Get Mystery Box with random crypto!

*ማን እንዳቺ* ማን እንደ አንቺ ፈጥኖ ደራሽ ሰላማዊት ልብን አዳሽ አረጋጊ እንባን አባሽ፡፡ ማን | 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

*ማን እንዳቺ*
ማን እንደ አንቺ ፈጥኖ ደራሽ
ሰላማዊት ልብን አዳሽ
አረጋጊ እንባን አባሽ፡፡
ማን እንዳቺ አዛኝቱ
የአምላክ እናት ድንግሊቱ
አማላጅ ነሽ የፍጥረቱ
ሰውን መላሽ ከስህተቱ፡፡
ማን እንዳቺ የሚየፅናና
የሚያወጣ ከፈተና
ደግፎ ከቅፎ የሚያቀና
ማን እንዳቺ አስታራቂ
ሀጢአተኛን የማትንቂ
ጆሮ ዳባን የማታወቂ
መልካም ስራሽ አስደናቂ፡፡
ማን እንደ አንቺ መከለያ
ታማኝ እናት መጠለያ
ቀና መንገድ መታመኛ
የንስሀ በር መግቢያ፡፡
ማን እንደ አንቺ ተቆርቋሪ
የማታልፊ የሰው ጥሪ
አቤት ብለሽ አናጋሪ
ሰማያዊት ንግሰት የኛ አብሳሪ፡፡
ማን እንዳቺ ለወደቁት
አዛኝ አፅናኝ ንፁህ እንቁ
ሰው ረስቶአቸው ለተናቁት
በሀዘን መከራ ለወደቁት፡፡
ማን እንደ አንቺ የሚረዳ
የመትሞይ የሁሉን ጓዳ
እባክሽ አውጪን ከዓለም ፍዳ
ሁዋላ ጠፍተን እንዳንጎዳ፡፡
ፀበልሽ ፈዋሽ ያለዋጋ
ለእኛ እኮነሽ ባለ አደራ
እባክሽ አውጪን ከሐጢአት ተራ
እንድንኖር ከአንቺ ጋራ፡፡
መን እንደ አንቺ ያለው ለዛ
ንግግር የሚያዋዛ
በረከትን የሚያበዛ፡፡
ማን እንደ አንቺ ልዩ ስጦታ
አምላክ ያደለን የነፍስ እርካታ
ደስ አለን ዛሬ ዲያብሎስ ሲመታ
መግቢያ መውጪያ አጥቶ ሲሄድ በአንድ አፍታ
ስምሽ ግሩም ነው የህይወት ገበታ፡፡
ማን እንደ አንቺ ታምረኛ
የኔ ላሉሽ ምስጢረኛ
አማላጅ ነሽ እውነተኛ
ዛሬም እባክሽ ነይ ወደኛ
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
✞@MENFESAWItsufoche✞
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤