Get Mystery Box with random crypto!

💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የሰርጥ አድራሻ: @join_maryam_amalajinet_telegram
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.51K
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ቻናል አላማ ስለ ድንግል ማርያም,ፃድቃን,መላእክት እና ሰማእይታት አማላጅነትና ገድል ተአምራታቸውን እንዲሁም ክብራቸውን መመስከር ነው። ለህይወታችን ለሚገጥሙን ፈተናዎች አስተማሪና ጠቃሚ የሆኑ መልእክቶች ይገኙበታል።

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-07-26 07:23:03
#ቅዱሰ_ገብርኤል_ሆይ_ሕፃኑ_ቄርቆስና አንጌቤናዊቷ እናቱ እየሉጣን በንፍር ውሃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው እኛን ወዳጆችህንም በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን የጥፋት፣ ወጥመድ አስወግድልን፡፡
የሰይጣንን ፈተና የምናልፍበትን እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነበዩ ዳንኤል አስተምረን አሜን
14.5K views04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 11:02:49 #አመቤቴ_ሆይ
ከልጅሽ ሌላ ባለመድኃኒት አልሻም፣ ከጸሎትሽም ረዳትነት በቀር ደግሞ ኃጠአቴን የሚያስተሠራይልኝ አልፈልግም። ንጽሕት ሆይ ከርኩሰቴም ከዕዳ በደሌም ሁሉ ንጽሕ አድርጊኝ፨ ከሥጋና ከነፍስም ቁስሌም ፈውሽን።
ለደዌ መድኃኒት ይሹለታል ለቁስልም አቃቂር መልካሙን ቅመም ይፈልጉለታል የኃጠአት ቁስል ግን ያለ ልጅሽ ፈቃድ አይጠገንም።
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
5.2K views08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 07:22:34
16
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
እንደወተት አንጀትን ለሚያርስ ልብን፤ ለሚያቀዘቅዝ የመልካም ወተት ስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል እያልኩ ሰላም እላለሁ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ርግብየ ርግብየ እያለ የሚያመሰግንሽ የጥበበኛው ሰሎሞን ርግብ ነሽና ድንቁርና ረኃብ እንዳይጸናብኝ እህል ጥበብን መግቢኝ።

እመቤቴ  ሆይ፤
ኀጥእን ለጥፋት የማይመኝ ቂም በቀልን የማያውቅ ልብሽ ፍጹም የዋህ ነው።
ስለዚህ ይቅርታ ልማድሽ ነውና ይቅር በይኝ፡፡ በልቤ ውስጥ ያለውን ምኑን ስንቱን እነግርሻለሁ? ኅዘኔን ጭንቀቴንም አንች ታውቂዋለሽና፡፡
መልክአ ኤዶም
የኪዳነምህረት ምልጃ አይለየን
9.5K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 07:08:50
እግዚአብሔር የሚፈሩትን እንደ አጥር  ሆኖ የሚጠብቃቸው እንደዚህ መልአክ ማነው? በእሱ የሚያምኑትንስ ከጭንቅ የሚያወጣቸው ማነው? ይህ ቅዱስ ሚካኤል አይደለምን?
ድርሳነ ሚካኤል
የቅዱስ ሚካኤል ምልጃና ጥበቃ ለዘወትር አይለየን ገናና የሆነ የመላእክት አለቃ
ቅዱስ ሚካኤል ልመናውና አማላጅነቱ ፈጽሞ ይጠብቀን፡፡
ከጽኑ ጠላት እጅ በክንፎቹ ጋርዶ ይሰውረን ለዘለዓለሙ አሜን
9.9K views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 20:10:11 ድሮ ልጅ እያለን ጭራቅ መጣ እየተባልን እየፈራን አድገናል የትናንቱ ትንብያ ጭራቅ ዛሬ እምናየው ነው።
4.9K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 07:11:02 21
የብርሃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትወጂኛለሽን? ብየ አልጠይቅሽም ፍቅርን የወለድሽ አንቺ ለአለሙ ሁሉ ፍቅርሽ የበዛ ነውና፤ አትናፍቂኝምን? ብየም አልጠይቅሽም፡ ዘወትር እኔን ለመጠበቅ ከጎኔ እንደማትለይ አውቃለሁኝና ፤ሆኖም እመቤቴ ሆይ፦ እንደቶማስ አይሽ ዘንድ በእጅጉ እጓጓለሁ የቶማስ ንፅህናና ቅድስና ግን የለኝም፡ እንደ ዮሐንስ ከጎንሽ ልሆን እጓጓለሁ፡ የዮሐንስ ፀጋ ግን የለኝም ፤ እናቴ ሆይ ፦ እንደ ኤልሳዕ የልቦናየ አይን በርቶ ሰማያዊ ክብርሽን ላይ አልተቻለኝምና አዝናለሁ ኤልሳ በፀሎት ሃይል የግያዝን አይን እንዳበራ አንቺም አይኔን ታበሪልኝ ዘንድ ሃይልሽን በእኔ ላይ አበርቺ፡፡ ድንግል ሆይ፦ ይህን የምል የእምነት ማረጋገጫ ፈልጌ አይደለም ፡ በልጅሽ መሰረትነት የታነፅኩኝ በልጅሽ ስምም የተጠመቅኩኝ ነኝና፤ ነገር ግን ስለምትናፍቂኝ ይህን አልኩኝ፦ ስለዚህም ነይ ነይ እምየ ማርያም እያልኩኝ እንደ እናቶቼም እለምንሻለሁ፡፡ የብርሃን ልብስሽን ለብሰሽ ነይ፡ የክብር አክሊልሽን ደፍተሽ ነይ፡ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ነይ እናይሽ ዘንድ ነይ፡፡ መኃ.4:10፤ እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት መልካም ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እንዴት ይሻላል! የዘይትሽም መዓዛ ከሽቱ ሁሉ ይበልጣል
የድንግል ማርያም አማላጅነት የልጇ ምህረት አይለየን
10.7K views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 08:12:11 አንድ የቆሎ ተማሪ ነበር ይህ ተማሪ ከሌሎች እሱን መሰል ተማሪዎች
የሚለየው ስለ ማርያም ስለ እመብርሃን ብሎ ከለመነ በኋላ ያገሬው ሰው
ሲሰጡት
" ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ "
ብሎ መርቆ ይሄዳል፡፡
እናም ይህ የቆሎ ተማሪ ትምህርቱን እየተማረ የተዘከሩትንም ' ደግም ለራሱ
ክፉም ለራሱ'
እያለ ሲኖር ባንድወቅት ወደ አንዷ ሴትዮ ቤት ገብቶ "ስለ ማርያም ስለ ወላዲተ
አምላክ ተዘከሩኝ" ብሎ ሲለምን የቤቱ ባለቤት ቁራሽ እንጀራ አውጥታ
ተዘከረችው እሱም የለመደው ነውና
"ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ" ብሎ መርቆ ይሄዳል በዚህ ግዜ ሴትዮዋ
"እንዴት ስዘከረው እግዚአብሔር ይስጥልኝ ብሎ መመረቅ ሲገባው
'ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ' ይለኛል" ብላ ትናደዳለች፡፡ "እንዲህ ከሆነማ
ጥሩ ብላ ነገ ሲመጣ አሳየዋለሁ" ብላ ትፎክርበታለች በነገታውም ወደ አመሻሹ
ለእራት የሚሆነውን ሊለምን ወደ መንደሮቹ እንደለመደው "ስለ ማርያም" እያለ
ሲሄድ ሴትዮዋም በጎማ ጠላ አዘጋጅታ ጠላው ውስጥ መርዝ ጨምራ
ጠበቀችው ተማሪውም እሷ ቤት እንደደረሰ ስለ ማርያም ስለ እመብርሃን ብሎ
ደምፁን እንዳሰማት ወዲያውኑ ያዘጋጀችውን ጠላ የያዘውን ጎማ አውጥታ
ሰጠችውና ከዛው ቁጭ ብሎ ከጠጣው መርዙ ሊገለው ስለሚችል "በል እዚህ
ቁጭ ብለህ ከጠጣኸው ስለሚመሽብህ ከቤትህ ሄደህ አረፍ እንዳልክ ጠጣት፡፡
እንዴት ያለች ጠላ መሰለችህ" ብላ ትልከዋለች፡፡ "እሱም ደግም ለራሱ
ክፉም ለራሱ " ብሏት ይሄዳል "እስኪ ደግም ሆነ ክፋት ለራስ ከሆነ እናያለን"
ብላ በውስጧ ሞቱን አስባ ተሳለቀችበት፡፡ እሱም የተዘከሩትን ምግብም ሆነ
መጠጥ ይዞ ወደ ማደርያው ጉዞውን ጀመረ በመንገድ ላይ የሴትዮዋ ልጆች
በረሃ ቆይተው በጣም ደከሟቸው ከተማሪው ጋር ተገናኙ ወደ ተማሪው ቀረብ
ብለው "እባክህን በርሃ ቆይተን በጣም ደክሞን መግባታችን ነውና እቤት
እስክንደርስ የውሃ ጥማችንን ቢያስታግስልን ከያዝከው መጠጥ ትንሽም ቢሆን
አጠጣን" ብለው ሲለምኑት "እኔም ለምኜው ነው ደግነትም ለራስ ነው" ብሎ
ከያዘት ጎማ እንዲጠጡ ፈቀደላቸው ሁለቱም ልጆች ከጎማዋ እንደጠጡ
ወደያው ይሞታሉ ይህን ጊዜ እሪታው ቀልጦ የመንደሩ ሰው በሙሉ ይሰበሰቡና
ግማሹ ዱላ ይዞ ደብድበን ካልገደልነው
ገሚሱም በድንጋይ መወገር አለበት
የተቀሩት ደግሞ ለህግ መቅረብ አለበት ሲባባሉ ሴትዮዋ የመንደሩን ግርግር
ሰምታ ስትመጣ ሁለቱም ልጆቿ ሞተው መርዝ ከጠላ ጋር ቀላቅላ የሰጠችውም
ተማሪ ሰዎች እያመናጨቁ ይዘውት ወደ ህግ እናቅርበው ብለው ሲወስዱት
ታያለች ይሄኔ ነበር 'ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ' የሚለው ነገሩ ትዝ
ያላት ሴትዮዋም "በሉ የያዛችሁትን ተማሪ ልቀቁት የዚህ ሁሉ ችግር ምክንያት
እኔው እራሴው ነኝ" በማለት የሆነውን ነገር ሁሉ ተናግራ "በገዛ ክፋቴ የገዛ
ልጆቼን የገደልኩት እኔው እራሴው ነኝ እናም ይሄ ሰው ንፁህ ሰው ነው ልቀቁት"
ብላ እራሷን ለህግ ሰጠች፡፡
እውነትም ደግም ሆነ ክፉ መሆን ለራስ ነው ክፉ መሆን በቅድሚያ የሚጎዳው
እራስን ነውና ደግ እንሁን ከደግነት በላይ መልካም ነገር የለምና።
10.6K views05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 12:02:34 አንድ ስሙን የማልጠቅሰው አንድ ታዋቂ ሚዲያ ስለሮቦት ሚስቶች ውሸት ነው ብሎ ሲመሰጥ ዐይቼው ሳቄን አጭሮኝ አለፍኩት:: ለማንኛውም ትንቁን መራር ሃቅ ላውርድላችው እስከ ፳፻፶፪(2052)ዓ.ም በዓለም በተፈጥሮ ስርዓት የተደነገገው የሰው ልጅ ትዳር ሰው ከሮቦቶች ጋር የሚጋባበት መጠን ይበልጣል የሚል መረጃ አለ:: ይኼ የሴኬሬት ሶሳይቲው አንዱ የሕዝብ ቅነሳ መንገድ ነው::

እኔ ሰው ግርም የሚለኝ ይኼ ዜና ብርቅ ሆኖ መነገሩ ነው:: በጃፓን ከሮቦቶች ጋር የቀለጠ ፍቅር ከተወደቀ እኮ ቆየ:: ወገን ንቃ ዕውነት አይደለም የሚልህ ሰው ዕውነት እንኳ ባይሆን መንገዱን ጠርጥረኸ አካሄድን እንድታርም የማይጋብዝ ነው:: በነገራችን ላይ ኢ-አማኝ አድርገው ራስ ወዳድ ያደረጉት የምዕራባዊያኑ ሕዝብ በዲግዶግ (በአርቴፍሻል ራስን ማርኪያ) ፍቅር ከወደቀ ዓመታቶች ነጎዱ እና ሮቦት ቢያገኝ ራሱን ለማጋባት የሚሽኮረምም ይመስልሃል? በሰዶምነት በረከሰ የኃጥያት ጥግ በነካ ስብህና የሮቦት ሚስት አይፈበርክም አያገባም ይኸንንም ኃጥያት ይንቀዋል ብለው ማሰብ በግድ ጅል እንዲሉ ተጋብዘሃል ማለት ነው:: የዓለም መሪ በኃጥያተኞች ተይዞ ወደ ሲዖል እየነዱን ለማወቅ ነብይ መሆን አያሻም:: ለማንኛውም ኤለን መስክ በብር የተለበጠ ልቡሰ ሥጋ አጋንት መሆኑን አለመረዳት ቅጥፈት ነው::

«የሮቦት ሚስቶች ይህን ዓለም ሊቀላቀሉ ነው!

ኤሌን መስክ እና ኩባንያው የሮቦት ሚስት እየሰሩ ነው ። በመስከረም ፳፻፲፮(2016)ዓ.ም የሮቦት ሚስቶች ለዓለም ገብያ ለሽያጭ ይቀርባሉ ተብሏል ። ለአፍሪካ ገብያ ደግሞ በህዳር ፳፻፲፮(2016) ይቀርባሉ።

እነዚህ የሮቦት ሚስቶች ከወር አበባ ዑደት ጋር የሚሄድ ባትሪ ይጠቀማሉ ተብሏል ። ባትሪዎቹ ለሦስት ቀን ሙሉ ቻርጅ ይደረጉና ለአንድ ወር ያገለግላሉ ተብሏል ። ከሮቦት ሚስቶች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለማድረግ ደግሞ ፓስወርድ፤ ፓተርን ወይም አሻራ ያስፈልጋል ። ማንም ዘው ብሎ አይገባም ተብሏል።» አይገርም ኃጥያትን ታማኝ ሚስት ለማድረግ እንዳትወሰልትበት እግሯን መክፈቻ ሲያደርጉላት:: ይማረን ያውጣን!

የቅድስት ሥላሴ ፍጡር
የእመብርኅን ባሪያ
ባለ ከበሮው ኪሩብኤል!
12.2K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 06:36:30 #ግንቦት_1

#ልደታ_ለማርያም

በግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኀነት የሆነባት ናት። ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ። ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቅበሉም ነበርና።

እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ።

ክቡር እያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኀነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው።

በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ነው ደግሞም ሀብትና ስጦታ ማለት ነው።

በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
4.8K views03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 06:51:28
፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል?
፤ እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ።
፤ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ከመድኃኒቱ አምላክም ምሕረትን ይቀበላል።
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 24 ቁ4-5)
5.7K views03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ