Get Mystery Box with random crypto!

ፆም እንዴት ነው? ከእለታት አንድ ቀን አንድ ወጣት ወደ ነፍስ አባቱ ይሄድና ሰላም ካላቸው በ | 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

ፆም እንዴት ነው?

ከእለታት አንድ ቀን አንድ ወጣት ወደ ነፍስ አባቱ ይሄድና ሰላም ካላቸው በኃላ
ልጄ መንፈሳዊ ሂይወት እንዴት ነው?
ወጣቱም መልሶ በጣም ጥሩ ነው አባ።
ደስ ብሏቸው ጎሽ ልጄ በርታ እና ፆሙስ እንዴት ይዞሃል?
ወጣቱም አይ አባቴ ፆም እንኳን እየፆምኩ አይደለም።
ለምን ልጄ ምን ነካህ?
ወጣቱም አይ አባቴ ፆም ከገባ በኋላ ፍርጅ ውስጥ የነበረ ስጋ ወጥ ረሰቸው በላሁት ከዛም ያው አንዴ ሽርያለሁ ብየ አልፆምም።
የነፍስ አባቱም በጣም አዘኑና እህህህ ልጄ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?
ወጣቱም እሺ ይጠይቁኝ
እሳት አየሞክ እያለህ ሳታስበው በድንገት እግርህን ወደ እሳቱ ቢገባና እግርህ ቢቃጠል አንዴ ተቃጥያለው ብለህ ሳታወጣው ዝም ትላለህ ወይስ ታወጣዋለህ?
ወጣቱም በድንጋጤ እንዴ አባቴ ለምን ዝም እላለው ቶሎ ብዬ አውጥቼ በፍጥነት ወደ ህክምና ሄጄ እታከመዋለው።
ጥሩ ብለሃል ልጄ ፆምም አንዴ በልቻለው እያልክ መብላትህ ተገቢ አይደለም። ሃጥያትም ነው ልጄ ልክ ከእሳቱ እግርህን ቶሎ ብለህ አውጥተህ ወደ ህክምና እንደ ሄድክ ነፍስም ከቁስሏ ቶሎ ብለህ ከስህተት ተመልሰህ በፆም በጸሎት ማከም ይገባሃል ልጄ።በስህተት የሻርከውን ንስሐ ይሰጥህና የቀረውን መፆም ነው የሚገባህ ልጄ በስህተት ላይ ስህተት እየጨመርክ መንፈሳዊ ህይወትህ ማጥፋት የለብህም በማለት ቀኖና ሰጥተው ፆሙን እንዲፆም ነግረው አሰናበቱት።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
መልዕክት፦አብዛኞቻችን አንዴ ፆሙን ሽርያለው በሃጢአት ወድቅያለው ገና ወጣት ነኝ ነገ እሳሳታለው እያልን ብዙ ምክንያት እየደረደረን መንፈሳዊ ሂይወታችንን ረስተን በዝሙት በመጠጥ በጭፈራ በተለያዩ ወጥመድ ተይን ወጥተን የጠፋን ስንቶቻችን ነን ቤት ይቁጠረን። ቶሎ ብለን ዲያብሎስን ካልነቃንበት ህይወታችንን በማበላሸት ያጠፋናል።አንዴ ተሳስቻለው ብለን ሁሌም መሳሳት የለብንም በንስሃ ተመልሰን መልካሙን መንፈሳዊ ህይወታችንን እናጠናክር እንዲ እያሉ የሚገስጹ ደግ አባቶቻችንን ያብዛልን።
በንስሐ እንመለስ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
፨ከተስፋ ሚካኤል ሃይለ ማርያም

@MENFESAWItsufoche