Get Mystery Box with random crypto!

🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
የሰርጥ አድራሻ: @menfesawitsufoche
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.03K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ትምህርታዊ ጹሑፎችን፣ ብሂለ አበው፣ ከመጽሐፍት ዓለም እና ሌሎችም ''መንፍሳዊ ሥነ-ጹሑፎችን'' ያገኛሉ።
.
.
.
ሃሳብ አስተያየታቹን ወይም ቻናሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ስነ-ጹሑፎች ለመደገፍ @kal002 ላይ አድርሱን።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-19 11:53:34 ፨መስቀሉ በፊቴ፨
=======✞========

የቀራኒዮ አርማ የፍቅር ሰሌዳ
የሰላም ብራና ቀለሙን የቀዳ
የድህነት ማህደሯ ጠቋሚ መሪዋ
እንቅፋት ነቃፊ አዳኝ ጠባቂዋ
የሰማዩ ንጉስ ስጋው ቆርሶባት
ደሙን አፍስሶ ላቡን ደቅኖባት
የትውልድን አረም ሊነቅል ከስሩ
ባሪያውን መስሎ ወረደ ከክብሩ።
ኤሎሄ ብሎ ጮኸ አምላክ ሆኖ ሳለ
የጠላትን መንግስት ንዶ እየጣለ
ደብዳቤውን ደምስሶ በችንካሩ ፋቀው
የዕዳው ፅሕፈት በደሙ ጠረገው።
በመስቀል የዋለ ጎልጎታ ያደረ
እባቡን ቀጥቅጦ አዳምን የማረ
ሄዋንን ከጭንቀቷ ጎትቶ ያወጣት
ልጆቿን ከሲኦል አትርፎ ከእሳት
በመስቀሉ ገፅ በችንካሩ ጫፍ
በእሾህ አክሊል ብሳት በከሳሾቹ አፍ
መከራው ሲፀና ስቃዩ ሲበረታ
ፊቱን በጥፊ ሶስት ጊዜ ሲመታ
የአምላካችን ፍቅር ከልብ የፈለቀ
ቢሆን ነው እንጂ ይቅርታው የላቀ።
በቃ!
ታዲያ ከመስቀሉ ወዲያ መገለጫ ለእኔ
ከወዴት ይገኛል ማረፊያ ለአይኔ?
ኧረ ከየት ይመጣል ተግዳሮቱን ሚያክል
የዕዳዬን ጣጣ በነፍሱ ሚከፍል።
ትምክህቱ ይራቅ ከጌታዬ መስቀል በቀር
አይኔ ሌላ አያይም ከቀራኒዮ መንደር
የመስቀሉን ፍቅር የሚያደንቀው አለ
ልቤ ላይ ከትሞ ነፍሴ እየነዋለለ።
የክርስቶስ መስቀል በፊቴ ተስሎ
እኔ እንድጠነክር እርሱ ስለኔ ዝሎ
የምሸከመውን እርሱ ተሸክሞ
ለኔ እንዲበራ እርሱ ላይ ጨልሞ
መስቀሉን ደረሰው ፍቅሩን እየፃፈ
የአመፃን ማዕበል በምሕረት ቀዘፈ
ቸርነቱ በዝቶ ቅጣቱ አለፈ።
➴ከእህተ ማርያም


➴ ➴ ➴ ➴ ➴ ➴
@MENFESAWItsufoche
741 viewsKalkidan, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 17:52:23 *ግዑዙ ከበሮ*

ሁለት ወራት ሙሉ እጥፍ ቅልጥፍ ብሎ
በጾምና ጸሎት ከስራው ተገልሎ
በሐዘን በድማሜ ዘውትር አዘንብሎ
የቆየው ከበሮ ዛሬ ዜና ሰማ
የራቀው ቅላጼ በርጋታ ተሰማ
ከሩቅ አስተጋባ በሚነሽጥ ዜማ
ድምጹ ከአጽናፍ አለም ፈሰሰ በግርማ
በአምሳለ እየሩሳሌም በቅድስት ከተማ
ግዑዙ ከበሮ እንዲ ከረቀቀ
በሁዳዴ ተኝቶ ትንሳኤን ካወቀ
የሰው ልጅ ምን ነካው እንቅልፉ ጨመረ
በትንሳኤ ማግስት እንደተኛ ቀረ።


@MENFESAWItsufoche
716 viewsKalkidan, edited  14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 17:52:23 ፨መንፈሳዊ ዜና፨

በበዓሉ እለት ሆዱ እስኪተረተር የተመገበው ግለሰብ 750kg ምግብ ከሆዱ ውስጥ በቀዶ ጥገና ወጣለት።ይህ ግለሰብ ሀገር ሰላም ብሎ የበዓሉን ምግብ ያላግባብ ሲበላ ቆየእና ባልጠበቀው ሁኔታ ሆዱ ከበሮ ያክልበታል በሁኔታው በመደናገጥ ወደ ሆስፒታል ያመራው ግለሰብ በዶክተሮቹ በተደረገለት ምርመራ ከፍተኛ የሆነ የምግብ ክምችት በሆዱ ውስጥ በመኖሩ ምክንያት ቀዶ ጥገና እንደሚያስፈልገው ይነገርዋል። በኋላም በተደረገለት የቀዶ ጥገና 750 kg ምግብ ከሆዱ ውስጥ ሊወጣ ችሏል። እንደ ዶክተሮቹ ገለፃ በሰውየው ሆድ ውስጥ የተገኘው የምግብ መጠን በትንሹ ለ100 ሰዎች ምሳ እና እራት እንደሚሆን ነው።
እንግዲ ክርስቲያኖች በበዓል ወቅት አመጋገባችንን በአግባቡ እና በስርዓቱ በማድረግ
"ብራብ አብልታችሁኛል....ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን አለም ሳይፈጠር ወደ ተዘጋጀላቹ እርስት መንግስተ ሰማያት ግቡ" የሚለውን የአምላካችን የህይወት ቃል እንድንሰማ የሚበቀምሱት አጥተው በረሃብ የሚሰቃዩትን ነዲያን እና ድኩማንን በመመገብ እና በመርዳት ለነፍሳችንም ለስጋችንም ዋጋ እናግኝ እንላለን።
ከቃልኪዳን ተፈራ
➴ ➴ ➴ ➴ ➴ ➴
@MENFESAWItsufoche
➴ ➴ ➴ ➴ ➴ ➴
735 viewsKalkidan, 14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 17:50:45
665 viewsKalkidan, 14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 00:01:35 ከበዓል በኃላ ለሰርጎ , ለልጆቾ ክርስትና የዲኮር ስራ ማሰራት ይፈልጋሉ ?



ለ ሰርግ                            ለ ክርስትና
ለ ልደት                            ለ ቀለበት
ለ ገዓት                             ለ ሽምግልና
ለ ተማሪዎች ምረቃ           ለ ልጆች ልደት
ለ ቤት ምርቃት                   ለ ሆቴል ምረቃ
ለ ስብሰባ አዳራሾች          ለ ቤተሰብ ኘሮግራሞች
ለ ሰርግ ለመኪና ዲኮር
በ ቤተክርስቲያን ስርዓት ለሚፈፀሙ ሰርጎች እና ኘሮግራሞች

ለተለያዮ ዝግጅቶችም ጭምር የተለያዮ የዲኮሪሽን ስራዎችን እንሰራለን እንዲሁም የተለያዮ የዲኮር እቃዎችን እናቀርባለን !
       

     
              ይህን ይጫኑት  ...  ይህን ይጫኑት

█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█


Tel .   +251961064953
                 +251703504953
.
112 viewsመንፈሳዊ 3k, 21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 15:20:05 ፨በደሙ አተመኝ፨

ለሌባ ዋስ የለው
ለቀማኛ ዘመድ
ከጓደኛዬ ጋር
ተቀብለን የሞት ፍርድ
ተገልጾ ሲታየኝ
በደሉና ጽድቁ
የጸጸትን እንባ
ዓይኖቼ አፈለቁ
ለካስ ከሞት ሀገር
ሕይወትም ይገኛል
የዕድሜ ልክን ኃጢአት
ንስሐ ያጠራል
ዕንባዬን አብሶ
የተስፋ ቃል ሰጠኝ
ዳግም እንዳልጠፋ
በደሙ አተመኝ
ቁልፉን ተረክቤ
ከሕይወት ባለቤት
አዳምን ቀድሜ
ገባሁ ወደ ገነት።

➴ ➴ ➴ ➴ ➴ ➴
@MENFESAWItsufoche
935 viewsKalkidan, 12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 09:40:10 አማን በአማን





ዘማሪት ማኅሌት ታደሠ

@MENFESAWItsufoche
1.2K viewsKalkidan, 06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 09:34:50 ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ
ተሃፂባ በደመ ክርስቶስ





ማኅሌት ታደሠ

@MENFESAWItsufoche
1.1K viewsKalkidan, 06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 09:30:55
፨ክርስቶስ ተነሳ፨

ድውይ በፈወሰ ሙታንን ባነሳ
ይሰቀል ተባለ ውለታው ተረሳ።
ክርስቶስ ይሰቀል በርባንን ልቀቀው
ብሎ ተናገረ ሀጢያት የናፈቀው።
የይሁዳ ክህደት ዓይኑን ያፈጠጠ
ለሰላሳ ብር ሲል አምላኩን የሸጠ።
ቸሩ መድሐኒዓለም ብዙ ተገረፈ
መከራው ቢጠናም በትዕግስት አለፈ።
እየተጋገዙ ጨርሶ እስኪቀር አጥንቱ
የአዳም ዘርን ሁሉ ከሲኦል ለማውጣት
ፈጣሪ በፍጡር ተቀበለ ቅጣት።
ተሰቀለ ብላ ስታዝን እናቱ
ገድለነዋል ብለው አህዛብ ሲዘብቱ
አዳኙን ቢገድሉት ያለ አንዳች አበሳ
ሞትን ድል አድርጎ ክርስቶስ ተነሳ።

➴ ➴ ➴ ➴ ➴
@MENFESAWItsufoche
1.1K viewsKalkidan, 06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 09:29:01 ፨የትንሳኤ ሳምንት ሰላምታ፨

ክርስቶስ ተንስአ እሙታን


ወአብይ ሃይል ወስልጣን


አሰሮ ለሰይጣን


አጋዞ ለአዳም


ሰላም


እምዝየሰ


ኮነ


ፍስሐ ወሰላም።


ትርጉም
ክርስቶስ ከሙታን ተነሳ
በታላቅ ሃይልና ስልጣን
ሰይጣንን አስሮ
አዳምን አዳነው
ሰላምም ሆነ ለሁላችን
ድስታና ሰላም።


፨እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!
ለብርሃነ እርገቱም በሰላም በፍስሐ ያድርሰን አሜን



➴ ➴ ➴ ➴ ➴
@MENFESAWItsufoche
1.0K viewsKalkidan, 06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ