Get Mystery Box with random crypto!

🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
የሰርጥ አድራሻ: @menfesawitsufoche
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.03K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ትምህርታዊ ጹሑፎችን፣ ብሂለ አበው፣ ከመጽሐፍት ዓለም እና ሌሎችም ''መንፍሳዊ ሥነ-ጹሑፎችን'' ያገኛሉ።
.
.
.
ሃሳብ አስተያየታቹን ወይም ቻናሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ስነ-ጹሑፎች ለመደገፍ @kal002 ላይ አድርሱን።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-11 23:25:28 ለክርስትና , ለሰርግ የዲኮር ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋሉ ?


ለ ሰርግ                            ለ ክርስትና
ለ ልደት                            ለ ቀለበት
ለ ገዓት                             ለ ሽምግልና
ለ ተማሪዎች ምረቃ           ለ ልጆች ልደት
ለ ቤት ምርቃት                   ለ ሆቴል ምረቃ
ለ ስብሰባ አዳራሾች          ለ ቤተሰብ ኘሮግራሞች
ለ ሰርግ ለመኪና ዲኮር
በ ቤተክርስቲያን ስርዓት ለሚፈፀሙ ሰርጎች እና ኘሮግራሞች

ለተለያዮ ዝግጅቶችም ጭምር የተለያዮ የዲኮሪሽን ስራዎችን እንሰራለን እንዲሁም የተለያዮ የዲኮር እቃዎችን እናቀርባለን !
       

     
              ይህን ይጫኑት  ...  ይህን ይጫኑት

█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█


Tel .   +251961064953
                 +251703504953
.
125 viewsመንፈሳዊ 3k, 20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 10:57:11 13 ሕማማት መስቀል
።።።።።። በግጥም ።።።።።።
በሃበታሙ
❶ኛ ➬ ወደ ዋላ ምታስር (ተስሮ ድሕረት)
አምላክ ሆይ ስለእኛ
ወደዋላ ተስረ የፊጢኝ
በእፀ መስቀል መተክ
ሲኦልን ወርደ እኛን ለትጎበኝ
ስለ በደላችን ታሰርክ
ከታሰርንበት እኛን ለትፈታን
ስለኛ ታሰርክ በገመድ
ቤዛችን ነህ ለኛ ለሃጣን
አዳምን ከአፈር ከመሬት
የሰሩት ቅዱሱ እጆች
በገመድ ወደዋላ ታሰሩ
በጲላጦስ ጭፍሮች

❷ኛ ➬ በገመድ መሳብ (ተስቦ በሃብል )
አምላክን በገመድ ጎተቱት
አይሁዶች በመሬት ላይ
በሰዎችም ፊት ተዋረደ
እኛን ሊያወጣን ከፍታ ላይ
ሁሉንም በሁሉ ሁሉን የፈጠረ
የሰማይና የምድር ጌታ
አለም እንደ ወንበዴ የዘችው
ለታሰቀየው በገመድ ግታ
ችሎታ ሃይል ትግስቱ
የእርሱስ በእውነት ይደንቃል
እንደ እየሱስ ኤልሻዳይ የለ
የትስ ይገኛል ከወዴትስ ይመጣል

❸ኛ ➫ በምድር ላይ መውደቅ (ወዲቅ ውስተ ምድር )
ሰማይን እንደ ቀመር
የሰቀለ የቆመ አምላክ
ምድሩንም በውሃ ላይ ያፀና
ሁሉን ያቆመ ሁሉንም በልክ
ጭፍሮች ገፍተው ሲጥሉ
በግንባር ምድር ላይ
እንደ አምላክነቱ ሁሉን ቻለ
እየሱስ አምላክ ኤልሻዳይ
የእውራን የድሆች አባት
የወደቁትን የጠፉትን ማይረሳ
አይዞህ የሚለው ጠፋ
ከተጣለበት ደግፎ ሚያነሳ
በግንባሩ ወድቆ ተደፋ
አቅም እንደሌላችው እንደ ደካሞች
አምላክን አሰቃዩ አንገላቱት
የእስትንፋሱ የእጁ ፍጥረቶቸች

❹ኛ ➪ በእግረ አይሁድ መረገጥ ( ተከይዶ በእግረ አይሁድ)
ሰማያት ዙፋን
መንግስቱ ናት
ምድርም የእግሩ
መረገጫ ነት
አይሁዶች ረገጡት
በሃጥ እግራቸው
እርሱ ግን ዝም አለ
እየለመነ ይቅር እያላቸው
ምን አይነት ይቅርታ
ምን አይነት ታጋሽ ነው
ለሚገድሉት ራርቶ
ይቅር የሚላቸው

❺ኛ ➬ ከምሶሶ ጋር ማላተም ( ተገፋዖ ማዕአለ ዓምድ)
ገፍተው ጥለው ሲያጋጩት
ከዓምድ ከምሶሶ ጋራ
አይሁድ ግፍ አበዙበት
አስጨነቁት በመከራ
እውራነን አብርቶ
መንገድን የሚመራ
አይን እንደሌለው
ተላተም ከምሶሶ ጋራ
የጭፍሮች ስራ
አቤት ጭካኔያቸው
በአምላክ ጨከኑ አፌዙ
ሃዘን ርህራሄም የላቸው

❻ኛ ➪ በጥፊ መመታት (ተፅፋዓ መለታሕት )
ኪሩቤል እና ሱራፌል
ከእርሱ ፊት የማይቆሙት
በፍርሃት በእንቅጥቅጥ
ፍጥረት የሚሰግዱለት
በፊቱ ቀይ ግምጃ
ሸፍነው አልብሰውት
በጥፊ ሚመታህን
እወቅ ንገረን አሉት
አንተስ አምላክ ከሆንክ
ንገረን እወቅ ቢሉትም
እንደ ሚሸለት በግ
ቃልንም አልመለሰም

❼ኛ ➪ ጀርባውን በጅራፍ መገረፍ
( ተቀስፎ ዘባን)
ያሁሉን ግርፋት
በጀርባው ላይ ዋለ
የወታደሩ ጅራፍ
በአምላክነቱ ቻላ
ስለ እኛ ግርፋት
አምላክ ተገረፍ
የኛን ፅዋ አሳልፎ
በራሱ ላይ አሳረፈ

❽ኛ ➫ ራሱን በዱላ መመታት ( ተኮርዖተ ርእስረ)
በራሱ ልይ አክሊል
በኪሩቤል ላይ ዙፋኑን
የሚያረገው አምላክ
እንደ እባብ እራሱን
አይሁድ ቀጠቀጡት
በብረት ዘንግ እራሱን
የጲላጦስ ወታደር
አሰቃዩት ቀጡት በግርፋት
ሄሮርስም በተራው
ተሳልቆ ፈረደበት
ንጉስ እየሱስን
አሶግዱት አለ በሞት

❾ኛ ➬ የእሾክ አክሊል አቀናጁት ( አከሊለ ሦክ)
ለቅዱሳን ሰማዕታት
የክብር አክሊል ሚያቀናጅ
የእሾክ አክሊል ተደፋለት
በአይሁድ በአመፀኞች እጅ
በእርሱ ተሳለቁበት
የአይሁድ ንጉስ በለው
ወደ እግሩ ሰገዱለት
በእጁ ዘንግ አሲዘው

❿ኛ ➫ መስቀል መሸከም ( ፀዊረ መስቀል)
መስቀል መከረኛውን
ተሸክሞ በአምላክነቱ
ማንስ ያድነን ነበረ
ባይገድል ሞትን መሞቱ
ሕማመ መስቀል ተሸክሞ
እኛ ሃጥዑን ነፃ አወጣን
የከበደነን ታላቁን ሃጢያት
እሱ በአምላክነቱ ተሸከመልን
በደል ሸክማችነን ተሸክሞ
እኛን ከባርነት ነፃ አወጣን

➊➊ኛ ➪ በችንካር መቸንከር ( ተቀንዎ በቅንዎት)
የሁሉ ፈጣሪ የሁሉ ንጉስ
ምድርን በውሃ ላይ የዘረጋ
እንደ መስዋዕት በግ
በመስቀል ለይ ተዘረጋ
እውራን ያበሩት እጆቹ
በመስቀል ተቸነከሩ
አዳምን ፍለጋ የተመላላሱ
በገነት የሄዱ እግሮቹ
አለምንም እንዲሁ የረገጡ
በሚስማር መስቀል ላይ ተቸነከሩ

➊❷ኛ ➬ በመስቀል መሰቀል ( ቸሰቅሎ በዕፀ)
በመስቀል ለይ ተሰቀለ
በእንጨት ተሰቀለ
እኛን ከሞት ሊያድነን
እንደ አመፀኞች ተቆጠረ
በካህነታ ሰማይ በመላዕክት
ተከቦ በዙፋኑ የሚቀመጥ
እርቃኑን በወንበዴ መሃል
ሁሉን ያስገኘ ሁሉን የሚሰጥ

➊❸ኛ ➬ መራራ ሐሞትን መጠጣት (ሰረበ ሐሞት)
ሁሉን በግዜው ያስገኝ
ፈሳሽ ወንዝ ባህሩን
በእፀ ላይ ተጠማሁ ሲል
አንስተው ሰጡት ሃሞትን
ለፍጥረት ከአለት ላይ ውሃን
ከሰማያት ላይ መናን
የሚሰጥ አምለክ
አበዙበት ጭካኔውን
አቤት የእርሱስ የገርማል
አቤት የእርሱስ ይደንቃል
ስቃዩን ለመግለፅ
ቃላት ያጥራል
ስብሃት ለእግዚአብሔር ልዑል ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር


ተፃፈ በሃብታሙ አበራ


@MENFESAWItsufoche
1.3K viewsKalkidan, 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 10:54:37
፨ ማክሰኞ /የጥያቄ ቀን/ ፨
ሰኞ ባደረገው አንጽኦተ ቤተመቅደስ ምክንያት ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን፣ ስለሥልጣኑ በጸሓፍት ፈሪሳዊያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።


ማቴ21፥23-27 ፣ ማር11፥7-35
ሉቃ 21፥23-27 ፣ ማር11፥27-33
ሉቃ 20፥1-8


@MENFESAWItsufoche
1.0K viewsKalkidan, 07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 19:53:31 ኪ..ራ..ላ..ይ..ሶ..ን ማረን


ኪራላይሶን ማረን አባ አባታችን
ለተወጋዉ ጎንህ
ለበትረ መስቀልህ
ለፈሰሰዉ ደምህ
ቀራንዮ ሞትህ
ጎለጎታ ቤትህ
ኪራላይሶን ማረን ለዛ ህማማትህ።
አባ አባታችን
በጥፊ ስመታህ እጆቼን ይዘሀኝ ልማርህ ብለሀል
ዉሀ አልሠጥም ብዬ በከርቤ ኮምጣጤ ጉንጭህን ሞልተሀል
ጠማኝ አባቴ ስል ይሄ አይጠቅምም ብለህ
የዘላለም ዉሀ ለኔ አዘጋጅተሀል።
ኪራላይሶን ማረን
አባ አባታችን..........
መፃጉ ሆኜ ሳለሁ መዳኔን ሽተሀል
አልጋህን ተሸከም ብለህ ምረሀኛል
ሰንበት አፈረሰ እያልኩ መክሰሴን
ጌታ አረሳሁትም ማራት ይህቺን ነፍሴን።
ጎንህን ወጋሁት በጦሩ ጎርጉሬ
አቤቱ ማዳንህ አይኖቼን አበራህ ትተህ መነወሬን።
የሀጥያቴ መብዛቱን አይተህ ሳትጠየፍ
ፈራሽ ሰዉነቴን አፈር ማንነቴን ተመልክተህ ሳታልፍ
እኔ የከንቱ ከንቱ ፊትህን ተጠይፊ
የማይፈርስ አካልህን ፍቅርህን ጠፍፌ
ማረዉ ብለህ ስትል ሰዉነቴ ቀፎት
ምራቅ ተፋዉብህ ለኔ መምጣትህን እኔነቴ ክዶት።
ኪራላይሶን ማረን
ስለናትህ ማረን................
ሸክማችሁን በኔ ጣሉት ብለህ ስትል
ችግሬን ጥዬብህ
እንቅልፍና እረፍትን ባንተ አገኘዉብህ
ችግሬ አንሶብኝ
መስቀል ማሸከሜን ጌታ አትይብኝ
ከኃላ እንድትፈጥን እየገፈተርኩ
ከፊት ቀስ እንድትል እየገፈተርኩ
መሬት ስትወድቅ እያንቀለቀልኩ
ስትነሳ ደግሞ እያወዛገብኩ
መቼ ይረሳኛል እንዳንከራተትኩህ።
ኪራላይሶን ማረን
አባ አባታችን...............
መዳፍህ ይታየኛል
ጭቃ አበጃጅቶ እኔን የሰራልኝ
ዳብሶ የፈወሰኝ
እኔ የእፉኝት ልጅ
አዴራ አላዶር ሳዳርና ዳናት በሚባል ችንካሮች
መዳፍህን በሳዉ አለምን በያዙ በነዛ ድንቅ እጆች።
እግርህን ቸነከርኩ ምድርና ሰማይ ሊችሉት ያልቻለ
አልፋና ኦሜጋ በመስቀል ላይ ዋለ።

ኪ..ራ..ላ..ይ..ሶ..ን ማረን


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@MENFESAWItsufoche
861 viewsKalkidan, 16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 07:29:00 ኦርቶዶክሳዊያን ሆይ በየቤታቹ ስትሰግዱ በዚህ የህማማት ሳምንት ከስግደት ጋር እየተባለ የሚፀለይ ጸሎት ነው። በምትሰግዱበት ክፍል ውስጥ በመለጠፍ ስገዱ እንስገድ ፀሎት ልመናችንን በቀራኒዮ የተሰቀለው መድሃኒታችን ቤዛችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ ይቀበለን አሜን


ሥርዓተ ጸሎት ወስግደት ዘሰሙነ ሕማማት
ነግህ (ሰዓት 7 ቅ.ቀ.)፡ ሠለስቱ (ሰዓት 9 ቅ.ቀ)፡ ስድስቱ (ሰዓት 12 ድ.ቀ.)፡ ተስዓቱ(ሰዓት 3 ድ.ቀ)፡ ዓሠርቱ ወአሐዱ (ሰዓት 5 ድ.ቀ.)፡ ዘሎ ሥርዓተ ጸሎት ወስግደት ነዚ ይመስል።

ናይ ‘ለከ ኃይል’ ጸሎትን ስግደትን

ጸሎታት መዝሙረ ዳዊት፡ ውዳሴ ማርያም ምስለ አንቀጸ ብርሃን ይጽለ።
* ለከ ኃይል

ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም

አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም

ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም

ኃይልየ ወፀወንየ ውእቱ እግዚእየ

እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት


* አቡነ ዘበሰማያ

አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ

ትምጻእ መንግሥትከ ወይኩን ፈቃድከ

በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር

ሲሳየነ ዘለለዕለትነ ሃበነ ዮም

ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ

ከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ

ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት

አላ አድኅነነ ወባልሐነ

እምኵሉ እኩይ እስመ ዚአከ

ይእቲ መንግሥት

ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።

* ለአምላክ ይደሉ

ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም

ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም

ለማሕየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለሕማሙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም (በዓርብ)

ለከ ይደሉ ኃይል ለከ ይደሉ ስብሐት ወለከ ይደሉ አኰቴት ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም

*
ተኣምረ ማርያም፡ ተአምረ መላእክት፡ ተአምረ ሰማዕት፡ ተአምረ ጻድቃን፡ ተኣምረ ኢየሱስ ይንበብ። መዝሙረ ዳዊት “ምስባክ”፡ ‘ወንጌል ቅዱስ’፡ ኣርባዕተ ወንጌል ንባብ የንብብ። ተግሣፅ’ውን ፡፡

*

ናይ ‘ኪርያላይሶን’ ጸሎትን ስግደትን

* ካህን፦ 'ጸልዩ በእንተ ጽንዐ ዛቲ መካን . . ./
“ እግዚኦ ተሠሃለነ /

* ኪርያላይሶን

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን እብኖዲ ናይን ኪርያላይሶን

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ታኦስ ናይን ኪርያላይሶን

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ትስቡጣ ናይን ኪርያላይሶን

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ማስያስ ናይን ኪርያላይሶን

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኢየሱስ ናይን ኪርያላይሶን

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ክርስቶስ ናይን ኪርያላይሶን

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኣማኑኤል ናይን ኪርያላይሶን

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን


• 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ይብሉ። 'መልክዐ ሕማማት' ይዝየም።
*
እቲ ወንጌል ዘንበበ ካህን ፡ ‘ፍትሐት ዘወልድ፡ ጸሎተ ቡራኬ ወዕቀቦሙ፡ ኦ ሥሉስ ቅዱስ፡ ኦ ማኅበራኒሁ ለክርስቶስ ፡ ነዋ በግዑ . . .’ ምስ ጸለየ 41 ስግደትን 12 ኣቡነ ዘበሰማያት ይእዝዝ።
* ዲያቆን ድማ ብዜማ ኃዘን ብውርድ ንባብ ከምዚ እናበለ ንሕዝቢ የሰናብት፦
“ ሑሩ በሰላም እግዚአብሔር የሀሉ ምስሌክሙ ንዑ ወተጋብኡ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት በጊዜ ____ ሰዓተ መዓልት ለጸሎት።”

***
#እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጸጽሐክሙ#

@MENFESAWItsufoche
1.7K viewsKalkidan, 04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 07:29:00 ሰሙነ ሕማማት፦ ሕማም የሚለው ቃል ሐመ፣ ታመመ ከሚለው የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን የጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማሙን እና ሞቱን የሚዘከርበት ሳምንት ነው።
፨ ሰኞ፨
ሁለት ነገሮችን አድርጓል
1* ከቅጠል በቀር በለስ ያልተገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል።
2* ወደቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸቱትን እና የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን አስወጥቷል።
ማቴ21:12 ፣ ማር 11:17 ፣ ሉቃስ 19:45


@MENFESAWItsufoche
1.3K viewsKalkidan, 04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 07:29:00
1.2K viewsKalkidan, 04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 20:11:33
1.4K viewsKalkidan, 17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 15:08:14 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች pinned a photo
12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 15:06:35
የአብይ ፆም ስምንተኛ ሳምንት

ሆሳእና



፨አህያዋ፨


ከእንስሳት ተለይታ
ልትቆም በሰው ተርታ
ሊቀመጥባት ጌታዋ
ሊታወቅላት ዋጋዋ
ላይጠፋባት አደራዋ
ሰው የማገልገል ስራዋ
ሲመጣላት ፈጣሪዋ
ደስ አላት አህያዋ
ሲቀመጥባት በጀርባዋ።
ውርንጭላነቷ ቀርቶ
የታሰረችበት ገመድ ተፈቶ
መናቅ መሰደቧ ጠፍቶ
የዋሁ የጺዮን ልጅ ትህትናን ተመልቶ
አስገባት ከተማ በህዝቡ ፊት መርቶ።
አፋቸው ተለጉሞ
ሃሳባቸው ከፍቶ ጠሞ
አዋቂ ነን ባዮቹ
የአይሁድ ካህናት ግብዞቹ
ዝም ቢሉ ለምስጋና
ለመራቸው በደመና
ለመገባቸው ከሰማይ መና
መመስገኑ መቼ ቀረና
እየተባለ ሆሳእና።
በሴቶች በወንዶቹ
በአዛውንት በልጆቹ
በህጻናት ጡት ጠቢዎቹ።
የዘኪዮስ ምኞት
መቼ ተረሳ በእጥረቱ
ዛፍ ላይ ብቻ በመታየቱ
አለቀረም ፍላጎቱ
ለመዘመር መጓጓቱ
ገብቶለታል ወደ ቤቱ
የጺዮን ልጅ ያትሁቱ
ሊበላ አብሮት ከፍትፍቱ።
መቅደስ ገብቶ ዞሮ ሲቃኝ
ሲመለከት ጊዜ አባካኝ
ጽሎት ትቶ ሲቸረችር
ከሌባ ጋር ሲደራደር
አልቻለም ስለ ቤቱ
ሲያቃጥለው ቅንአቱ
ጅራፍ ሰራ ለትምህርቱ
ቤቱን ሊያጠራ ከጠላቱ።


@MENFESAWItsufoche
1.8K viewsKalkidan, 12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ