም ወደ አንበሶቹ ጉድጓድም ወደ ዳንኤል በቀረበ ጊዜ በኃዘን ቃል ጠራው፤ ንጉሡም ተናገረ ዳንኤልንም፡- የሕያው አምላክ ባሪያ ዳንኤል ሆይ ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ከአንበሶች ያድንህ ዘንድ ችሎአልን? አለው፡፡ ዳንኤልም ንጉሡን ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ንገሥ በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና በአንተም ፊት ደግሞ ንጉሥ ሆይ አልበደልሁምና አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ፤ እነርሱም አልጎዱኝም አለው” የዳንኤል ከሳሾች ግን “በአንበሶች ጉድጓድ ጣሏቸው፤ ወደ ጉድጓዱም መጨረሻ ሳይደርሱ አንበሶች ያዟቸው ዐጥንታቸውንም ሁሉ ሰባበሩ” /ዳን. 6፥19-25/፡፡
ንጉሡ የክርስቲያኖቹ በሰማዕትነት መጽናት ስለነደደው በረሃብ እንዲያልቁ እንዲታሠሩ አዘዘ፡፡ እግዚአብሔርም በአምስተኛው ቀን በብርሃን ቤቱን ሞልቶት የሚበሉትን በመሶብ የሚጠጡትን በጽዋ ከሰማይ አወረደላቸው፡፡ንጉሡም ይህንን በማየቱ ከዚያ አውጥቶ በእሳት ውስጥም አስገባቸው፡፡ ሠለስቱ ደቂቅን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ ከእሳት ያወጣቸው እግዚአብሔር አምላክ እነርሱንም አዳናቸው፡፡ የክርስቲያኖቹ የእምነት ጽናት የሚደንቅ ስለነበር ንጉሡ አማካሪዎቹ ጠርቶ
“ምን ብናደርግ ይሻላል?” የሚል ምክር ጠይቆ ሁሉንም በሰይፍ ተሰይፈው እንዲሞቱ ስምምነት ላይ ይደርሳል፡፡
እያንዳንዳቸውን ተራ በተራ ሲሰይፋቸው ቅድስት አርሴማ ለሚሰየፉት ሁሉ የድል አክሊል ከሰማይ ሲወርድላቸው ትመለከት ስለነበር የእርሷን ተራ በጉጉት ትጠብቀው ነበር፡፡ በሰማዕትነት አምላኳ እንዲያጸናት እየጸለየች “አይዟችሁ ጽኑ! የዚህ ዓለም መከራ አያሰቅቃችሁ! አትፍሩ” እያለች ታጽናናቸው ነበር፡፡
ንጉሡም ሌሎቹን አሰይፎ ሲያበቃ ወደሷ ዞሮ በቁጣ እየጮኸ “አንቺን እንደ ባልንጀሮችሽ በቀላሉ አልገልሽም! ስቃይ አጸናብሻለሁ” ብሎ ለአገልጋዮቹ ትእዛዝ በመስጠት ዓይኗን አስወጥቶ በእጇ እንድትይዝ አደረጋት፤ ጡቷን ቆረጣል፤ በኋላም አንገቷን በሰይፍ በመቅላት መስከረም 29 ቀን በሰማዕትነት እንድታልፍ አድረጋት፡፡
ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ
‘‘ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ’’ እንዲል /መዝ. 8፥3/፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‘‘በእኔ ስም አምነሽ የዚህ ዓለም ተድላና ደስታ ሳያታልልሽ አንገትሽን ለሰይፍ ሰጥተሽ ተሰይፈሻል፤ የሰማዕትነት ተጋድሎ ፈጽመሻልና ስምሽን የጠራ፤ በዓልሽን ያከበረ፤ ዝክርሽን ያዘከረ፤ ገድልሽን የጻፈና ያጻፈ፤ የሰማና ያሰማም እስከ 12 ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ’’ ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡
የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከት ጸሎትና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይኑር፡፡ አሜን! ! !

"አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዛ ዓለም ፡ ወከዓዉ ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ፡ ወተዐገሱ ሞተ መሪረ በእንተ መንግሥተ ሰማያት።"

በዳ/ን በሃይሉ ተፈራ

@MENFESAWItsufoche
509 viewsKalkidan, 09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 12:51:55 * አርሴማ *

አርሴማ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት(፪)
ሞገስ አግኝተሻል በክርስቶስ ፊት

ታምርሽ ልዩ ነው....አርሴማ
ገድልሽአስደናቂ .....አርሴማ
ስምሽ ብርሃን ነው....አርሴማ
ማለዳ ፈንጣቂ ....አርሴማ

አዝ======

ስምሽን እየጠራ...አርሴማ
ጠግቧል የተራበው...አርሴማ
ምስኪኑም ዘመረ.....አርሴማ
ባንቺ አልፎ መከራው....አርሴማ

አዝ=====

ፅኑ ነው ኪዳንሽ....አርሴማ
የተሰጠሽ ከአምላክ....አርሴማ
በአይኔ አይቻለው...አርሴማ
ጠላት ሲንበረከክ....አርሴማ

አዝ=======

ዓለም ይስማው ዛሬ....አርሴማ
ዜና ተጋድሎሽን.....አርሴማ
ይገረም ይደነቅ....አርሴማ
ይመስክር ዝናሽን....አርሴማ

@MENFESAWItsufoche
456 viewsKalkidan, 09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 12:53:07 ፆም እንዴት ነው?

ከእለታት አንድ ቀን አንድ ወጣት ወደ ነፍስ አባቱ ይሄድና ሰላም ካላቸው በኃላ
ልጄ መንፈሳዊ ሂይወት እንዴት ነው?
ወጣቱም መልሶ በጣም ጥሩ ነው አባ።
ደስ ብሏቸው ጎሽ ልጄ በርታ እና ፆሙስ እንዴት ይዞሃል?
ወጣቱም አይ አባቴ ፆም እንኳን እየፆምኩ አይደለም።
ለምን ልጄ ምን ነካህ?
ወጣቱም አይ አባቴ ፆም ከገባ በኋላ ፍርጅ ውስጥ የነበረ ስጋ ወጥ ረሰቸው በላሁት ከዛም ያው አንዴ ሽርያለሁ ብየ አልፆምም።
የነፍስ አባቱም በጣም አዘኑና እህህህ ልጄ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?
ወጣቱም እሺ ይጠይቁኝ
እሳት አየሞክ እያለህ ሳታስበው በድንገት እግርህን ወደ እሳቱ ቢገባና እግርህ ቢቃጠል አንዴ ተቃጥያለው ብለህ ሳታወጣው ዝም ትላለህ ወይስ ታወጣዋለህ?
ወጣቱም በድንጋጤ እንዴ አባቴ ለምን ዝም እላለው ቶሎ ብዬ አውጥቼ በፍጥነት ወደ ህክምና ሄጄ እታከመዋለው።
ጥሩ ብለሃል ልጄ ፆምም አንዴ በልቻለው እያልክ መብላትህ ተገቢ አይደለም። ሃጥያትም ነው ልጄ ልክ ከእሳቱ እግርህን ቶሎ ብለህ አውጥተህ ወደ ህክምና እንደ ሄድክ ነፍስም ከቁስሏ ቶሎ ብለህ ከስህተት ተመልሰህ በፆም በጸሎት ማከም ይገባሃል ልጄ።በስህተት የሻርከውን ንስሐ ይሰጥህና የቀረውን መፆም ነው የሚገባህ ልጄ በስህተት ላይ ስህተት እየጨመርክ መንፈሳዊ ህይወትህ ማጥፋት የለብህም በማለት ቀኖና ሰጥተው ፆሙን እንዲፆም ነግረው አሰናበቱት።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
መልዕክት፦አብዛኞቻችን አንዴ ፆሙን ሽርያለው በሃጢአት ወድቅያለው ገና ወጣት ነኝ ነገ እሳሳታለው እያልን ብዙ ምክንያት እየደረደረን መንፈሳዊ ሂይወታችንን ረስተን በዝሙት በመጠጥ በጭፈራ በተለያዩ ወጥመድ ተይን ወጥተን የጠፋን ስንቶቻችን ነን ቤት ይቁጠረን። ቶሎ ብለን ዲያብሎስን ካልነቃንበት ህይወታችንን በማበላሸት ያጠፋናል።አንዴ ተሳስቻለው ብለን ሁሌም መሳሳት የለብንም በንስሃ ተመልሰን መልካሙን መንፈሳዊ ህይወታችንን እናጠናክር እንዲ እያሉ የሚገስጹ ደግ አባቶቻችንን ያብዛልን።
በንስሐ እንመለስ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
፨ከተስፋ ሚካኤል ሃይለ ማርያም

@MENFESAWItsufoche
3.6K viewsKalkidan, 09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ