Get Mystery Box with random crypto!

💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የሰርጥ አድራሻ: @join_maryam_amalajinet_telegram
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.51K
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ቻናል አላማ ስለ ድንግል ማርያም,ፃድቃን,መላእክት እና ሰማእይታት አማላጅነትና ገድል ተአምራታቸውን እንዲሁም ክብራቸውን መመስከር ነው። ለህይወታችን ለሚገጥሙን ፈተናዎች አስተማሪና ጠቃሚ የሆኑ መልእክቶች ይገኙበታል።

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-09-27 10:36:28
በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም እምትገኙ የተዋህዶ ልጆች
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
2.6K views07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 07:27:04 16
ድንግል ሆይ
ከልጅሽ ሌላ ባለመድኃኒት አልሻም፡፡ ከጸሎትሽም ረዳትነት በቀር ደግሞ ኃጢአቴን የሚያስተሠርይልኝ አልፈልግም፡፡ ንጽሕት ሆይ ከርኩሰቴም ከዕዳ በደሌም ሁሉ ንጹሕ አድርጊኝ፡፡ ከሥጋና ከነፍስ ቁስሌም ፈውሽኝ፡፡
ለደዌ መድኃኒት ይሹለታል፤ ለቁስልም አቃቂር መልካሙን ቅመም ይፈልጉለታል፤ የኃጢአት ቁስል ግን ያለ ልጅሽ ፈቃድ አይጠገንም፡፡
በዕብራይስጥ ማሪያም የተባልሽ የተመረጥሽ ደንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ! የደናግል መመኪያ የቅዱሳንም ሁሉ የመመረጣቸው አክሊል ኃጢአቴን እንደ ነጭ ሐር ግምጃ ንጹሕ አድርጊው ዕዳ በደሌንም እንደ በረድ ነጭ አድርጊው፡፡
ጸሎቴም ወደ ልጅሽ ፊት ትግባ፡፡ በልጅሽም በወዳጅሽም ጆሮ የተሰማች እርሱም የተቀበላት ትሆን ዘንድ ባንቺ ፊት እማለላለሁ፡፡ ከልጅሽም ዘንድ ለኃጢአቴ ሥርየት እሻለሁ፡፡
በየሰዓቱም በየጊዜውም ለማኅፀንሽ ፍሬ ይቅርታ መምጣት ደጅ እጠናለሁ፡፡ ልጅሽም እንደ በደሌ ቢበቀለኝ እንደ ሥራዬም ቢከፍለኝ አንዲት ሰዓት ለመቆም የተገባሁ ባልሆንኩም ነበር፡፡
ነገር ግን የጸሎትሽ ረዳትነት የልጅሽም ይቅርታው በየዕለቱ በየዘመኑ ሁሉ ይከራከርልኛል፡፡ ስለዚህ አልፈራም ምንም ምድር ብትናወጽ ተራሮችም በምድር ላይ ቢናወፁ ባንቺ ምልጃ እድናለሁና አልፈራም።
የኪዳነምህረት ምልጃ ለዘወትር አይለየን
2.5K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 08:00:27
ሁሌም ቢሆን ጥቁር ብቻ መስሎ ከሚታይህ ቀን ጀርባ የታዘለ ደማቅ ብርሃን አለ ሊገፈትሩህ ከበረቱ እልፍ ክንዶች ኋላ ሊያቀሙህ የቆሙ ልስልስ መዳፎች አሉ አንሸራትተው ከሚደፉህ ሃሳቦች ባሻገር በተስፋ ሞልተው የሚያቆሙህ ቅን ሀሳቦች ተሰልፈዋል ያላየኸው ነገ ብዙ አዲስ የህይወት ገፆችን ይዞ ይጠብቅሃል ካጎነበስክበት ቀና ትላለህ ሀዘንህ በሳቅ ይተካል ጉስቁልናህን ወዝ ይሽረዋል ይህ እንዲሆን ግን ነገን ጠብቀው አሊያም ተስፋ አትቁረጥ ነገ ያንተ ሲሆን ብቻ አሸናፊ ነህ::
3.3K views05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 19:33:34
የመስቀሉ ኃይል እንደ ምን ይደንቅ? በሰው ልጆች ዘንድ በመስቀሉ ኃይል የኾነው የተደረገው ለውጥ እንደ ምን ይረቅ? ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን አውጥቶናልና፤ ከሞት ወደ ዘለዓለም ሕይወት መልሶናልና፤ ከዘለዓለም ጥፋት ወደ ዘለዓለም ልማት አሸጋግሮናልና፡፡
በመስቀሉ ያልተደረገልን በጎ ነገርስ ምን አለ? ምክንያቱም በመስቀሉ ርትዕት ሃይማኖትን ዐወቅን፤ የእግዚአብሔር የጸጋውን ብዛት ተረዳን፡፡ በመስቀሉ ስለ እግዚአብሔር እውነት የኾነውን ዐወቅን፡፡ በመስቀሉ፥ ርቀን የነበርን እኛ ሕዋሳተ ክርስቶስ እስከ መኾን ደርሰን የቀረብን ኾንን፡፡ በመስቀሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተካፋይ የመኾን መብት (ሥልጣን) አገኘን፡፡
በመስቀሉ የፍቅርን ኃያልነት ዐወቅን፡፡ በመስቀሉ ለሌሎች መሞትን ተማርን፡፡ በመስቀሉ ንቀት፣ ውርደት፣ መከራ ማለት ምን ማለት እንደ ኾነ ዐወቅን፡፡ ጊዜያዊ ያይደለ የዘለዓለም በረከት ምንጭ መኾኑን ተረዳን፤ የማይታየውን እንደሚታይ አድርገን ተቀበልን፡፡
በመስቀሉ የተሰቀለው ይሰበካል፤ በእግዚአብሔር ማመንን እውነትም ለዓለም ኹሉ ይነገራል፡፡ በመስቀሉ የተሰቀለው ክርስቶስ ይሰበካል፤ በትንሣኤ ማመንንና በላይ በሰማያት ያለችውንም ሕይወት መንግሥተ ሰማያትም በእውነት ያለ ሐሰት ያለ ጥርጥር ይሰበካል፡፡
ከመስቀሉ በላይ የከበረ፣ ለነፍስም ድኅነትን የሚሰጣት ምን አለ? መስቀል አጋንንት ድል የተነሡበት ነው፡፡ መስቀል የኃጢአት ድል መንሻ የጦር ዕቃ ነው፡፡ መስቀል ጌታችን እባቡን የመታበት ሰይፍ ነው፡፡
መስቀል የአብ ፈቃድ፣ የወልድ ክብር፣ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ፣ የመላእክት ጌጥ፣ የቤተ ክርስቲያን አጥር፣ የቅዱስ ጳውሎስ ውዳሴ፣ የቅዱሳን ጋሻ፣ የዓለምም ብርሃን ነው፡፡
8.7K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 23:28:48
እንኳን ከዘመነ ማርቆስ
ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገራችሁ
2015 የሀዘን ሳይሆን የደስታ ዜናን እምንሰማበት
ከክፉ ምኞት በስተቀር ምኞታችን እውን እሚሆንበት ያድርግልን
5.2K views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 06:56:18
ቅዱስ እሩፋኤል እንኳን አደረሳችሁ
ከባህሪው ቅድስና ፍጥረቱን በጸጋ ቅድስና መርጦ የሚለይ እግዚአብሔር አክብሮ እንዲህ ያለ ሰማያዊ ፀጋ ከሰጣቸው ቅዱሳን መላእክት መካከል በስልጣኑ ሊቀመናብርት (የመናብርት አለቃ) የሆነ በሹመት ፈታሔ ማኅጸን (ማሕጸን የሚፈታ) ከሳቴ እውራን (የእውራንን ዓይን የሚያበራ) ሰዳዴ አጋንንት (አጋንንትን የሚያባርር) ፈዋሴ ዱያን (ድውያንን የሚፈውስ)፣ አቃቤ ኆኅት (የምህረትን ደጁ የሚጠብቅ) ተብሎ የተገለጠ ከሊቃነ መላእክቱ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ተከትሎ የሚነሳ መልአክ ራሱን እንዲህ በማለት ገለጠ « የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነት ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ» (ጦቢ.12÷15)
ከመልአኩ ከቅዱስ ሩፋኤል ረድኤት ያሳድርብን አሜን !
9.1K views03:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 07:17:58 #ተወዳጅ #አምላክ #ክርስቶስ ሆይ በራሱ ጥቁር ጥላ ሥር ሆኖ የሌላው ብርሃን አይታየኝም እንደሚል ሰው እንዳልሆን ጠብቀኝ፤ ሁሉም ኮርቻውን እንደሚጭንበት ፈረስ ጀርባዬ በትህትና ለሁሉም ይጎንበስ፤ የሥጋ ሆድ ፍጻሜ ድረስ ብቻ አልከተልህ፤ ካሳው ጀርባው ያለው መከራህን ልገኝበት፤ የሕይወቴ አላማ አሳ ለመብላት፣ ተዓምር ለማየት፣ ደምግባትህን ለማድነቅ፣ አንተን ለመፈተን፣ ግፊያ ብቻ መጋፋት አይሁን፤ ፈጣሪዬ ሆይ በእባብ ትምህርት ተነድፈን አንተ ሞክረህ ያልተሳካልህ ፍጹም ደግ ሆነህ ደግ ማፍራት እኔ ምን ብዬ እነካካዋለውና ለራሴም እንኳ የማይተርፈውን እኔነቴን አስብልኝ፤ ታጥቦ ከተሰጣበት ገመድ እንደ ጠፋ ልብስ በደምህ ያጠብካት ነፍስ ልብሴ በሥጋ ምኞት ጠፍታለችና ሥጋዬ ገርተህ የነፍስ ሥራ መፈጸሚያ አርግልኝ::

#አማኑኤል #ጌታዬ ሆይ ልቤ ላይ ዳናውን የተወው ለቅሶዬ መከፋቴን ይነግርኃልና ስማው፤ ስለ ሥጋ መኖርን አላስተማርከኝምና ስለ ሥጋ አላውራ፤ ማንም ያሻው ሁሉ በትልቅ እመጫት የሚያስገባብኝ አልሁን፤ ተሸራርፈው እያለቁ ነገር ግን ጡረታ እንዳልወጡ ባሊዎች አሊያ ሁሉም ወሬ ሲከካባቸው ከንፈራቸውን የሸራረፈባቸው በቡና የወየቡ ሲኒዎች ሆኜብሃለውና ከኃጥያትና ከሰው የሐሜት ዝተት አሳርፈኝ፤ ክዳናቸው የራሳቸው እንዳልሆነ ጀበኖች በትንሽ እሳት እንደሚገነፍሉ እኔም በሞትህ ክብር ባከበርከው ክቡር ሕይወቴ ላይ ክዳኔ ባልሆነው በዓለም ምቾት ተተብትቤ በትንሽ መከራ ተፈቅፍቄብሃለውና ውለታህን ከፊቴ ሳልልኝ::

#በዓለ #ወልድ #ሆይ የውስጡን ቡሽነት በኮርኪ እንዳጠነከረ በርጩማ የውስጤን ደካምነት በአንተ ጠንክሬና አምሬ ለሰውም ሐሳብ ጭንቀት ማስቀመጫነት ልትረፍ፤ በተቦረተፈ ፌስታል እንደታዘሉ ልብሶች ገበናዬ ወቶ መች እንደሚዘረገፍ ለሚጠባበቁኝ ሰብሰብ አርገህ እሰረኝና ምህረትህን ይዩብኝ፤ ጭንቅላቴ ላይ በሆዴ ከመተኛት አውጣኝ፤ ለጅቦች እንደሚያደላው የአገሬን ሕግ አልምሰል፤ ለእንቅልፌ ጣፋጭ ሕልም የሰጠኸው አንተ ነህና ተመስገን። አሜን ወአሜን ለይኩን ለይኩን አሜን ጌታችን ሆይ ከእመልዑል ጋር ናልን ተመልሰህ!

የቅድስት ሥላሴ ፍጡር
የእመብርኅን ባሪያ
ባለ ከበሮው ኪሩብኤል!
ቸሩ መድሃኒአለም ከከበቡን ችግሮች ያውጣን
3.0K views04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 23:00:57 ከቶ ምን ይረባል ጭካኔን ማብዛት!
ፈጥኖ ለሚጠፋው ለዚህ አለም ቤት፣
በቋንቋ በጎሳ መከፋፈል ሞት ነዉ፣
የእንጨት ዘር አይቀርም እንኳን ሰዉና ሰው።
6.5K views20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 07:30:58
እመብዙኀን ሆይ ከባዘቶ ለሚጠራው ንፅህናሸ
ሰላም እለዋለው!
እመብርሃን ሆይ ባለቀዉ ታሪኬ ላይ አንቺ ጀምሪ፤ ውስጤን ለመብላት የላይ ቆዳዬን ልጠው አይጣሉት፤ በምስጋናሽ እንጂ በወይን ጠጅ አልስከር፤ እንዳላሸንፋት ዓለም ገለባ ሆና የሸፈነችውን ስንዴነቴን በእርዳታሽ ወቅተሽ አርግፊያት፤ ባንቺ ያረኩት ተስፋ በነዋይ ተስፋ እንዳይሻግት ተስፋዬን ብርሃንሽን አብሪባት፤ በማርያም ስምሽ ተምጬ እንደተወለድኩ በማርያም ስምሽ ልገነዝ።

የልቤ ሰላም ሆይ በየ ብናኝ ኮሽታው፣ በቀጭን ወፍራም መስመሩ፣ በጎሊያድም ይሁን በየተራ ወታደሩ የስምሽን መቀነት አልፍታ፤ አንቺን የምዘነጋበት፣ ክብርሽን ለመርሳት የምጨነቅበት የሕይወት ትርክት አይኑረኝ፤ ተጉመጥሙጣ ሳተፋኝ የጎረስኳትን ዓለም አስተፊኝ፤ ሁሌም በምልጃሽ ልቃኝ፣ የሕይወቴን በገና አንቺ ደርድሪው፣ የውስጤን ማሲንቆ አንቺ ቆርቁሪው፣ የእምነቴን ዋሽንት አንቺ ወሽቺው፣ የእኔነቴን ከበሮ አንቺ ምቺው፣ አማናዊው ቅዱሱ መላእክ ኩሩብኤል አምላኩን በጀርባው እንደገለጠ፤ በኔ ኃጥያተኛው ኪሩብኤል ላይ አዲስ መቅደስ ሰርተሽ በጀርባዬ አትሮስ ተገለጭ።

ቋንቋዬ ሆይ አንቺ እንደሰው አይደለሽም የቅርብ ዘመዴ ነሽ በጥቅም አግንነሽ በማጣት አታኮስስሺኝም፤ ደመናውን አይተሽ አትፈርጂብኝም፤ በልብ የማወራሽ ቋንቋዬ ነሽና አፍ ሳልከፍት መልሴ ነሽ፤ በስሜ ሳይሆን በስምሽ ይጥሩኝ፣ በእያንዳንዱ የህይወት ታሪክ ግልገሉም፣ ጠቦቱም፣ በጉም ሁኚ፤ አንቺ በሌለሽበት ጉባዬ እንኳን አካሌ ስሜ አይገኝ። አሜን ወለላይቱ ሆይ ከተወዳጅ አምላክ ልጅሽ ጋር ስመጪ ምልጃሽ አይዘንጋኝ!

የቅድስት ሥላሴ ፍጡር
የእመብርኅን ባሪያ
ባለ ከበሮው ኪሩብኤል!
የድንግል ማርያም ምልጃ አይለየን አሜን
8.7K views04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 07:02:31
ቀኑ 16 ነው !!!
ስሟ ኪዳነምህረት ነው

ሰማያዊት ፍጡር እንዳንላት የአዳም ልጅ ናት ፡፡
ምድራዊት እንዳንላት ፈጣሪን የወለደች ንጹህ ፡ ብፅዕት ናት
ስጋ ለባሺ እንዳንላት እሳትን ወልዳለች ፡፡
መለኮታዊት እንዳንላት የአዳም ዘር ናት ፡፡
ሴት እንዳንላት ከሴቶች የተለየች ናት ፡
መልአክ እንዳንላት የሄዋን ልጅ ናት ፡፡
ሰው እንዳንላት ከኃጢአት ፍፁም የነጻች ናት ፡
መልአክ እንዳንላት የፈጣሪ አምሳል ናት ፡፡
ሳትቃጠል እሳትን ያዘለች እጸ ጳጦስ ፡
አዳምን ከሲዖል ያወጣች እጸ ምህረት፡
ኖህን ከሞት ያተረፈች እጸ ሒወት ፡
በላዕየ ሰብዕን ከፍዳ ያወጣች እጸ ጽድቅ፡
ለቅዱሳን ጥበብ የሰጠች እጸ ጥበብ
ለባ ህታውያን ጉልበት የምትሰጥ እጸ ጉልበት
እናት እንዳንላት እናት የወለደችውን ትሰለቻለች፡፡
አባት እንዳንላት አባት የወለደውን ይከዳል፡፡
እመቤታችን ለማመሳጠር ቋንቋ አልተፈጠረም፡፡
ምን አልባት በብሄረ ብጹኣን !
ምን አልባት በብሄረ ሕያዋን !
እሷን የሚገልጽ ፊደላት ይኖራሉ ::

የቅድስት ኪዳነምህረት አማላጅነት አይለየን
14.7K views04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ