Get Mystery Box with random crypto!

ባሕራን ዐላማዬ ዕቅዴ፥ ቶሎ የምሮጥለት፤ በጉያዬ ይዤ፥ የምታትርለት፤ ለሕይወት እንደሆነ፥ አ | 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

ባሕራን

ዐላማዬ ዕቅዴ፥ ቶሎ የምሮጥለት፤
በጉያዬ ይዤ፥ የምታትርለት፤
ለሕይወት እንደሆነ፥ አለዚያም ለሞት፤
ከመንገዴ ቆመህ፥ እስቲ አምጣ በለኝ፤
አንባቢ ነህና፥ ለእኔም አንብብልኝ፤
አንድ አፍታ እፍ ብለህ፥ ክፉን ሰርዝልኝ፤
እኔም ባሕራን ነኝ፥ ከዓለም ያወጣኸኝ፡፡

ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ

@MENFESAWItsufoche