Get Mystery Box with random crypto!

💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የሰርጥ አድራሻ: @join_maryam_amalajinet_telegram
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.51K
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ቻናል አላማ ስለ ድንግል ማርያም,ፃድቃን,መላእክት እና ሰማእይታት አማላጅነትና ገድል ተአምራታቸውን እንዲሁም ክብራቸውን መመስከር ነው። ለህይወታችን ለሚገጥሙን ፈተናዎች አስተማሪና ጠቃሚ የሆኑ መልእክቶች ይገኙበታል።

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-16 03:51:46
መቃብሩ በፈርጣማ ወታደሮች ተጠበቀ። በትላልቅ ደጎራ ተዘጋ።
አይሁዶች በደስታ ሰከሩ። ፖለቲከኞች በፍርዳቸው እረኩ።
እናቱ እንባዋ እንደ ጅረት ፈሰሰ። ሐዋርያት የሀዘን ደመና ከበባቸው። ከበረከቱ፣ ከፈውሱ የተጠቀሙት ሕዝቦች በአምላክነቱ ተጠራጠሩ። ጥቂቶቹ በሀሰት በመገደሉ አለቀሱ።
እውነት በዝምታ ተቀበረች።
ነገር ግን ሙታንን የሚያስነሳው አምላክ መቃብሩን ፈንቅሎ ወጣ -
እሁድ ሌሊት 6:00።
የአርብ ልቅሶ በእሁድ ደስታ ተሻረ። የወላጅ እናቱ የጠነከረ ሀዘኗ እንደ ጤዛ ተነነ። ሐዋርያት በደስታ ተሰባበቡ። የተጠራጠሩት ወደ ማመን ተመለሱ። የተቀበረችው እውነት ተገለጠች።
በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም እምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች የድንግል ማርያም ወዳጆች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ
3.7K views00:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 15:57:44
ተፈፀመ
" ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 19:30)
2.9K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 14:03:17
ጌታዬ ሆይ! ልዑል አምላክ ስትሆን ዝቅ ብለህ የእኔን የባርያህን እግር ልታጥብ ፈቀድክን? እንግዲያውስ እጄንና ራሴን ጭምር እንጂ እግሬን ብቻ አትጠብ። አባቴ ሆይ የቆሸሸው ልቤን፥ ያደፈችው ነፍሴን መላ አካላቴን እጠበኝ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም።
3.1K views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 09:41:39
ተወዳጅ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይቺ ዓለም እውነታና ፍርድን ፊት እያየች ለምታቀው እየደበቀች፣ ለማታቀው በአደባባይ ፀሐይ እያሰጣች የምትኖር ከንቱ ናትና እውነት እራሷ ሆይ አንተ ብቻ አሰማራኝ፤ አንተ ፍርድህ አይዛባም፣ ለተበደለም ደስታ፣ ለበዳይም መልስ አለህና ፍትህ ሁሉ ካንተ ይጠበቅ፤ በውሸተኛው ሰው መሃል ፍትህ መጠበቅ ለራስ መቀለድ ነው:: በቃ ማሰማሪያዬ ሁነኝ፣ የልቤ ናፍቆት ነህና ሁሌም በስምህ እንደ ዶኪማስ ሰርግ አረግበታለው፤ አንተም በታመንኩበት ስምህ በእናትህ ጥዑም ምልጃ ከውስጤ የነፍሴ የድንጋይ ጋን ያለውን መናኛ ወይን አንጠፍጥፈህ ከኔ አልፎ ለሰዎች ተርፎ ይጣፍጥ:: በብርቱ የምተማመንብህ፣ ስደገፍህ የማጥለኝ፣ እያሞገስክ የማሰድበኝ፣ የውጪ አልጋ የቤቱ ውስጥ ቀጋ የማትሆንብኝ፣ ሰላምህን በላዬ ላይ የምታፈስብኝ፣ በብቸኝነቴ ሞገስ ሆነህ ግር ብዬ የምኖርብህ፣ እስከ ጥግ መተህ ፈልገህ ከሞት ያወጣኸኝ አንተ እኮ አንተ ነህ::
ቸሩ አምላካችን ከክፉ ጠላት ይጠብቀን
1.2K views06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 20:38:33
ሆሳዕናችን ሆይ
በአህያዋ ጀርባ የተመለከቱህ
አዳኝ መድሐኒት እንደሆንክ ያወቁህ
ክብር በአርያም ብለው ሆሳዕና
ህጻናት አዛውንት በጥዑም በምስጋና፣
ልብስ እና ዘንባባ እያነጠፉልህ
ብሩክ ነህ ዘለዓለም ብለው ተከተሉህ፤
እንዳይዘምሩልህ ቢያደርጉም ከልካዩች
አንተን ለማመስገን ዘለሉ ደንጋዮች።
ግባ ወደ ልቤ ግባ ኢየሩሳሌም
ታስፈልገኛለህ መድኃኒቴ ለእኔም
ሆሳዕና እንዳልል ክብር በአርያም
ስምህን መስክሬ እንዳላገኝ ሰላም
አስሮኛል ኃጥያት በደል ክህደቱ
ተፈትቼ ልምጣ እንደ አህያይቱ
ይሸከምህ ጌታ የልቤ ትከሻ
አንተን ብቻ ያንግስ እስከመጨረሻ
ቆመህ ስታንኳኳ ልክፈተው ደጃፉን
የክብር ንጉስ ሆይ ኑርበት እልፍኙን
ይሁንልህ ዙፋን እረፍበት ግባ
እንዲመችህ ላንጥፍ የእምነት ዘንባባ
ሆሳዕናችን ሆይ ትብዛ አሜናችን
ክብር እና ምስጋና ይድረስህ ጌታችን።
2.8K views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 07:58:31 27
መድሃኒዓለም ሆይ ሰዎች አላዩኝም ብዬ የሰራሁትን ገመናዬን ከአንተ በቀር ያየ እንደሌለ በሙሉ ልቤ አምናለሁ፡፡
አማኑኤል ሆይ ቻይ እንደሆንክ አዉቅ ሀሳብህም ሁሉ ይሆን ዘንድ ከቶ እንደማይከለከል በአለማት ላይ አንተ ብቻ እንደሰለጠንክ የሁሉ ፍጥረታት ስራ አስኪያጅ እንደሆንክ ያለጥርጥር በሙሉ ልቤ አምናለሁ፡፡
ዉዴ የህይወቴ አባት ካንተ ሌላ ሳለቅስ እንባዬን የሚያብስ፣ስወድቅ የሚያነሳኝ፣ስራብ የሚያበላኝ፣ስጠማ የሚያጠጣኝ፣ስጠፋ የሚፈልገኝ፣ስጨነቅ የሚደርስልኝ፣አንገቴን ስደፋ ቀና የሚያደርገኝ
ካንተ በቀር ማንም እንደሌለኝ አዉቃለሁ፡፡
መድሃኒዓለም ሆይ
ሌትተቀን እንደ ንስር እናት የምትጠብቀኝ እና የምታየኝ -አቤቱ እንዴት ባለ አንደበት ላመስግንህ....
በአንድ ነገር ተስፋ አለኝ እሱም አንተ ዘወትር ከኔጋ ነህ.
የቸሩ መድሃኒአለም አብሮነት ለዘወትር አይለየን
2.5K views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 21:53:09
7ኛ ሳምንት ኒቆዲሞስ
በዚህ ሳምንት እንደ ኒቆዲሞስ ያሉ
ዓለማዊ የመሠሉ ጠንካራ  ክርስቲያኖች ይዘከራሉ።
ኒቆዲሞስ ምሁር ነው፤ ባለሥልጣን ነው፤ ሀብታም ነው።
የፈሪሳዊ ዘር ሆኖ ክፋት አላሸነፈውም።
ቀን ዓለማዊ ሥራውን እየሰራ ሌሊት ወደ ክርስቶስ እየሄደ ሃይማኖትን ይማራል። 
እውቀቱ፣ ሥልጣኑ፣ ሀብቱ ... ለሃይማኖቱ እንቅፋት አልሆኑትም።
ሥልጣን ሲይዝ የሚመራውን ሕዝብ ራሱ  የፈጠረ የሚመስለው፣
በገንዘቡ ሰውን ሁሉ የሚገዛ የሚመስለው፣ በእውቀቱ ፈጣሪን ያወቀ የሚመስለው ፣
በበዛበት ዓለም ክርስቲያን ሆኖ መገኘት መታደል ነው።
2.6K views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 06:24:19
ድንግል ሆይ ምስጋናሽ በሁሉ መላ ውዳሴሽም በዓለም ዳርቻ ሁሉ ሰፈፈ የውቅያኖስ ባሕር በመደቡ የተወሰነ ነው ፣ የሐኖስም ባሕር እንደ መጠኑ ልክ አለው ያንቺ ምሥጋና ግን ልክ፣ወሰን፣ሥፍር፣ቁጥር፣ማለቂያ የለውም ፤ አዕምሮ ሊወስነው፣አንደበት ተናግሮ ሊፈጽመው አይችልም፡፡ በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ ሁሉ ላንቺ ሆነ ፣ ሁሉ ስላንቺ ተፈጠረ፡፡ አዳም ከኅቱም ምድር የተፈጠረ አንቺን ያፈራ ዘንድ ነው፡፡ ሔዋንም ከአዳም ጎን የተፈጠረች አንቺን ትወልድ ዘንድ ነውና›› ፡፡
(አርጋኖን ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)
3.6K views03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 11:12:23 የፖለቲካ ፓርቲ የአባላት ብዛትን ይፈልጋሉ።
እግዚአብሔር ግን አንድም ቢሆን  ንጹህ ልብ ብቻ ይፈልጋል። 
ከሰባ ትካት ኖህን ብቻ መረጠ።
ከሶዶሞ  ከተማ ሎጥን ብቻ  መረጠ።
ከምድረ ግብጽ ሙሴን ብቻ መረጠ።
የነነዌን ሕዝብ ለማዳን አንድ ዮናስ ብቻ ተመረጠ።
የከተማዋን ሕዝብ አልፎ አንዲት ሳምራዊት ሴት ብቻ አነጋገረ።
2.9K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 16:01:36 " የዚህ ዓለም ኑሮ እንደ እንቅልፍ ነው ። በዚህ ሕይወት የሚሆኑት ሁሉ ሕልም ናቸው ።
በሕልምህ ባለጸጋ ብትሆን ምን ጥቅም አለው? በእንቅልፍ ልብ ሆኖ በቅዠት የሚናገር ሰው ስለ ንግግሩ አይፈረድበትም ። እኛ ግን በዚህ የእንቅልፍ ዘመን የምንናገረው ሁሉ የዘላለም ሕይወትን ሊያሳጣን ይችላል"

"በድህነት እና በረሃብ የሚሰቃዩ ሰዎች እንደ ሰለስቱ ደቂቅ ናቸው ። ከድህነት የበለጠ ምን እሳት አለ? ከረሃብስ የሚበልጥ ምን ነበልባል አለ?
ሶስቱ ወጣቶች እሳት ውስጥ ሆነው እንደዘመሩ በመከራ ውስጥ ሆኖ ፈጣሪን የሚያመሰግን ሰው የመከራው እሳት ውኃ ይሆንለታል ለድሆች ምጽዋትን የሚሰጥ ሰው ደግሞ ሰለስቱ ደቂቅን ከእሳት የታደገውን የእግዚአብሔር መልአክን ይመስለዋል!"

"አንድ ሰው እኔ ክርስቲያን ነኝ ሲል በአንድ ቃል ዜግነቱንና ቤተሰቡን ስራውን ጠቅልሎ ተናገረ ማለት ነው የሚያምን ሰው ከሰማያዊት ኢየሩሳሌም በቀር ምድራዊ ከተማ የለውም "

በትንንሽ ነገሮች ማመስገንን ከለመድህ ትንንሽ ነገሮች ብዙ ስለሆኑ ሕይወትህ ምስጋና ይሆናል"

" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "
961 views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ