Get Mystery Box with random crypto!

እናቴ ስማፀን በስምሽ ድንግል ማርያም ብዬ ስማፀን በስምሽ በቅድመ እግዚአብሔር ልመናዬን አድር | 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

እናቴ ስማፀን በስምሽ

ድንግል ማርያም ብዬ ስማፀን በስምሽ
በቅድመ እግዚአብሔር ልመናዬን አድርሽ
እኔ ደካማ ነን ኃጢአቴ የበዛ
እኔ ጎስቋላ ነኝ በደሌ የበዛ
ጊዜዬን ያባከንኩ በዋዛ ፈዛዛ
ጊዜዬን ያባከንኩ በከንቱ በዋዛ
እመብርሃን ስልሽ ፈጥነሽ ድረሽልኝ
ልመናዬን ሰምተሽ ቆመሽ ለምኝልኝ
ኃጢአቴ ቢበዛም ይዣለው አንችን
አስምረሻልና በላዔ ሰብን
አንገቴን ቢያስደፋኝ በዝቶብኝ ኃጢአቴ
ምልጃሽን ፈለኩኝ ድንግል ሆይ እናቴ
ያን ክፉ ጨለማ እንዳላይ አደራ
ድንግል ሆይ ከልይኝ ከዲያብሎስ ጭፍራ
እመብርሃን እያልኩ ቆሜ ከደጅሽ
በብርሃን እጆችሽ እንባዬን አብሽ
አለም አታላይ ነች ወደሷ ተሳብኩኝ
ታማልጅኝ ብዬ አንቺኑ ተራብኩኝ

ከእህተ ማርያም
➴ ➴ ➴ ➴ ➴ ➴
@MENFESAWItsufoche