Get Mystery Box with random crypto!

🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
የሰርጥ አድራሻ: @menfesawitsufoche
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.03K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ትምህርታዊ ጹሑፎችን፣ ብሂለ አበው፣ ከመጽሐፍት ዓለም እና ሌሎችም ''መንፍሳዊ ሥነ-ጹሑፎችን'' ያገኛሉ።
.
.
.
ሃሳብ አስተያየታቹን ወይም ቻናሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ስነ-ጹሑፎች ለመደገፍ @kal002 ላይ አድርሱን።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-20 11:25:39 እሱ ማነው???


ሀይማኖቱን ከከሀዲ ዮዲት ጉዲት መሳይ
የሚከላከለው መንጋን ተመለስ ባይ
ማርያን- ጠንቋዩን ለአምላክ ያስገዛ
የወንጌል ገበሬ የኢትዮጵያ መዓዛ
እኮ እርሱ ማነው??
የትሩፋት መምህር የእግዚአርያ በረከት
የክርስቶስ ወታደር የብዙዎች አባት
ኢትዮጵያን ያበራት በወንጌል አዝመራ
ባለ ብዙ ሰብል በመኸር ጎተራ
በሰባኬ ክረምት በተዓምራት ፀደይ
የበረከት አባት በፍሬው የሚለይ
እኮ እርሱ ማነው??
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ
ለምስጋና ሚቆም ከመንበረ ስሉስ
እንደ መላእክቱ ክንፍ የተሸለመ
እርሱስ ባህታዊው ተክለ ሃይማኖት ነው፡፡
"" እንኳን ለአባታችን ለፃዲቁ ለአቡነ ተክለሀይማኖት በዓል በሠላም አደረሳችሁ፡፡""
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
✞@MENFESAWItsufoche✞
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
1.1K viewsKalkidan, 08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 11:25:39 አባ አባ



አባ አባ ተክለሃይማኖት አቡዬ/2/
በለኒ በለኒ ወልድዬ /2/
አዝማች
አባ አባ....እንኳን ሰው ምድሪቱ
አባ አባ....ፆም አያሳድርም
አባ አባ...አምላከ ተክልዬ
አባ አባ...ብዬ አፍሬ አላውቅም
አባ አባ... ምድራዊ መላክ ነህ
አባ አባ...የኢትሳ አንበሳ
አባ አባ...ለደብረ ሊባኖስ
አባ አባ...አንተ ነህ ሞገሷ
አዝማች
አባ አባ...ስማኒ ብያለሁ
አባ አባ...ሳለ በሰማይ
አባ አባ...ከኪሩቤል ተርታ
አባ አባ...ሆነህ ስትታይ
አባ አባ...ስምህም ሲጠራ
አባ አባ...ገድልህ ሲነገር
አባ አባ...እጹብ ድንቅ ያሰኛል
አባ አባ...የተሰጠህ ክብር
አዝማች
አባ አባ...አባቴ እልሃለሁ
አባ አባ ...ልጄ ሆይ በለኝ
አባ አባ...የአባትና የልጅ
አባ አባ...ፍቅርህ ይጽናልኝ
አባ አባ...ንፍሮ ውሃ ጠጥቼ
አባ አባ...ታምር አይቻለሁ
አባ አባ...እባብ እና ጊንጡን
አባ አባ...ተረማምጃለሁ
አዝማች
አባ አባ... እለት በእለት ሂጄ
አባ አባ... ደጅ ስጠናው
አባ አባ... ይሰማል ተክልዬ
አባ አባ... ዛሬም ህያው ነው
አባ አባ... እንቆቅልሽ ፈቶ
አባ አባ... ደስ አሰኝቶኛል
አባ አባ... የተክለሃይማኖት
አባ አባ... ብራኬው ደርሶኛል

@MENFESAWItsufoche
1.0K viewsKalkidan, 08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 16:00:07
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ
1.5K viewsKalkidan, 13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 16:00:07 *ጽናጽል*
ከብርና ከነሐስ ከሌላም ብረት የሚሰራ የዜማ እቃ ነው፡፡
እንዲሿሿም የብረት ቀጠል ይደረግበታል አገልግሎቱም ለእግዚአብሔር ክብር ይዘመርበታል፤ ጸናጽል ከከበሮ ጋር አብሮ የሚሄድ የዜማ ዕቃ ነው፡፡
ምሥጢሩ፦ በግራና ቀኝ ያለው ዓምድ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን ምሳሌ ነው፡፡
- በሁለቱ ዓምዶች መሐል ያሉት ሁለቱ ቀጫጭን ዘንጎች ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ መላዕክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያያት መሰላል ምሳሌ ነው፡፡
በዘንጎቹ ላይ ያሉት የብረት ቅጠሎች ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በመሰላል ላይ ሲወጡ ሲወርዱ ያያቸው መላእክት ምሳሌ ነው፡፡
በሌላ በኩል የብረት ቀጠሎቹ ብዛት ቢያንስ አምስት ቢበዛ ሰባት ይሆናል፡፡ አምስት ሲሆን የአምስቱ አዕማደ ምሥጢር ምሳሌ ሲሆን ሰባት ሲሆን ደግሞ የሰባቱ ሰማያት ምሳሌ ነው፡፡
የብረት ቀጠሎቹ በመጀመሪያ ዘንግ ላይ ሁለት ይሆናሉ፣ ይህም ወልድ ሁለት ልደታት እንዳሉት ለማመልከት ነው፡፡ ቅድመዓለም ያለ እናት ከአብ ድህር አላም ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት መወለዱን ያሳየናል፡፡
ድምጹ ያማርና መልካም መሆኑ በመላዕክት ዜማ ይመሰላል፡፡
ወዲያና ወዲህ መባሉ ጌታችን በአይሁድ እጅ የመንገላታቱ ምሳሌ ነው፡፡
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
✞@MENFESAWItsufoche✞
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
1.5K viewsKalkidan, 13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 15:59:24 ያሬድ ማኅሌታይ







ዘማሪት ማኅሌት ታደሠ



@MENFESAWItsufoche
1.6K viewsKalkidan, 12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 11:18:29 ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
@MENFESAWItsufoche
2.0K viewsKalkidan, 08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 13:39:04 አርሴማ ቅድስት


ዘማሪት ማኅሌት ታደሰ

@MENFESAWItsufoche
3.7K viewsKalkidan, 10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 07:48:13 እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!!
ግንቦት ፩


@MENFESAWItsufoche
1.9K viewsKalkidan, 04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 07:45:37
ዓለሙ ከነውበቱ
ውበትም ከነእውነቱ
እንዲኖር

አዳም ወደ ልጅነት
ሰውነት እንዲሆን ገነት

ብዙዎች ብዙ ተመኙ
እነሆ
ነብያት ትምክታቸውን
መላእክት እህት አገኙ፡፡
"ማርያምን"
ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን

@MENFESAWItsufoche
1.8K viewsKalkidan, 04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 14:07:09 @MENFESAWIAtsufoche
3.9K viewsKalkidan, edited  11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ