Get Mystery Box with random crypto!

🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻 መ
የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawitsufoche — 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
የሰርጥ አድራሻ: @menfesawitsufoche
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.03K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ትምህርታዊ ጹሑፎችን፣ ብሂለ አበው፣ ከመጽሐፍት ዓለም እና ሌሎችም ''መንፍሳዊ ሥነ-ጹሑፎችን'' ያገኛሉ።
.
.
.
ሃሳብ አስተያየታቹን ወይም ቻናሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ስነ-ጹሑፎች ለመደገፍ @kal002 ላይ አድርሱን።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-03-22 01:14:53 የምሰራች የምሰራች...      ለተዋህዶ ልጆች !


መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች መማር ይፈልጋሉ

 
እምቢልታ መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች  ማሰልጠኛ  ተቋም 

➜  በገ ና
➜  ክራር
➜ መሰንቆ
➜ ዋሽንት

   በሚፈልጉት ቀን እና ሰዓት  እንዲሁም በግል ቤት ለቤት  እናስተምራለን ! በተጭማሪ  ጥራት ያላቸው  የበገና , የክራር , መሰንቆ እንሸጣለን እናከፋፍላለን የክራር የበገና የመሰንቆ ቦርሳ እኛ ጋርም ያገኛሉ !


አድራሻችን  -  ጀሞ 1 ሩት የገበያ ማዕከል
                            
        Tel.  +251967437703
                     +251993945900


አሁኑኑ በዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉልን !

.
367 viewsመንፈሳዊ 3k, 22:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 18:46:12 ፨ና! ከደብርዘይት ፨

......የቀጠለ

ኑፋቄ የሚያቀርቡ ክህደት የሚዘሩ
በመቅደስ ሆነው እየተዟዟሩ
የሚሸጡም አሉ ንፍቅና ሚሰፍሩ
መግባት ያቃታቸው ከውጭ ያቀርባሉ
ችርቻሮ ጅምላ ዱቤ ዋጋ እያሉ
ውስጥ ያሉ በርካሽ ከመቅደሱ ሆነው
ይቸበችቡታል የኑፋቄውን ንግድ
ቤቱን ለመቦርቦር መቅደሱን ለመናድ
አስመጪ አከፋፋይ ሆነዋል ብዙዎች
ኑፋቄ እየሸጡ ሃጢአት ማከፋፈል
ገንዘብ እየሰጡ ቅድስናን ማስጣል
.
.
.
ናት ከደብረ ዘይት ቁል ቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ ጅራፍ አበጅና
አውሬው ተደስቷል ገብያው ሰምሮለት
ሰርግና ምላሽ ነው መቅደስ እረክሶለት
አንድ ዕቃ ለገዛ ሁለት አለን ነፃ
ማስታወቂያው በስቷል በየጥጋጥጉ
መክፈልም ካቃተ ዱቤ አለን አትስጉ
የትኛው ያተርፋል ይሄ ስንት ያወጣል
ይኽን የሚገዛ ያንን የሚለውጥ
ይኼ ሆኗል በቋንቋው በቤተመቅደስ ውስጥ
ውጡ እናንት ሸማቾች
ውጡ እናንት ነጋዴዎች
ገበያ ሰሪዎች
በተቀደሰው ላይ ገንዘያ የምትሰሩ
በምስጋናው ዕቃ ሸቀጥ የምትሰፍሩ
ነፃውን ግልጋሎት ገቢያ ያወጣቹ
በጸሎት ስፍራዬ ሱቅ የከፈታቹ
ውጡ እናንት ሸማቾች ቤቴን የለዋጮች ስፍራ ያረጋቹ
በተቀደሰው ላይ መደብ የሰራቹ
የነጋዲያኑ መደርደርያ የእርግብ ሻጮቹ ወንበር
የሻጭ የለዋጩን የሱቁን መደብር
በትን ብራቸውን ግረፍ በጅራፍህ አርቅ ከደጃፍህ
ውጡ እናንት ሸማቾች ቤቴ የጸሎት ነው
ቤቴ የአምልኮ ነው
ቤቴ ለስግደት ነው
አንሱ ይኽን ወንበር ውሰዱ ከፊቴ
የምስጋና ስፍራ የጸሎት ነው ቤቴ
የገበያ ሃሳብ የሌባ ሸመታ
አይሆንም ከዚህ ውስጥ ውጡ ከዚህ ቦታ
ለሌላ አሳልፈህ ለአህዛብ አትስጠን
ቤቱ ያንተ ቤት ነው እኛም ያንተው ነን
እንደ አባትነትህ እራስህ ገስጸን
እጠባት ቤትህን እጠብቃለሁ ሁላችንን
አጽዳ መቅደስህን ፍታው ገቢያውን
ያንተ ግርፊያ ይሁን ለሌላ አትተወን
ስለ ቅዱሳንህ ብለህ ተለመነን
ቤቴየሰ ብለህ አንተው አስተካክለን
.
.
.
ና ከደብረ ዘይት ከቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ አለንጋ ያዝና
ና ከደብረ ዘይት ቁል ቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ ጅራፍ አበጅና።

ተፈፀመ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

➴ ➴ ➴ ➴ ➴ ➴
@MENFESAWItsufoche
210 viewsKalkidan, 15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 18:46:12 ፨ና! ከደብረ ዘይት፨

....የቀጠለ


አፍኒን እና ፊናስ መቅደስህን ደፍረው
ኤሊን አስቆጥተው ህዝቡን አስመርረው
በከበረው ነዋይ ጨዋታ ይዘዋል
በቅዱስ ቁርባኑም ማፌዝ ጀምረዋል
ግዴለሾች ሆነው ግልጋሎት እረስተው
የእግዚአብሔርን ቁርባን ንቀው አቃለዋል
በድንኳኑ ደጃፍ በአገልግሎት ካሉት ከሴት ተኝተዋል
የካህኑ ኤሊ ድምፁ አልተሰማም
የልጆቹን በደል አይቶ አልተናገረም
የቤተመቅደሱ የጦፈ ገቢያ ዝም ብሏል እያየ የንግዱን መዋያ
ሳሙኤል ተኝቷል እግዚአብሔር ይጣራል
ደጋግሞ እስኪሰማ ድምጹን እያጣራ ሳሙኤል ተኝቷል
እግዚአብሔር ይጣራል
ሳሙኤል ሳሙኤል የሰው ያለህ ይላል
እግዚአብሔር ይጣራል
ከአፋኒን እና ፊናስ በደል ከፍ ብሎ
ከነጋዴዎች ጩኽት ከነጋዴዎች ሁከት ድምጽ ሁሉ አይሎ
እግዚአብሔር ይጣራል ሳሙኤል ብሎ
በቤተመቅደሱ ድምጹ ያስተጋባል
የጅራፉ ጩኸት ድምጹ ቋንቋ ፈጥሯል
ሳሙኤል ሳሙኤል እግዚአብሔር ይጣራል
ኤሊም ዝም ብሏል
የቤተመቅደሱን ንግድ አልተቃወመም
በቅዱሱ ስፍራ የማይገባውን አልተከላከለም
ተው አላለም ኤሊ እንደ ክህነቱ
ተው አላለም ኤሊ እንደ ስርዓቱ
መቅደሱ ሲደፈር ልጆቹ ሲስቱ
ንግዱ ተጧጥፏል ኤሊም ዝም ብሏል
ይሄ በደል ከብዶ ፀጋህ ሳትወሰድ
መቀጣጫ ሆኖ አህዛብ ሳይለብሱ
እውነት ሳይጋረድ
ምህረት ሳይርቀን ጥበቃህን ሳተው
ጽዮን ሳትማረክ ፊትህን ሳታዞረው
.
.
.
ና! ከደብረ ዘይት ቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ አለንጋ ያዝና
መቅደስህን አጽዳ ጅራፍ አበጅና።

ይቀጥላል....

➴ ➴ ➴ ➴ ➴

@MENFESAWItsufoche
186 viewsKalkidan, 15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 18:46:12 ✞ ና! ከደብረ ዘይት ✞

....የቀጠለ

የፖለቲካው ንግድ መቅደስክ ውስጥ ሆኗል
ያኛው ይራገማል ይህኛው ያወግዛል
ዘር ቡድን ለይቷል ልዩነቱ ሰፍቷል
የኬፋ ነን ያሉ በአንድ ወገን ሆነው
መደብር አቁመው ወንዝ ጎሳ ጠርተው ገብያ ሰርተዋል
ሌሎች ከዛ ማዶ ከመቅደሱ መሃል
አጥንት የቆጠሩ ደም የመረመሩ ዘር የዘረዘሩ
የአጵሎስ ነን ያሉ ሌላ ንግድ አላቸው ሸመታ ይዘዋል
የሚሸጥ ይሸጣል የሚገዛም በስቷል
የገቢያው ጩኸት የሌቦች ኹካታ
ቤትህን ሞልቷታል የመንደር ጨዋታ
ሰላሟን ነስቷታል ክብሯን አዋርዷታል
በተቀደሰው ቤት በደጀ ሰላሙ እርኩሰቱ ገኗል
የቤቱ ባለቤት ማንነት ተረስቷል የቅዱሳን ህይወት ታሪክ ብቻ ሆኗል
የምድራዊው ነገር በዝቶ ይነገራል
ግማሹ ከጳውሎስ ነን ብሎ ይቆማል
ቀሪው ከኬፋ ጋር ብሎ ይቧደናል
በክርስቶስ ህብረት አንድነት ቦታ አጥቷል
ቋንቋ ደም ዘረ ሆኗል ቅድሚያ የሚሰጠው
ማነህ ከወዴት ነክ ከነማነህ ሆኗል አቋቋሙ ቅኔው
መስቀል ተሸክመህ ቀራንዮ ውለህ
ደምህን አፍስህ
አጥንትህን እስኪታይ ስጋህ እስኪደማ ግርፋቱን ችለህ
የሁሉን ሰው ደዌ ህማም ተሸክመህ
ስለሚተላለፍ ስለ በደል ቆስለህ
በመከራ መስቀል ህይወትኽን ሰጠህ
የከፈልከው ዋጋ ሁሉ ተዘንግቶ
መሞትህ ተረስቶ
ከፊት ተደርድርው ወንዝ ጎሳ መንደር
ገበያ ሰርተዋል በማስመሰል ፍቅር
በእንግድነቱ አለም በዚህ ከንቱ ምድር
ጥለን የምንሄደው የዘር የወንዝ ክብር
በቤተክርስቲያን በመቅደሱ ስፍራ የደራ ንግድ ነው የሚያተረፍ ስራ
ቋንቋም ሆኗል ገንዘብ የመግባቢያው በሩ
ወይንም ዘር መቁጠር ነው ወንዝ እየከተሩ
.
.
.
ና ከደብረ ዘይት ቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ አለንጋ ያዝና
ና ከደብረ ዘይት ቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ ጅራፍ አበጅና

ይቀጥላል......

➴ ➴ ➴ ➴ ➴ ➴
@MENFESAWItsufoche
155 viewsKalkidan, 15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 18:46:12 ✞ ና! ከደብረዘይት✞

@MENFESAWItsufoche

የሰው ልጅ ፍቅር ከዙፍን ከሰማያት ከከብርህ ወደ ምድር ስቦህ
የኛን ስጋ ለብሰህ ደዌያችንን ተቀብለህ
ህማማችንን ተሸክመህ
በጲላጦስ አደባባይ ቀራንዮ በመስቀል ላይ
እየሞትክ ያነጽካት ደም የከፈልክላት
ቤዛ የሆንክላት
የሲኦል ሃያላን የዲያብሎስ ጭፍሮች ያልተገዳደሩአት
በደምህ ነጠብጣብ በዋጋ የገዛሃት
ቤትህ አድፋለች ወንበዴዎች ከበዋት
ሻጮች ሰፍረውባት ገበያ ሆኖባት
ሸመታው ደርቶባት በአህዛብ ተንቃለች
በርግብ ሻጮች ወንበር ቤትህ ቆሽሻለች
በለዋጮች ዕቃ በዕዳ ተይዛለች

ና! ከደብረ ዘይት ቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ አለንጋ ያዝና
ና! ከደብረ ዘይት ቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ አለንጋ ያዝና

ወደ እየሩሳሌም ስትገባ ያጀቡክ
ቁልቁል ደብረ ዘይት ስትወርድ የከበቡክ
ልብሳቸውን ጥለው ሆሳእና ዛሬ የዳዊት ልጅ ያሉ
ማለዳ ተነስቶ በቅዳሴ ስምህ ክበር ያሉህ ሁሉ
በምስጋና ፍክተው በልልታ በሆታ
መድሃኒት ነክ ያሉ
አረፋፋዱ ላይ መቅደስ ውስጥ ገብተው
ቤትህ ተመልሰው ቅዱሳቱን ከበው
በአገልግሎት ዕቃ ገቢያ ይዘዋል
ገዢና ሻጭ ሆነው ሁሉም ርቀዋል
የጦፈ ገበያ የደራ ሸመታ
የሌቦች ትርምስ የለዋጮች ወይታ
መልኳን ቀይሯታል ያለስሟ ስም ስም አሰጥቷታል።

ና! ከደብረ ዘይት ቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ አለንጋ ያዝና

ይቀጥላል......

➴ ➴ ➴ ➴ ➴ ➴
@MENFESAWItsufoche
187 viewsKalkidan, 15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 23:46:06 የምሰራች የምሰራች...      ለተዋህዶ ልጆች !


መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች መማር ይፈልጋሉ

 
እምቢልታ መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች  ማሰልጠኛ  ተቋም 

➜  በገ ና
➜  ክራር
➜ መሰንቆ
➜ ዋሽንት

   በሚፈልጉት ቀን እና ሰዓት  እንዲሁም በግል ቤት ለቤት  እናስተምራለን ! በተጭማሪ  ጥራት ያላቸው  የበገና , የክራር , መሰንቆ እንሸጣለን እናከፋፍላለን የክራር የበገና የመሰንቆ ቦርሳ እኛ ጋርም ያገኛሉ !


አድራሻችን  -  ጀሞ 1 ሩት የገበያ ማዕከል
                            
        Tel.  +251967437703
                     +251993945900


አሁኑኑ በዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉልን !

.
861 viewsመንፈሳዊ 3k, 20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 19:20:23 +++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን+++
(መቼ ትመጣለህ ? )

መቼ ትመጣለህ? ነገ ወይስ ዛሬ?በኃጢአት አልክበር ፤ ዕድሜዬን አልጨርስ ፤ አልብላው መንዝሬ።
ንገረኝ ጊዜውን ፤ ቆሜ ልጠብቅህ ፣
ግራ ቀኝ አልባክን ፤ እንዴት ነው አመጣጥህ ?
ትዘገይ እንደሆን ፤ ላትጠራኝ ቶሎ ፣
ከእፀ በለስ ልብላ ፤ ስሜቴ ገንፍሎ ፣
ምክንያቴን አብዝቼ ፤ አግዝፌ ልቆይህ ፣
ሔዋን አስታኝ ነው ፤ ሰይጣን አሳስቷት ፤
መክሯት ነው ልበልህ።
ለሥጋዬ ልስጣት ፤ ሥልጣኑን በሙሉ ነፍሴን ትበድላት ፣
ለጊዜው ትጠቀም ፤ አንተ ከዘገየህ ትሁነው እንዳሻት ።
ጊዜ አገኝ እንደሁ ፤ በተራገምኩበት መመረቅ እንድችል ፣
እስከ ጊዜው ድረስ ፤ ነፍሴ ታንጎራጉር ትንደደው ትቃጠል ።
ሰዎች ተስፋ ቆርጠው ፤ ይኸው በዚህ ሰሞን ታሪክ ያወራሉ ፣
ያ! ስምንተኛው ሺህ ፤ ከተነገረ እንኳ ቆይቷል እያሉ
ሰዉ ጽድቁን ትቷል ሁሉም በያለበት ሀሜቱን ቀጥሏል ፣
መጋደል መጣለፍ ፤ መቋሰል መቧደን ዝርፊያውም በርክቷል ፣
እንኳን ዳግም ም'ጻት የዓለም ፍጻሜ ስምህ ተዘንግቷል።
 
መቼ ትመጣለህ ነገ ወይስ ዛሬ?
                                
ግዴለም ንገረኝ ፤ ልክ እንደኖኅ ጊዜ ዘመኑን አስላና፣
ሃያዋ ብትበቃኝ ለንሰሓ ጊዜ ፤ በመቶው ልዝናና።
ገና አልበረደኝም ሰውነቴ ግሎ ውስጥ አካሌ ዘንቶ፣
ዓለሙን ያስሳል ፤ አንተ ከዘገየህ ለምን ሥራ ፈትቶ።
እበላው እንደሆን የሰበሰብኩትን ፤ ከሌላው ዘርፌ፣
እኖረው እንደሆን እንደማቱሳላ እድሜዬን አትርፌ።
ሺህ ዓመቴን ወስደህ ፤ የአንተን አንድ ቀን ትሰጠኝ እንደሆን ፣
ምናለበት ብዘርፍ ምናለ ብዘሙት ፤ መዘግየትህ ላይቀር ።
ከምድር እሰከ ሰማይ ፤ ተዘርግቶ 'ማያልቅ ለበዛው ኃጢአቴ ፣
ጊዜ ካበደርከኝ እንዲሰረዝልኝ ፤ እንዲፋቅ ጥፋቴ ፣
ልክ እንደ ኢያሱ ፤ ፀሐይን አቁመህ ከጠበቅኸኝ በቃኝ ፣
ዛሬን ልዝናናበት ፤ ኃጢአት ልጨማምር  ጨለማ ሳይወርሰኝ ፣
ይኸው ሰዉ ሁሉ ነገሩን ዘንግቶ ፤ ሁሉ ሆድ ብሶታል ፣
"ይዘገያል " አሉ እያለ ያወራል ፤ ኃጢአት ይሸምታል።
እኔም በቀደም 'ለት ፤ ከደጀ ሰላሙ ብዙ ጉድ አይቼ፣
ገዛሁት በርካሽ ፤ ኃጢአትን ከደጅህ ፤ ከቤትህ አግኝቼ።
ግዴለም ንገረኝ ፤ ሃያው ይበቃኛል በሌላውስ ላትርፍ ፣
እንዴት ከሌላው ህዝብ ፤ እኔ ተለይቼ እንደ ጅል ልንከርፈፍ ?

   መቼ ትመጣለህ ነገ ወይስ ዛሬ?
                                     
ሌላውን ልበድል ፤ ነገርን ልዶልት ህዝብህንም ልቁጠር ፣
ከድንኳን ደጃፍ ፤ ተቀምጬ ላሹፍ ፤ ዘፈን ላንጎራጉር ።
ጊዜ ከሰጠኸኝ ፤ የምለይበትን ዘፈንን ከመዝሙር ፣
ንሰሐ ገባለሁ ልክ ስትመጣ ፤ ዛሬን ግን ልጨፍር።
ከጥብርያዶስ ባሕር ፤ ኃጢአት ዓሣን ላጥምድ፣
ትዘገይ እንደሆን ምናል ይህን ብትፈቅድ?
ይኸው ሰዉ ሁሉ ፤ ግራ ያጋባኛል ነገር እያማታ ፣
ኃጢአትን አግብቶ ፤ ትዳርን መስርቶ ጽድቅን እየፈታ ።
በክፋት ላይ ክፋት ፤ በዚያ ላይ ስምህን በፍፁም ደርቦ ፣
ጽድቅና ኃጢአትን ባንድ እያካሄደ በደስታ ተከቦ ፣
ጻድቅ ሲሸማቀቅ አንገቱን ሲደፋ ፤ ተመልካችም ሲያጣ ፣
እንዳሻው በመሆን ፤ ኃጥእ ሲዝናናበት ሲስቅ በለበጣ ።
ዘመናት አለፉ ፤ ይኸው ዛሬም የስምህ አጥፊዎች፣
ሥራቸውን ሰደው ፤ በደንብ ተስፋፍተው ዙሪያውን ብዙዎች ፣
ከደሃው ላይ ሰርቀው ፤ ምስኪን አስለቅሰው ለታቦት ሲያገቡ ፣
ወገን ጦሙን አድሮ ፤ ሲበሉ ሲጠጡ ሲያገቡ ሲጋቡ ።
እንኳንስ መምጣትህ ፤ ስምህ ተዘንግቶ አዳሜ ሲጨፍር ፣
እኔስ ምን ተዳዬ ፤ ከዚህ ህዝብ መሃል ተለይቼ ልቅር ?
ይልቅስ ንገረኝ ፤ ትመጣ እንደሆን ፀሐይ ሳትገባ ፣
አሊያም ልደባለቅ ከምድር ወገኖቼ ፤ ከወጣው ወጥቼ  ከገባው ጋር ልግባ ።
                            
  መቼ ትመጣለህ ነገ ወይስ ዛሬ?
                                    
የበራፌ ጥላ ከበር እስኪከተት ፤ 'ማትመጣ ከሆነ፣
አሸንክታብ ላርዝም ክብሬንም ልፈልግ ፤ ጊዜዬ ባከነ ፣
ዓለሙን ልከተል የዛሬን ልደሰት ፤ ነገ እመለሳለሁ ፣
አንተ ዛሬ ትመጣ ፤ ወይም እንደምትቀር በምን ዐውቀዋለሁ ?
ይኸው በዚህ ሰሞን ፤ ሰዎቹ በሙሉ ታሪክ ያወራሉ፣
እሱ ቀርቷል ብለው፣ ባንተም ላይ ደርበው ጣዖት ያመልካሉ።
ይኸው በዚያ ሰሞን ፤ ሥጋ ቤቱ ደጃፍ ሁሉ ተኮልኩሎ ፣  
በሁዳዴ ምድር ቁርጥ ያወራርዳል ፤ መስቀል አንጠልጥሎ ።
እኔስ አያምረኝም ? አንተ እንደው አትመጣ ፤ ብበላ ምናለ ፣
ጠበል እረጫለሁ ፤ ወደፊት ጾማለሁ አንተ ከዘገየህ ፣
እንዲሁ በከንቱ ጊዜ ከሚባክን ፤ ቅዳሴ አስቀድሼ ዳንኪራ ቤት ብሄድ    
ጽድቅን እንደሆነ ፤ መቼም አላጣትም ለኃጢአት ብሰደድ ፣
የልቤ ግድግዳ ቢጠቁር በክፋት ፤ ደግሞም ቢበሰብስ ፣
ዛሬ አንተ ካልመጣህ ነገ እታጠባለሁ ፤ ንሰሐ ሳሙና እስካለልኝ ድረስ!
ምናለ ብሳደብ ሌላውን ብጎዳ ፤ ማንም እናዳይነካኝ ፣
ግዴለም ለነገ ግራዬን ቢያጮሉኝ ፤ ቀኜን ሰጣለሁኝ።
እንደ  ሕፃን በርሬ ያሻኝ ቦታ ልድረስ ፤ ያሻኝን ልተንፍስ ፣
አኩኩሉ ልበል ፤ በኃጢአት ጫካ እስክትመጣ ድረስ ።

  መቼ ትመጣለህ ነገ ወይስ ዛሬ?
                                           
ምናለ እንደ ዴማስ ፤ ይህችን ዓለም ብወድ አንዴ ብተፈቅድልኝ ?
በኋላ መጣለሁ ልክ እንደ ድሮዬ ፤ አገለግላለሁ ቆመህ ከጠበከኝ።
ትዘገይ እንደሆን ፤ በቶሎ ማትመጣ አሊያ የምትቀር ፣
ምናል ሳማ ሰንበት ፤ ብሄድ ለሽርሽር ?
ቢራዬን ገዝቼ ፤ ቱታዬን አጥልቄ ፣
ልክ እንደ ቱሪስቶች ፤ ምግቤንም ሰንቄ ፣
በውጭዎች ፈሊጥ ፤ እየተቀናጣሁ ደርሼ ብመለስ፣
ምናለ ባልጸልይ ፤ ምናል ባላስቀድስ ?
ይኸው ትናንት እንኳ ፤ ትናንትና ማታ
ሰዎች ተኮልኩለው ፤ ከዐውደ ምሕረቱ ፣
አየሁኝ ሲጣሉ ፤ በቡድን ተከፍለው ነገር ሲዶልቱ።
እኔስ ምን አለበት ፤ በነሱ ብጽናና በኃጢአት ባድግ፣
አንተ እንደሁ አትመጣ ፤ ስንት ዘመን ሆነኝ ቆሜ ሳደገድግ ።
ፍጹም ልመሳሰል ከዚህ ዓለም ጋራ ፤ ማንነቴ ጠፍቶ ፣
አንተ ከዘገየህ ፤ ምናል ይህ አካሌ ቢኖር ሕይወት አጥቶ ?
ጊዜዬን ልስራበት ለኃጢአት ልነሣ ፤ ለጽድቅህም ሞቼ ፣
ክርስትናው እንደው መቼም አይቀርብኝ ፤
ነገ እቆርባለሁ በምርኩዝ መጥቼ ።

       መቼ ትመጣለህ ነገ ወይስ ዛሬ?
                           
ይኸውና ዛሬ ሁሉ ቀላል ሆኖ ፤ መፈራትህ ጠፍቶ ፣
የነዲዮስቆሮስ የነጴጥሮስ እምነት ፤ ከኋላ ተገፍቶ፣
ሰው ሰውን እያየ በሥጋ ሲጽናና ፤ አምላክን ረስቶ ፣
ከዐውደ ምሕረቱ አንተ ተሸፍነህ ፤ እኔን ስሙኝ በዝቶ ፣
እምነት እንደፋሽን ራሱን ተኩሎ ፤ ራሱን ቀብቶ ፣
በደፋሮች ጩኸት መቅደስህ ታውኮ ፤ መቅደስህ ሲረክስ ፣
ዐዋቂ አንገቱን በደፋበት መድረክ ፤ ታዋቂ ሲነግሥ።
ነጠላና ቀሚስ የጽድቅ መገለጫ ፤ በሆኑበት ዘመን፣
በስሜት ተነድቶ በስም ብቻ ሲሮጥ ፤ ህዝብህም ሲባዝን ፣
እኔስ ምን ተዳዬ ፤ ለግዜው ብደሰት ?
ሆ! ካለው ሆ ብዬ አብሬው ብዘምትም ፤ ሆሳዕና ብዬ ዛሬ ብዘምርም ፣
ከሳምንት በኋላ በዚያው አንደበቴ ፤ ይሰቀል !ይሰቀል! ማለቴ አይቀርም ።
እምነቱ ባይገባኝ ፤ እኔ ምን አገባኝ ?
ዝም ብዬ ሮጣለሁ
ምን ችግር አለበት አንተ ከዘገየህ ፣ ምስጢረ ሥላሴን ውዳሴ ማርያምን ፤
ቀስ ብዬ እማራለሁ ፣
አንተ እንደ ምትመጣ ፤ ወይ እንደ ምትቀር በምን ዐውቀዋለሁ ???????

@EMNFESAWItsufoche
1.3K viewsKalkidan, edited  16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 17:07:06 አምስተኛ ሰንበት(ሳምንት)
፨፨፨፨፨፨፨፨✞፨፨፨፨፨፨፨
ደብረ ዘይት ተብሎ ይታወቃል።
በዚህ ቀን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ስለመምጣቱ (ዳግም
ምፅአቱ) ይሰበካል። ይህን ዓለምንም አሳልፎ ለመረጣቸውና ላከበራቸው ዘላለማዊ
መንግሥትን ሊያወርሳቸው እንደሚመጣ ይነገርበታል። ይህ ቀንም እኩለ ፆም በመባል ደ/ሰ/መ/ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤ/ት/ክ
የሚታወቅ ሲሆን በዚህች በተለየች ቀንም ሁሉም እንደ የሥራው ፍርዱን ከአምላክ
የሚቀበልበት መሆኑ፤ መልካም ላደረጉ መልካም እንደሚመለስላቸው ክፉም ላደረጉ
የክፋታቸውን ዋጋ እንደሚያገኙ ይሰበካል። ጌታም የአባቴ ቡሩካን የተዘጋጀላችሁን
የክብር ቦታ ውረሱ በማለት ወዳጆቹን እንደሚጠራ ይነገራል።
ምስባኩም፦ መዝ.፵፱፡፫ ነው።
እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽዕ እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል
ወአምላክነሂ ኢያረምም አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ እሳት በፊቱ ይቃጠላል
ወንጌሉም ማቴ.፳፬፡፩-፴፮ ነው።
በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡት ጥቅሶችም፦
፩ተሰ.፬፡-፲፫-እስከ ፍጻሜ፤
፪ጴጥ.፫፡፯-፲፭፤
የሐዋ.ሥራ ፳፬፡፩-፳፪ ።

@MENFESAWItsufoche
1.3K viewsKalkidan, 14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 17:07:06
የዓብይ ጾም 5ኛ ስምንት

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
@MENFESAWItsufoche
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
1.2K viewsKalkidan, 14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 23:52:38 የምሰራች የምሰራች...      ለተዋህዶ ልጆች !


መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች መማር ይፈልጋሉ

 
እምቢልታ መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች  ማሰልጠኛ  ተቋም 

➜  በገ ና
➜  ክራር
➜ መሰንቆ
➜ ዋሽንት

   በሚፈልጉት ቀን እና ሰዓት  እንዲሁም በግል ቤት ለቤት  እናስተምራለን ! በተጭማሪ  ጥራት ያላቸው  የበገና , የክራር , መሰንቆ እንሸጣለን እናከፋፍላለን የክራር የበገና የመሰንቆ ቦርሳ እኛ ጋርም ያገኛሉ !


አድራሻችን  -  ጀሞ 1 ሩት የገበያ ማዕከል
                            
        Tel.  +251967437703
                     +251993945900


አሁኑኑ በዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉልን !

.
481 viewsመንፈሳዊ 3k, 20:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ