Get Mystery Box with random crypto!

፨በደሙ አተመኝ፨ ለሌባ ዋስ የለው ለቀማኛ ዘመድ ከጓደኛዬ ጋር ተቀብለን የሞት | 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

፨በደሙ አተመኝ፨

ለሌባ ዋስ የለው
ለቀማኛ ዘመድ
ከጓደኛዬ ጋር
ተቀብለን የሞት ፍርድ
ተገልጾ ሲታየኝ
በደሉና ጽድቁ
የጸጸትን እንባ
ዓይኖቼ አፈለቁ
ለካስ ከሞት ሀገር
ሕይወትም ይገኛል
የዕድሜ ልክን ኃጢአት
ንስሐ ያጠራል
ዕንባዬን አብሶ
የተስፋ ቃል ሰጠኝ
ዳግም እንዳልጠፋ
በደሙ አተመኝ
ቁልፉን ተረክቤ
ከሕይወት ባለቤት
አዳምን ቀድሜ
ገባሁ ወደ ገነት።

➴ ➴ ➴ ➴ ➴ ➴
@MENFESAWItsufoche