Get Mystery Box with random crypto!

💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍ ስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የሰርጥ አድራሻ: @join_maryam_amalajinet_telegram
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.71K
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ቻናል አላማ ስለ ድንግል ማርያም,ፃድቃን,መላእክት እና ሰማእይታት አማላጅነትና ገድል ተአምራታቸውን እንዲሁም ክብራቸውን መመስከር ነው። ለህይወታችን ለሚገጥሙን ፈተናዎች አስተማሪና ጠቃሚ የሆኑ መልእክቶች ይገኙበታል።

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-03-07 11:03:42 ዐቢይ ጾም ሰኞ መጋቢት 2 ይገባል
በቤተክርስቲያን ስያሜ መሰረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፡-
ዘወረደ
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡

ቅድስት
ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን ቅድስት የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ስለዚህም ዕለተ ሰንበት ቅድስት ተብላለች፡፡

ምኩራብ
ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኩራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ይህች ዕለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ ገብቶ እንዳስተማረ የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ ምኩራብ ማለት የቤተ አይሁዳውያን የጸሎት ቤት ነው፡፡

መጻጉዕ
ይህ የአራተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ እውራንን ማብራቱ ለምጻምን ማንጻቱ ሽባዎችን መተርተሩ የሚያነሳ መዝሙር የሚዘመርበት እንዲሁም እነዚህ ሁሉ ድንቅ ገቢራተ ታምራቶች የሚዘከሩበት ዕለት ነው፡፡

ደብረ_ዘይት
ይህ የአምስተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ነገረ ምጽአቱን እንዳስተማረ የሚወሳበት ሰንበት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ማለት ወይራ የበዛበት ተራራ ማለት ነው፡፡

ገብርኄር
ይህ የስድስተኛው ሳምንት ሰንበት ስያሜ ሲሆን ይህም ዕለት ለጌታው ታማኝና በጎ የሆነው ባርያ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ተብሎ እንደተመሰገነ የሚነገርበት ዕለት ነው፡፡

ኒቆዲሞስ
ይህ የሰባተኛው ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ይህም ዕለት ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ መምህር በሌሊት ወደ ጌታው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየመጣ ይማር እንደነበረ ይታሰብበታል በዚም ዕለት የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡

ሆሳዕና
ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቷ እና በውርንጭላይቷ ላይ ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ እየተባለ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚተሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::
ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን፡፡
12.7K views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-25 21:03:49
ፆመ ነነዌ
ነብዩ ዮናስ ሦስት ቀንና ሌሊት በአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሰነበተ
፤ ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እንዲህም አለ።
፤ በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ እርሱም ሰማኝ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ፥ ቃሌንም አዳመጥህ።
፤ ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ፥ ፈሳሾችም በዙሪያዬ ነበሩ፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፉ።
፤ እኔም። ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ፤ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁ አልሁ።
፤ ውኆችም እስከ ነፍሴ ድረስ ከበቡኝ፤ ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ነበረ፤ የባሕሩ ሣር በራሴ ተጠምጥሞ ነበር።
፤ ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፤ በምድርና በመወርወሪያዎችዋ ለዘላለም ተዘጋሁ፤ አንተ ግን፥ አቤቱ አምላኬ፥ ሕይወቴን ከጕድጓዱ አወጣህ።
፤ ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ገባች።
፤ ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል።
፤ እኔ ግን በምስጋና ቃል እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እከፍላለሁ። ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
፤ እግዚአብሔርም ዓሣውን አዘዘው፥ እርሱም ዮናስን በየብስ ላይ ተፋው።
(ትንቢተ ዮናስ ምዕ. 2ቁ2-11)
በሦስተኛ ቀኑ ከነነዌ የባህር ዳርቻ ሲደርስ  ተፋው። እግዚአብሔርን አመሠገነ። ወደ ነነዌ ከተማ ገባ። ያለማይክ ሕዝቡን ሰበከ። ከህጻን እስከ አዋቂ፣ ከእንስሳ እስከ ሰው፣ ከሎሌ እስከ ንጉሥ ድረስ  አዳመጡት። በክፋታቸው ተጸጸቱ። ጾሙ፣ ራሳቸውን ስለ እግዚአብሔር አዋረዱ። እግዚአብሔርም ማራቸው። /

ነብዩ ዮናስ ሆይ ባንተ ስለሆነ ዳግም የኛ ተስፋ
አንዴ ተነስና ቀንደ መለከቱን በምድር ላይ ንፋ
የፍርድ ፅዋው ሞልቶ....
ዳግማዊ ነነዌ ኢትዮጵያ እንዳትጠፋ
12.6K views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-30 07:46:40 ጥር 21 ድንግል ማርያም በ 64 አመቷ ያረፈችበት እለት
የጥንት ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ እመቤታችን ዕረፍትና ትንሳኤ በዓይናቸው ያዩትንና የተማሩትን እንዲህ ይመሰክራሉ!
....................
1. # ኢቮድየስ_ዘአንጾኪያ (የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀመዝሙር) :- ይህ ታላቅ አባት ከጴጥሮስ ጋር አብሮ የነበረ፣ የድንግል ዕረፍትዋ በዓይኑ የተመለከተ፣ የትንሳኤዋም ሕያው ምስክር የሆነ ነው! ያየውምን ነገር በሙሉ "Homily on the Dormition of the falling asleep of Mary" በተባለው ክታቡ እንዲህ ይተርካናል!
...........
(ነሐሴ) ወር በአስራ ስድስተኛው ቀን ጠዋት በተመሳሳይ ምሽት በብርሃን ሰዓት፣ ጌታችን በታላቅ ክብር ወደኛ መጣ! ሰግደንም አመለክነው! ጌታም "ለምን ታዝናላችሁ?" ሲለን፣ አባቴ ጴጥሮስም "በእናትህና በሁላችን እመቤት ሞት፣ ከሞተችም ብኋላ ስጋዋን ስላላሳየሀን ነው" አለው! ጌታም ወደ መቃብሩ በመጣራት የድንግል እናቱን ስጋ በማስነሳት፣ ነፍስዋንም እንደገና ወደ ስጋዋ በማስገባት ልክ ቀድሞ በስጋ እንደምናውቃት በስጋ አየናት። መድኃኒታችንም ለስለስ ባለ ድምፅ "እነኋት ውድ እናቴን" አለን። ይህ የሁላችን እመቤት እና የወላዲተ አምላክ የሕይወትዋ መጨረሻው ይህ ነው በጦቢ(ጥር) ወር 21ኛ ቀን። ትንሳኤዋ ደግሞ በሜሶሪ (ነሐሴ) ወር በ16ኛው ቀን ነው> በማለት ከቀብሯ ተገኝቶ ትንሳኤዋን አይቶ ይመክረናል።
.............
2.ቅዱስ # ቴዎዶስዮስ_ዘእስክንድርያ (535 ዓ.ም)
አባታችን ቴዎዶስዮስ ስለ ትንሳኤዋ ሲንፕግረን <የነበሩበት ቦታ በእሳት ተሞላ። ጌታም በኪሩቤል ላይ ሆኖ የድንግልንም ነፍስ በእቅፉ በሰማያዊ ልብስ አጊጣ ይዟት ተገለጠ። ሐዋርያትም በፍርሐት ተሞልተው መሬት ላይ እንደ ሞቱ ሆኑ። እርሱ ፍርሐታቸውን አጥፍቶ እንዲህ አላቸው "እናንተ ደቀመዛሙርቴና ደናግል ሆይ፥ የእናቴን ክብር ታዩ ዘንድ ተነሱ።" እንዲህ ብሎም ወደመቃብሩ ጮሀ "ለእኔ መቅደስ የሆነሽኝ አንቺ ቅድስት ስጋ ሆይ፣ የእኔ የዘላለም ድንኳን የሆነችኝን ይህቺን ነፍስ ውሰጂ" ... ጌታ እነዚህን ቃላት ሲናገር መቃብሩ በዚያ ቅፅበት ተከፈተ... ከዚያም ብኋላ የከበረው የድንግል ስጋ ተነሳ፤ ነፍስዋንም አከበረቻት። ሁለት ወንድማማች ከተለያየ ሀገር እንድሚመጡ እንዲሁ ተባበሩ አንድም ሆኑ> ብሎ ወደ ትንሳኤዋ ይወስደናል።
.............
3.ቅዱስ # ዮሐንስ_ዘደማስቆ (675-749)
ይህ ቅዱስ አባትም <እርስዋ ልጅን ስትወልድ ድንግልናዋ እንደተጠበቀ እንዲሁ ስጋዋ ከሞትም ብኋላ ከመበስበስ የተጠበቀ ይሆን ዘንድ የተገባ ሆነ። ፈጣሪን በሕፃንነቱ በደረቷ እንዳቀፈችው እንዲሁ በመለኮታዊው ድንኳን (ሰማያዊ መቅደስ) ትኖር ዘንድ ተገባት! የእግዚአብሔር እናት የልጇ የሆነውን ነገር (ትንሳኤ) ታገኝ ዘንድ በፍጥረት ሁሉም የእግዚአብሔር እናትና አገልጋይ ተብላ ትመሰገን ዘንድ ሆነች> ይለናል።
.............
4.ቅዱስ # ጌርማነስ_ዘቁስጥንጥንያ (8ኛ ክ.ዘ)
ይህ አባት ደግሞ <አንቺኮ እንደ ተፃፈው በውበት የተገለጥሽ፣ ድንግል የሆነ ስጋሽም ቅዱስና ንጹሕ፣ መላውም የእግዚአብሔር ማደርያ ነው። ስለዚህም ጠቅልሎ አፈር ሆኖ ከመቅረት ነጻ ሆነ (ቀረ) ምንም እንኳን አሁንም ሰው ብትሆኚ ሥጋሽ ወደ ማይበሰብስ ሰማያዊ ሕይወት (አካል) ተቀየረ! አሁንም ስጋሽ በሕይወትና በክብር፣ ሳይጎድፍና ሳይጎድል በፍፁም ኑባሬ አለ!> እያለ ከእናቱ ከእናታችን ጋር ያወጋል። በአባቶቻችን እምነት ያፅናን!
.... የትንሳኤዋ በረከት ከወደቅንበት ኃጢኣት ያንሳን!
12.6K views04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-06 21:55:09
፤ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው።
፤ በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።
፤ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።
፤ መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
፤ ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።
፤ ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ።
፤ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።
፤ መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው። እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ ተባባሉ።
የሉቃስ ወንጌል ምዕ2 ቁ7-20
በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያላችሁ እህት ወንድሞቼ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ
13.0K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-29 05:43:28
19
መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ! አናንያን፣አዛርያን፣ሚሳኤልን ከሚነድ እሳት እንዳወጣሃቸው እኛንም ልጆችህን ከሚያስፈራን የሚያስጨንቀን ነገር ሁሉ ጠብቀን፣ ከገባንበት እሳት አውጣን አሜን!
በችግራችን ጊዜ ከሰው አለቃ ይልቅ የመላእክት አለቃ ከእሳት ከመከራ የሚያወጣው ቅዱስ ገብርኤል ይድረስልን።
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ
13.1K views02:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-17 09:04:47
ከበረታን
ሙሴ ፀሊም ምንኩስናን በጀመረበት ወቅት የአጋንንት ፆር ይበረታበታል ።ወደ አባ መቃርስም ሄዶ አባ አልቻልኩም አላቸው ። አባ መቃርስም የበቁ አባት ናቸውና ከፍ ወዳለ ተራራ ወስደው ወደ ቀኝ እይ ምን ይታይሀል ? አሉት ብዙ መላዕክት አላቸው

አሁን ደግሞ ወደ ግራ እይ ምን ይታይሀል ? አሉት ብዙ አጋንንት አላቸው አየህ ልጄ አንተ ከበረታህ መላዕክቱ ይረዱሀል አጋንንቱ ይሸሹሀል  ድል ታደርጋለህከደከምክ ደግሞ መላዕክቱ ይርቁሀል አጋንንቶቹ ድል ያደርጉሀል አሉት  ከዛን ጊዜ ጀምሮ ሙሴ ፀሊም በታላቅ ተጋድሎ በመጋደል አጋንንቱን ድል በማድረግ ታላቅ አባት ለመሆን በቃ

ዛሬ እኛም እንደዛው ነን ከበረታን እናሸንፉለን ከደከምን እንሸነፉለን ። ዛሬ ህይወት በትሯን እኛ ላይ በተደጋጋሚ ብታሳርፍብን እኛን ቅርፅ ለማስያዝ ነው አስታውስ አንድ የድንጋይ ሀውልት ያንን ቅርፁን የያዘው አናፂው በመዶሻ ስለቀጠቀጠው ነው  አንድ ካፒቴን ብቃቱ የሚታየው ማዕበል ሲመጣበት ነው ።

አንተም ብስለትህ የሚታየው በህይወትህ ውስጥ በሚመጣብህ መከራ ነው ችግሮች እንደ ኮፍያ ካንተ በላይ አታርጋቸው ይልቁንስ እንደ ጫማ ሶል ከእግርህ በታች አድርጋቸው መከራ ፈጣሪ ሰውን ወደ ራሱ የሚጎትትበት ገመድ ነው ። እግዚአብሔርን ይዞ ያፈረ የለም። እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው" ተብሎ ነው የተፃፈው ደሞም አስታውስ እንዲህም ተብሎ ተፅፏል "እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል እናንተም ዝም ትላላቹ " ።
ስለዚህ ወዳጄ በርታ
12.6K views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-13 06:23:59
እንኳን ለባእታ ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ
3
የብርኅን እናት
የከበበሽ ዕንቁ ብርሃን ከጨረቃ በላይ ይደምቃል ፣
የደምግባትሽ ጸዳል ከፀሐይ ያንፀባርቃል ።
ድንግል ሆይ ባህታውያን አለምን ጥለው መነኑ ፣
ከመቅደሱ ውስጥ ቢያገኙሽ በሀዘን ያሉት ተፅናኑ ።
መዓዛሽ የሚያረሰርስ የናርዶስ ሽቶ መጥመቂያ ፣
ለዘላለም የምትፈሺ የማየ ህይወት መፍለቂያ ፣
የድህነት መዝገብ ዶሴ የይቅርታ መጠየቂያ ፤
የአዲሲቷ ሠማይ ሚስጥር ያልተፈታሽ ድብቅ ቅኔ ፣
የአዳም ተስፋው ምልክት ነሽ ያወጣሽን ከኩነኔ ።
የመጎብኘት ምክንያት የሆንሽ የፍጥረት ሁሉ መዳኛ
የኖህ ቀስተ ዳመና የአርማው ቃል ኪዳን መገኛ ፣
የአልፋ ኦሜጋ ማደሪያ የሥላሴ መመስገኛ ፣
ማርያም ማርያም የምንልሽ እናታችን ነይ ወደ እኛ ።

ባዕታ ማርያም ሆይ ግና በልጅነትሽ አለምን ንቀሽ የአምላክ ማደሪያ ልትሆኚ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ
በንፅህናሽም መዓዛሽን የወደደ ወልድን ከመንበሩ
የሳብሽ በቅድስናሽም ለአዳም ተስፋ የሆንሽው
ትውልድ ሁሉ ብፅይት የሚልሽ እናቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ርስትሽ የምትሆን
የቃል ኪዳን ምድርሽን አስቢያት ። እኛ የአስራት ልጆቿንም ከጥፋት ሰውረሽ ከዚህ ዘመን ሞትና ፍጅት ለይተሽ በሠላምና በፀጥታ እናርፍ ዘንድ ከልጅሽ ከወዳጅሽ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኚልን ። አሜን አሜን አሜን ።
@ፍሠሐ ጽዮን
ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያግዝፉ
እንደ ዕብራዊያን ሴቶች በዋዛ በፈዛዛ
ያደግሽ አይደለሽም በንጽሕና
በቅድስና በቤተመቅደስ
ኖርሽ እንጅ
ባእታ ማርያም ምልጃዋ አይለየን አሜን
12.6K viewsedited  03:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-01 07:22:50
እንኳን ለፅዮን ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ።
የፅዮኗ እመቤት በያለንበት ፀሎት ልመናችንን ትስማን
13.2K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-22 06:33:08
እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ
የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ አይለየን
12.9K views03:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-25 09:53:23 "እግዚአብሔር ጠላቶችህን ከእግርህ በታች ያስገዛልህ!" አቡነ አረጋዊ።

የናግራን ሰማዕታትን በግፍ መገደል የመገልጽ ደብዳቤ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ኢትዮጵያው ንጉሥ ወደ ዐፄ ካሌብ ላኩለት፡፡ ዐፄ ካሌብም መልእክቱን ከተረዳ በኋላ ወደ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፣ ‹ፊንሐስ የተባለ አረማዊ የናግራን ክርስቲያኖችን ደም በከንቱ ያፈሰሰ፣ ቤተክርስቲያንን የመዘበረና ያጠፋ ፍጹም የእግዚአብሔር ጠላት ወደሚሆን ሄጄ እዋጋው ዘንድ ተዘጋጅቻለሁ፡፡ ስለዚህ አባቴ ሆይ! አንተም በበኩልህ ጸሎት አድርግልኝ፣ የጻዲቅ ጸሎት ትራዳለች፣ ኃይልንም ታሰጣለች፣ በጠላት ላይ ድልንም ታቀዳጃለችና› ሲል ላከበት፡፡

አባታችን አቡነ አረጋዊም ለንጉሡ ጭፍሮች ‹ወደ ጦሩ ግንባር ሂድ፣ እግዚአብሔር ጠላቶችህን ከእግርህ በታች ያስገዛልህ፣ ለአንተም ግርማ ሞገስ ይስጥህ፣ በሰላም ይመልስህ› ብለው መርቀው ሸኝተውታል፡፡ ዐፄ ካሌብም ወደ ናግራን ዘምቶ ከሓ'*ዲ*'ውን የአይሁድ ንጉሥ ፊንሐስን ከገደለውና ጦሩን ሁሉ ደምስሶ በማጥፋት የክርስቲያኖቹን ደም በሚገባ ተበቀለ፡፡ በአንጾኪያ፣ በእስክንድሪያ፣ በሮም፣ በቊስጥንጥንያና በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ ይህን ሲሰሙ በእጅጉ ተደሰቱ፡፡ ይህም የሆነው በ525 ዓ.ም ነው፡፡

ዐፄ ካሌብ ወደ አቡነ አረጋዊ "የእግዚአብሔርን ጠላት ሔጄ እዋጋው ዘንድ ተዘጋጅቻለሁና አባቴ በጸሎት አስቡኝ" በማለት መልእከት ሲልክባቸው እርሳቸውም የሰጡት መልስ "እግዚአብሔር ጠላቶችህን ከእግርህ በታች ያስገዛልህ!" የሚል ነበር። የእነ ዐፄ ካሌብ የእነ አቡነ አረጋዊ አምላክ የቅድስት ኢትዮጵያን ጠላቶች አጥፍቶ ትንሣኤዋን ያሳየን።

"እግዚአብሔር ደብረ ሃሌሉያ የተባለች ደብረ ዳሞን መርጧታልና ለአቡነ አረጋዊ ማደሪያው ትሆን ዘንድ ወዷታልና እርሷ ለዘለዓለሙ ማደሪያውና መሠወሪያው ናት" ቅዱስ ያሬድ ለደብረ ዳሞ የዘመረላት ዝማሬ ነው።

አቡነ አረጋዊ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብርሃኗ የሆነ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ እና ንጉሥ በዐፄ ገብረ መስቀል ሦስቱ ቅዱሳን አብረው ብዙ ታሪኮችን ፈጽመዋል፡፡ ገዳማትን ላይ በመዟዟር ቅዱስ ያሬድ ዜማን ሲያስተምር ንጉሡ ደግሞ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ ያስፋፉና ቋሚ መተዳደሪያ ይሰጡ ገዳማቱን ያጠናክሩ ነበር፡፡ አቡነ አረጋዊ ደግሞ አብረው ምኩስናን ያስፋፉ ነበር፡፡ ሦስቱም ይህን ተግባራዊ እንዳደረጉ ለማሳያ ይሆን ይሆን ዘንድ ቅዱስ ያሬድ 3 ዓመት ዝማሬ መዋሥዕት ያስተማረባትንና ዛሬም ድረስ ማስመስከሪያ የሆነችውን እጅግ ጥንታዊቷን ዙር አባ ጽርዓ አርያም አቡነ አረጋዊ ገዳም አንዷ ናት።

@ ከገድላት አንደበት
12.9K views06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ