Get Mystery Box with random crypto!

💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የሰርጥ አድራሻ: @join_maryam_amalajinet_telegram
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.51K
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ቻናል አላማ ስለ ድንግል ማርያም,ፃድቃን,መላእክት እና ሰማእይታት አማላጅነትና ገድል ተአምራታቸውን እንዲሁም ክብራቸውን መመስከር ነው። ለህይወታችን ለሚገጥሙን ፈተናዎች አስተማሪና ጠቃሚ የሆኑ መልእክቶች ይገኙበታል።

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-01-07 07:50:33
፤ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው።
፤ በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።
፤ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።
፤ መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
፤ ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።
፤ ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ።
፤ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።
፤ መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው። እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ ተባባሉ።
የሉቃስ ወንጌል ምዕ2 ቁ7-20
በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያላችሁ እህት ወንድሞቼ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ
3.3K views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-02 08:31:01

ተክለ ሃይማኖት ሆይ፤ በቀኝ ጎንህ ሦስት በግራ ጎንህ ሦስት ሆነው ለሠረፁት 6ቱ አክናፎችህ ሰላም እላለሁ፡፡
ቅዱሱ አባት ሆይ፤ እኔ ልጅህ የአንተን በረከት እፈልጋለሁና የቀን ጉዳይ ጥሎኝ ለእርዳታ በምፈልግህ ጊዜ በነዚያ በክንፎችህ ፈጥነህ ድረስልኝ፡፡
መልክአ አቡነ ተክለሃይማኖት
የተክልዬ ምልጃና በረከት አይለየን
2.0K views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 10:42:08
ጸጋን የተመላሽ ሆይ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ትለምኝልን ዘንድ ላንቺ ይገባል አንቺ ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጫለሽ ከነቢያትም ከመምህራንም ትበልጫለሽ። ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ። በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ! ለሰውነታችንም ሕይወትን የምትለምኝልን ነሽ፤ ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምኝልን እርሱን በማመን በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ ይቅርታውንና ምሕረቱን ይሰጠን ዘንድ በቸርነቱ ብዛት ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ቅድስት ሆይ ለምኝልን
3.0K views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 08:30:34
በመልአከ ሞት ከመውደቅ የምትታደግ ገብርኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። አማላጅነትህን በመታመን ተስፋ እናደርጋለንና በመዓልትም በሌሊትም አንተ ጠብቀን
ገብርኤል ሆይ ከሰው ወገን ከቶ ጠዋትና ማታ እንደኔ ኀዘንና ትካዜ የሚበዛበት የለም። ከመላእክትም ወገን እንዳንተ ያዘኑትን የሚያረጋጋ የለም። ገብርኤል ሆይ ስለዚህ እኔም አውቄና አንተን አምኜ። ይህን ያቀረብኩልህን ጸሎት እንደትልቅ ዋጋ ቆጥረህ የማረጋጋት ቃለህን አሰማኝ።
መልክአ ገብርኤል
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ
4.1K views05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 22:45:40 ስታገኝና ስታጣ፣
ስትሾምና ስትሻር፣
ስትቆምና ስትታመም፣
ስትደግስና ስትቸገር
የሚያጅቡህ ሰዎች
ቁጥራቸውም ዓይነታቸውም ይለያያል።
4.3K views19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 17:50:44
የቀደሙት ኣባቶቻችን ጥቁር ውሻ ይግዛህ ብለው ይረግሙ ነበረ ፡፡
እርግማኑ እውን እንዳይሆን እንጸልይ
3.0K viewsedited  14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 07:32:20
እንኳን ለፅዮን ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ
1.7K views04:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 07:20:28
ገብርኤል ሆይ ከሰው ወገን ከቶ ጠዋትና ማታ እንደኔ ኀዘንና ትካዜ የሚበዛበት የለም። ከመላእክትም ወገን እንዳንተ ያዘኑትን የሚያረጋጋ የለም።
ገብርኤል ሆይ ስለዚህ እኔም አውቄና አንተን አምኜ። ይህን ያቀረብኩልህን ጸሎት እንደትልቅ ዋጋ ቆጥረህ የማረጋጋት ቃለህን አሰማኝ።
መልክአ ገብርኤል
1.2K views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 07:20:50
እመቤቴ ኪዳነምህረት ሆይ፤ በብርሃናዊው ኮከብ ለተመሰለው ስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል፤ በጨለማ ለሚኖሩ ሕዝቦች ብርሃኑን አብርቶላቸዋልና፡፡
የቃል ኪዳኗ እመቤት ሆይ፡የአምላክ ቃል ኪዳኑ መዛግብት በዕለተ ዓርብ የተገኘው የደህንነታችን ተስፋ ያስገኘሽ ዕውነተኛ መዝገብ እኮ ነሽ፡፡ አባታችን ቀዳማዊ አዳም በጭንቅና በኃዘን ከገነት በተሰደደ ጊዜ ከልቦናው ኃዘን ተረጋግቶብሻልና፡፡
(መልክአ ኪዳነ ምህረት)
ኪዳነ ምህረት እኛንም ከሀዘን ከመከራ ታውጣን
2.9K views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 06:03:18 ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡

ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡ በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡
2.2K views03:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ