Get Mystery Box with random crypto!

🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
የሰርጥ አድራሻ: @menfesawitsufoche
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.03K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ትምህርታዊ ጹሑፎችን፣ ብሂለ አበው፣ ከመጽሐፍት ዓለም እና ሌሎችም ''መንፍሳዊ ሥነ-ጹሑፎችን'' ያገኛሉ።
.
.
.
ሃሳብ አስተያየታቹን ወይም ቻናሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ስነ-ጹሑፎች ለመደገፍ @kal002 ላይ አድርሱን።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-07 12:09:45 “ፆም የፀሎት ምክንያት ናት፤ የፀጋ ዕንብ መገኛ ናት፤ አርምሞን የምታስተምር ናት፤ ለበጎ ስራ ሁሉ ታነቃቃለች፤ የፀዋሚ ስጋው ምንጣፉን አንጥፎ ሌሊቱን ሁሉ ተኝቶ ማደር አይቻለውም በምን ጎኑ ይተኛዋል? ሰው አብዝቶ በፆመ ያህል በዚህ መጠን በትህትና ሁኖ እያለቀሰ ይፀልያል፤ ፀሎታት ከልቡናው ይታሰባሉ አንድም ፀሎተ ልብ ይሰጠዋል፤ በፊቱ የትእግስት ምልክት ይታያል በሃጢአቱ ያዝናል ክፉ ህሊና ይርቅለታል የበጎ ነገር መገኛ መከማቻ በምትሆን በፆም ይኖራልና፤ ፆምን የናቀ ያቃለለ ሰው በጎውን ነገር ሁሉ ከራሱ አራቀ፡፡”
ማር ይስሃቅ።
መልካም የፆም ጊዜ ይሁንልን
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
@MENFESAWItsufoche
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
3.2K viewsKalkidan, 09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 12:05:58 መልካም የሐዋሪያት ፆም እና ፆመ ድህነት ይሁንልን አሜን!

@MENFESAWItsufoche
2.7K viewsKalkidan, 09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 07:31:49

@MENFESAWItsufoche
2.9K viewsKalkidan, 04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 19:27:16

@MENFESAWItsufoche
3.2K viewsKalkidan, 16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 13:17:45 ዕርገት

በዚህ ዕለት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ሆነ።

“እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እየአያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” የተባለበት ታለቅ ቀን ነውና፡፡

ዛሬ ዕርገት ነውና “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ”

እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡

የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ ከሰማየ ሰማያት የወረደው ከድንግል ማርያም የተወለደው ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ያረገው ነው፡፡

ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡

በአባቱ ዕቅፍ የነበረው ፤ በጲላጦስ የተፈረደበትም ኢየሱስ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡

በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው፤ በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም ክርስቶስ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡

ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ ዛሬ ያረገው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጡቷን ያጠባችው ያዘለችው እሹሩሩ ብላ ጉንጮቹን የሳመችው እሱ ዛሬ ያረገው እንጂ ሌላ አይደለም።

በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡

በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡

እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡

ነቢያት በትንቢት መነፅር እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሐብተ ፈውስና ባለ ሙሉ ስልጣንን ያደረጋቸው፥

“አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ እየታያቸው ዓረገ፡፡

ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ነው፡፡

መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ኃጢአታችንን የሚደመስስ፣ ሳንለምነው የልባችንን ሐሳብ የሚፈፅም እርሱ ነው፡፡

ስለርሱ ምድር ብራና ብትሆን ዛፎች ብዕር ቢሆኑ ባሕር ቀለም ብትሆን ፅፈን አንጨርሰው እንደው ዕፁብ ብቻ።

ለእርሱ ከቸር አባቱና ሕይወት ከሆነ ወመንፈስ ቅዱስ ጋር ምስጋና ስግደት አምልኮት ይገባል ለዘላለሙ አሜን።

@MENFESAWItsufoche
5.4K viewsKalkidan, 10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 13:17:45
እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ በስላም አደርሳቹ አደርሰን!!!

@MENFESAWItsufoche
3.6K viewsKalkidan, 10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 14:09:04 "የናቡቴ እርስት"



በላ * *ልበልሃ
ክፍል፫


@MENFESAWItsufoche
5.4K viewsKalkidan, 11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 14:08:44 "የናቡቴ እርስት"



በላ * *ልበልሃ
ክፍል፪


@MENFESAWItsufoche
4.4K viewsKalkidan, 11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 14:08:25 "የናቡቴ እርስት"



በላ * *ልበልሃ
ክፍል፩


@MENFESAWItsufoche
4.3K viewsKalkidan, 11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 23:46:29 የ ምስራች ለ ተዋህዶ ልጆች በሙሉ!

መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች መማር ይፈልጋሉ ?

 
የ ምስራች ለ ተዋህዶ ልጆች በሙሉ!

መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች መማር ይፈልጋሉ ?

 
እምቢልታ መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች  ማሰልጠኛ  ተቋም 
➜  በገ ና
➜  ክራር
➜ መሰንቆ
➜ ዋሽንት

   በሚፈልጉት ቀን እና ሰዓት  እንዲሁም በግል ቤት ለቤት  እናስተምራለን ! በተጭማሪ  ጥራት ያላቸው  የበገና , የክራር , መሰንቆ እንሸጣለን እናከፋፍላለን የክራር የበገና የመሰንቆ ቦርሳ እኛ ጋር ያገኛሉ


አድራሻችን  -  ጀሞ 1 ሩት የገበያ ማዕከል
                            
         Tel.  0995975237
                     
                     

.
366 viewsመንፈሳዊ 3k, 20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ