Get Mystery Box with random crypto!

🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
የሰርጥ አድራሻ: @menfesawitsufoche
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.03K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ትምህርታዊ ጹሑፎችን፣ ብሂለ አበው፣ ከመጽሐፍት ዓለም እና ሌሎችም ''መንፍሳዊ ሥነ-ጹሑፎችን'' ያገኛሉ።
.
.
.
ሃሳብ አስተያየታቹን ወይም ቻናሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ስነ-ጹሑፎች ለመደገፍ @kal002 ላይ አድርሱን።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2022-07-03 11:49:41 + ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንዲህ አለ +

"በምሰብክበት ጊዜ ስታጨበጭቡልኝ ሰው እንደመሆኔ በዚያ ቅጽበት ደስታና መደነቅ ይሰማኛል:: ወደ ቤቴ ሔጄ ያጨበጨቡልኝ ሰዎች ምንም ጥቅም እንዳላገኙ ሳስብ ግን ንግግሬ ሁሉ በከንቱ እንደቀረ ይሰማኛል:: ስለዚህ ማጨብጨባችሁን የሚከለክልና ዝም ብላችሁ እንድትሰሙኝ ብቻ የሚያደርግ ሕግ ስለማስቀመጥ አስባለሁ"
(On His Message 80)

“ቤት ውስጥ የእንግዳ ማረፊያ ቤት ይኑርህ:: አልጋ አዘጋጅ:: ጠረጴዛና መቅረዝም ይኑረው:: ክርስቶስ ሊመጣና ሊያርፍበት የሚችልበት ክፍል አዘጋጅና "ይህ የክርስቶስ ክፍል ነው" በል:: ምድር ቤት ያለ ትንሽ ክፍልም ቢሆን እሱ አይንቀውም:: ዕርቃኑን የሆነው እንግዳ የሚፈልገው መጠለያ ብቻ ነው"
(On Acts Homily 40.2)

“ለሞቱት ብቻ አናልቅስ:: በቆሙት ብቻም አንደሰት::
ታዲያ ምን እናድርግ? ለኃጢአተኞች በሞቱ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በቁማቸውም እናልቅስ:: ስለ ጻድቃን ደግሞ በቁማቸው ብቻ ሳይሆን በሞቱም ጊዜ ደስ ይበለን::
ምክንያቱም ኃጢአተኞች ቆመውም ሞተዋል:: ጻድቃን ግን ሞተውም ሕያዋን ናቸው::
(On Phil. 3)

"ጴጥሮስ አለቀሰ:: ማልቀስ ብቻ ሳይሆን ምርር ብሎ አለቀሰ:: ከዓይኑ በፈሰሰው ዕንባ ድጋሚ ተጠመቀ:: አምርሮ በማልቀሱም በዕንባው ኃጢአቱን አጠበ:: አንተም እንዲሁ አድርግ" (Paent 3.4)

“ንብ ከሌሎች እንስሳት ሁሉ ትከበራለች:: የምትከበረው ታታሪ ሠራተኛ በመሆንዋ ሳይሆን የምትሠራው ለሌሎች በመትረፉ ነው"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 12 2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


@MENFESAWItsufoche
5.4K viewsKalkidan, 08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 19:30:14 ፨እንኳን ደስ አላቹ፨

እውቀት እና ጥበብ ለማወቅ ሽታቹ
በእየድሜያቹ ልክ እጅጉን ለፍታቹ
ፈተና ፕሮፖዛል ፖሮጀክት አሳይመንት
ሪፖርትና ሪሰርች ስትሰሩ በትጋት
በቀራቹ ጊዜም ሳትሰላቹ ምንም
በስግደት በፀሎት ሱባኤና ፆም
ዘውትር የጠናቹ ወደ ፈጣሪያቹ
በአገልግሎት ጭምር እጅግ የተጋቹ
የድካማቹን ፍሬ አምላክ ቆጥሯልና
እንኳን ደስ አላቹ አልኩኝ እንደገና።
ከቃልኪዳን ተፈራ
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
@MENFESAWItsufoche
4.3K viewsKalkidan, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 19:30:14 ፨እንኳን ለዚህ ቀን አበቃቹ፨
እንኳን ለዚህ ቀን አበቃቹ/3/
በእግዚአብሔር ቤት መረቅናቹ።


አዝ
የድካም ውጤት ነው የመስቀሉ ፍቅር
እጅግ የሚያተጋ ለተሻለው ነገር
እሾህ ደፍቶ ጌታ ዘውዱን ጭኖብናል
የንጉስ ልጆች ነን ማን ይቃወመናል።

አዝ
ለፍተን ካሳረፍከን ሰርተን ከባረከን
እኛም ለአምላካችን የምንለው አለን
ቀልጧል እንደ ቅባት ፍቅርክ በውስጣችን
የማይታጠብ ነው አንተነህ ወዛችን

አዝ
መዳፍህ ሲያርፍብን እንለወጣለን
ለውርደት ሲያስቡን ለክብር እንሆናለን
ገና ነው ፍፃሜው ገና ነው አጽናፉ
እንነበባለን ሲገለጥ መፅሐፉ

አዝ
በለቅሶ የሚዘሩ በደስታ ያጭዳሉ
ትንሽ ሆነው ወጥተው እጅግ ይበዛሉ
የተከፈተ በር ስለተሰጣቹ
በማይሞተው አምላክ ኩሩ በአምላካቹ።

ለ2011ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላቹ እንኳን እግዚአብሔር አምላክ ለዚህ ቀን አበቃቹ እንላለን!!!

@MENFESAWItsufoche
4.2K viewsKalkidan, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 11:53:07
4.1K viewsKalkidan, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 20:32:42 ​​ምዕራፈ ቅዱሳን


ምዕራፈ ቅዱሳን ተክልዬ አባቴ
እለምንሃለሁ እስከለተ ሞቴ
በሄድኩበት ሁሉ ጻድቁ ምራኝ
የዚህ አለም ወጥመድ እንዳያጠምደኝ

አዝ#

ተራራን የሚያፈርስ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
ሃይማኖትን ይዞ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
ወንጌልን የዘራ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
መስቀል ተመርኩዞ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
ጣኦት አጋንንቱ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
ስፍራውን ለቀቀ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
በጨለማ ያለ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
አምላኩን አወቀ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ

አዝ#

የዳሞቱ ንጉስ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
ተንበረከከልህ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
ዛፉ ተፈንቅሎ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
ወድቆ ሰገደልህ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
ተክልዬ የሚልህ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
አምላክህንአምኖ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
ሁሉም ይመለሳል ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
ተፈውሶ ድኖ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ

አዝ#

ሚካኤል ከፊቱ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
ከኋላው ቆመለት ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
ሰይጣንን አሰረው ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
በሰማዩ ክህነት ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
እንደ ኪሩብ መልአክ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
በክንፉ በረረ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
የእግዚአብሔርን ክብር ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
እየመስከረ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ

አዝ#

ተክልዬ እልሃለሁ ፨፨፨ታላቅ እምነት አለህ
ሳልደክም ተግቼ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
አማልደኝ እላለሁ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
እጆቼን ዘርግቼ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
ከሃገሬ ብወጣ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
እርቄ ብኖርም ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
አምላከ ተክልዬ ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ
እልሀለሁ ዛሬም ፨፨፨ ታላቅ እምነት አለህ

➴ ➴ ➴ ➴ ➴
@MENFESAWItsufoche
4.5K viewsKalkidan, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 20:31:37 የፃድቁ የአቡነ ተክለሃይማኖት ተዓምር






ዲ/ን አቤል

@MENFESAWItsufoche
4.1K viewsKalkidan, 17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 08:59:37 #ይፍቱኝ_አባ

"የንስሀ መጀመርያ እየሰሩ ካሉት ኃጥያት መለየት ነው"
ፈገግ ብለው ትምህርት የሚያገኙበት ድንቅ ወግ


@ortodoxmezmur

@MENFESAWItsufoche

5.3K viewsKalkidan, 05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 14:03:24 ፨ግልጽ ነው ሚዛኑ፨


እንኳን ለመላዐኩ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በሰላም አደረሳቹ!

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
@MENFESAWItsufoche
6.2K viewsKalkidan, 11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 17:06:24 ፨የአፎምያ አጽናኝ፨





ከቀደመው መንገድ ከላይ በተሰጠን
ዕድሳት በማያውቅ በማይሻርው ዘመን
በድንቅ ምስክሮች ብርሃን በሆኑን
እንድንጓዝ ሁሌም የአፎምያ አጽናኝ
ጠላት ቀስቱን ሰብቆ ሊያጠፋን ሲመጣ
እንደ ቋጥኝ ከቦን የዚህ አለም ጣጣ
በከንቱ ስንሮጥ ኋላ እንዳንቀጣ
አማልደን መላኩ የነፍሳችን ዕጣ
የሁሉንም ጸሎት ከአምላክ የምታደርስ
ፍቅር እና ርህራሄ በሰው የምታለብስ
ልክ እንደ ትላንቱ ዛሬም ፈጥነህ ድረስ
በአንደበትህ ፍሬ ውስጣችን ይታደስ
የዳንኤል አጽናኝ የአፎምያ ረዳት
በህይወት የቀየርክ የባህራንን ጽሕፈት
በለአምን የታደክ ከእርግማን መቅጸፍት
እኛንም ጠብቀን ከምናየው መአት
የምጽአት ዋዜማ ለመሆኑ ምስክር
በመጽሐፍ ያለው ቃሉ ሲተገበር
መተማመን ጠፍቶ ሲቀዘቅዝ ፍቅር
በወንጌሉ አንድምታ ልባችን ይታጠር
ይቅርታ ምህርቱ ይምጣልን የእግዚአብሔር
እረኛ እንደሌለው ሲጨነቅ ትውልዱ
ተመሳስሎ ቆሞ ሲያስት በመንገዱ
ግራ በመጋት ስንቶቹ ተጎዱ
በየዋህነታቸው አብረው ተሰደዱ
ዘንዶ አፉን ከፍቶ ነፍሳት እንዳይወጥ
የተዋህዶን መዝገብ እውነቱን ለመግለጥ
የቆመውን ሁሉ በአውደ ምህረቱ
ያበረታን አምላክ እሰከ ምጽአቱ።


እንኳን ለሊቀመላአኩ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ የንግስ ክብር በዓል በሰላም አደርሳቹ አደረሰን የመላአኩ ረድኤት እና ምልጃው አይለየን አሜን!

✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
@MENFESAWItsufoche
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
9.6K viewsKalkidan, 14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ