Get Mystery Box with random crypto!

* አርሴማ * አርሴማ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት(፪) ሞገስ አግኝተሻል በክርስቶስ ፊት ታምርሽ ልዩ | 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

* አርሴማ *

አርሴማ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት(፪)
ሞገስ አግኝተሻል በክርስቶስ ፊት

ታምርሽ ልዩ ነው....አርሴማ
ገድልሽአስደናቂ .....አርሴማ
ስምሽ ብርሃን ነው....አርሴማ
ማለዳ ፈንጣቂ ....አርሴማ

አዝ======

ስምሽን እየጠራ...አርሴማ
ጠግቧል የተራበው...አርሴማ
ምስኪኑም ዘመረ.....አርሴማ
ባንቺ አልፎ መከራው....አርሴማ

አዝ=====

ፅኑ ነው ኪዳንሽ....አርሴማ
የተሰጠሽ ከአምላክ....አርሴማ
በአይኔ አይቻለው...አርሴማ
ጠላት ሲንበረከክ....አርሴማ

አዝ=======

ዓለም ይስማው ዛሬ....አርሴማ
ዜና ተጋድሎሽን.....አርሴማ
ይገረም ይደነቅ....አርሴማ
ይመስክር ዝናሽን....አርሴማ

@MENFESAWItsufoche