Get Mystery Box with random crypto!

💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የሰርጥ አድራሻ: @join_maryam_amalajinet_telegram
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.51K
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ቻናል አላማ ስለ ድንግል ማርያም,ፃድቃን,መላእክት እና ሰማእይታት አማላጅነትና ገድል ተአምራታቸውን እንዲሁም ክብራቸውን መመስከር ነው። ለህይወታችን ለሚገጥሙን ፈተናዎች አስተማሪና ጠቃሚ የሆኑ መልእክቶች ይገኙበታል።

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-06-14 21:16:40
ከጎንሽ ተኝቶ የማታምኝው ልጅሽ
ከውሀ ውስጥ ወድቆ ከትቦ ሲያድርብሽ
እንዴት ሁነሽ ይሆን?

ደባብሰሽ ቀባብተሽ ያለሽን አጉርሰሽ
የሸኘሽው ልጅሽ በስስት እያየሽ
ምሳ እቃውን ትቶ አንድ ጫማ አውልቆ
ውሃ ሽታ ሲሆን ከትቦ ሸምቆ
እንዴት ሁነሽ ይሆን?

ለሰዓታት እድሜ ተምሮ እስኪመለስ የማያምነው አንጀትሽ
ለቀናት ሳታይው ያለበት ሳይገኝ ሲርቅብሽ ከዓይንሽ
እንዴት ሁነሽ ይሆን?

ጌታ ሆይ! እባክህ ተመልከታት
በድኑን አግኝታ ቀብራ እንኳን ይውጣላት።
እግዚአብሔር ያበርታችሁ
18.6K views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 08:46:25
ሰኔ ፆም ሰኔ 6 ይጀምራል
ጾመ ሐዋርያት / የሴኔ ጾም /
ቅዱሳን ሓዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም
ከመበተናቸው በፊት አገልግሎታቸው የተቃና እንዲሆን
የጾሙት ጾም ነው ፡፡
12 ናቸው ፡፡ ግን ዓለምን አዳረሷት ፡፡ መንፈስ ቅዱስን
ተቀብለናል ብለው ይበቃናል አላሉም ፡፡ ጾም ጨመሩበት ፡፡
መንገዳቸው ተቃና ፡ አውሬው ሰገደላቸው ፡ አንደበታቸው
እንደ ማር ጣፈጠ ፡፡
ዓልጫውን ዓለም በጨው / በስብከታቸው አጣፈጡት ፡፡
ክርስቲያን የአባቶቼ ጾም የኔም ነው ሲል ይህን ጾም ይጾማል
ፆሙን የበረከት ያድርግልን
20.6K viewsedited  05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 11:48:08 ድንግል ሴት ትፈልጋለህ ?

ምንም እንኳን ሰዎች ሁሉም ባይሆኑም ብዙ ሰዎች ግን የሚያገቧት ሴት ድንግል እንድትሆን ይፈልጋሉ። አንዳንዶች ደግሞ መፈለግ ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያ መስፈርታቸው ያደርጉታል ። ይህ እጅግ ደስ የሚያሰኝ አቋም ነው። ምክንያቱም የኹሉም ሰው አቋም እንዲህ ቢሆን ኖሮ ሴቶች ኹሉ በንጽሕና መኖርን ለወደፊት ትዳራቸው መቃናት ሲሉ ስለሚለማመዱት ነው።

ታዲያ ሚስቱ ድንግላዊት ሆና ቢያገኛት የሚመኝ ሰው እርሱም ድንግልናውን የጠበቀ ሆኖ መገኘት እንዳለበት ለአፍታም እንኳን ቢሆን መዘንጋት የለበትም። ስለዚህ ይህን የሚመኝ ራሱን ይጠብቅ። ካላገባኻት ሴት ጋር አንሶላ መጋፈፍን አትሻ። ልታገባ አንድ ቀን የቀረህ ቢሆን እንኳን ሳታገባት ይኽን መሞከር የለብኽም። በሰዓታትና በቅጽበት ውስጥ በእቅፍኽ ያለች እጮኛህ ያንተ ሚስት መሆን የማትችልበት ሁኔታ ይፈጠር እንደሆነ አታውቅምና። አንተ ራስህ ከነድንግልናህ የምትፈለግበት ጋብቻ ከፊተህ ይጠብቅሀል ።

እርሷም በምትሄድበት ቦታ ባሏ ከነ ሙሉ ክብሯ ይሻታል። ታዲያ ካላገባሃት ሴት ጋር ለምን ትተኛለህ ? ካላገቧት ሴት ጋር ምንጣፍ መጋራት በሰው ቤት መግባትና ከባለ ትዳር ሴት ጋር እንደ ማመንዘር ነው። ያላገባች መሆኗ ልዩነቱ ባሏን መቅደምህ ብቻ ነው። አንተ በሰው ትዳር እንዲህ የምተገባ ከሆነ ሌሎች ደግሞ አንተ የምታገባትን ሴት ከክብር አስንሰው ንጽሕነዋን ገፈው ያቆዪሀል። አንተ ድንግል ሳትሆንና የብዙዎችን ሕግ አፍርሰህ ድንግል ሴት መፈለግህ አያስገርምም ?

ሰው የራሱን ድንግልና ቢጠብቅ እግዚአብሔር ደግሞ በድንግልና የተጠበቀች ሚስት እንደ ፍላጎቱ ሊሰጠው ተስፋ ሰጥቷል። ሰው የራሱን ዕቃ ቢጠብቅ ለእርሱ የሚገባውን ዕቃ እግዚአብሔር በክብር ይጠብቅለታል ። በመጽሐፍ ቅዱስ ዕቃ የሚባለው አባለ ዘርዕ (ኀፍረተ አካል ) ነው። ቅዱስ ዳዊት በእውነት ከመጣን ጀምረን እኛ ሰውነታችንን ከሴቶች ሶስት ቀን ጠብቀናል የብላቴኖችም ዕቃ የተቀደሰች ናት ስለዚህ ዛሬ ዕቃቸው የተቀደሰች በመሆኗ እንጀራው እንደሚበላ እንጀራ ይሆናል 1ኛሳሙ 21:5 በማለት የተናገረው ቃል ኀፍረተ አካል ዕቃ እንደሚባል ያስረዳል።

የራሱን ንጽሕና የጠበቀ ሰው ለእርሱ የምትሆነው ሚስቱ ከነቅድስነዋ ከነንጽሕነዋና ከነሙሉ ክብሯ (ድንግልነዋ) እንደሚያገኛት ማወቅ አለበት ሲል ሐዋሪያው "ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን እቃ (ሚስቱ የምትሆነውን ) በቅድስናና በክብር (ከነድንግልነዋ) ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ" በማለት ይናገራል። "ዕቃ" የሚለው ኀፍረተ አካል መሆኑ ከላይ በማያሻማ መልኩ ተገልጿል። ስለዚህ ድንግልን ማግባት የሚፈልግ ሰው የራሱን ክብር መጠበቅ ይኖርበታል። (1ኛ ተሰሎንቄ 4÷5)

በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ
19.4K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 06:54:34
ድንግል ሆይ
ያንቺ ባርያ ነው የሚል በልጅሽ በደሙ ቀለም በልቤ ሰሌዳ ላይ ይፃፍልኝ
እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ ዝገቴን በቅድስናሽ በንፅህናሽ ወልውለሽ ንፁህ አድርጊኝ
አንቺ ከወደድሽኝ ልጅሽ አይጠላኝም
( አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ )
20.6K views03:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 17:58:18
ጌቴሴማኒ የሚገኘው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም መቃብር።
የህይወት እናት ድንግል ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፣
እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል።
የድንግል ማርያም በረከት ለኛም ይድረሰን
እኛም ደጇን ለመርገጥ ያብቃን
21.5K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 07:40:21
እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአለ እርገት አደረሳችሁ
25.3K views04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 08:33:54
የጌታየ እናት ድንግል ማርያም ሆይ ላመሰግንሽ ልቤ ይነሳሳል አንደበቴ ግን ይሰንፋል፤ ህሊናየ በፍቅርሽ ደስታ ተነሳስቷል አፌ ግን ቃል ያንሰዋል።
እናቴ ሆይ፦ ክርስቶስ ምንኛ ወደደን? አዛኝ እናቱን አንቺን ሰጥቶናልና ሃጥያታችን እጅግ ብዙ ቢሆን የአንቺ የፀሎትሽ ሃይልም ብዙ ነው።
በየቀኑ እንበድላለን በየቀኑም ንስሃ እንድንገባ አንቺን በህሊናችን እንመለከታለን። የዚህ አለም ውበት በእጅጉ ይስበናል የአንቺና የልጅሽ ፍቅርም በእጅጉ ይማርከናል፤ ወደ ኃጢአት እናመራለን ወደ አንቺና ወደ ልጅሽም እንመለሳለን። የልጅሽ ምህረቱ ብዙ ነው ያንቺ ፀሎትም ልዩ ነውና እንደጠፋን አንቀርም ፡ እንዳወዳደቃችንም
አንሰበርም፡፡
ድንግል ሆይ ድኩማን መሆናችን እጅግ እንዳደከመሽ አስባለሁ፤ የዘወትር በደላችንም አሰልቺ ነው አንቺና ልጅሽ ግን በእኛ ተስፋ አትቆርጡም፡፡
ድንግል ሆይ፦ ይህ የልጅሽ ፍቅር ከአእምሮ በላይ መሆኑ ድንቅ ነው፤ የአንቺም የእናትነት ፍቅር ብርቱ መሆኑ ልዩ
ነው።
ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ሆይ፦ ስለዚህ እወድሻለሁ ከፍ ከፍም አደርግሻለሁ። ከልጅሽ ጋር ሆነሽ ከእኔ እንዳትለይ አውቃለሁ። ይህም ለልቤ ደስታ ነው፡፡
አሜን ፀጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አሜን
27.5K views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 21:23:49 የኔስ ማኩረፊያዬ!
የእኔስ ማኩረፊያዬ! የኔስ የቁጭት መርዶ መጽናኛዬ ፣ የከባድ ኀዘኔ ጭነትና የጭንቀቴ መክፈያዬ፣ የደስታዬ መፍሰሻ፣ የብስጭቴ ማርከሻ ፣የእልሄ መታገሻ፣ እኔስ ያላንቺ ማን እናት አለኝ??አንቺው ነሽ እንጉርጉሮዬና ዜማዬ!!
እናት ዓለም የስሜ ዐርማ ፣የሕይወት ወዝ፣ የዓይኔ ማማ፣ የማትነፍጊ፣ የማታቅማሚ ፣ረኀቤን የምትራቢ፣ ጥማቴን የምትጠሚ፣ ቁስሌን የምትታመሚ።
የዘመን ቅርስ መክሊቴ!
የጌታዬ እናት እመቤቴ!
የሐዲስ ኪዳን መሠረቴ!
ቸሪቱ፣አዛኝቱ ፣አማላጅቱ ማርያም እወድሻለሁ!!
18.7K views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 07:07:33
አብሳሪው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ
እሳት የሆነ ቅናት
እሳት የሆነ መከፋፈል
እሳት የሆነ ዘረኝነት
እሳት የሆነ ክፋት
እሳት የሆነ የአለም ሀሳብ
እሳት የሆነ የርኩሰት ስራ
እሳት የሆነ የገንዘብ ፍቅር
እሳት የሆነ ጠብ ክርክር
እሳት የሆነ መገዳደል
እሳት የሆነ ባልጀራን መጥላት
እሳት የሆነ የአመፅ እንጀራ መብላት
እሳት የሆነ የወንድም ደም ማፍሰስ
እሳት የሆነ የስጋ ምኞት
እነዚህ ሁሉ ነግሰውብን ፍፁም ከእግዚአብሔር ርቀን በሀጥያት ረክሰን ወደ አዘቅት ወርደን ወድቀናልና
አብሳሪው መልአክ ሆይ በበትረ መስቀልህ እሳቱን አቀዝቅዘው , ለሀገራችን ለኢትዮጵያም ሰላምን ስጣት
ጠላታችን ዲያብሎስን ከእግራችን በታች ጣልልን አሜን
21.5K views04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 11:35:56 «እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት ሆይ»

....."በአካል ሦስት ሲሆን በመለኮታዊ ባሕርዩ በአንድነቱ ጸንቶ የሚኖር የብርሃን መገኛ እሱ እግዚአብሔር አብ ለቃል ኪዳንሽ የተሰጠውን ልዩ ክብር ብሩህ አድርጎ ያሳየኝ ዘንድ የቸርነቱ ጸዳለ ብርሃን ዓይነ ልቡናዬን ያብራልኝ። የቃል ኪዳኗ እመቤቴ ሆይ ከእግዚአብሔር በታች በሰማይም በምድርም አንቺ የሁሉ እመቤት ነሽ" ።
[መልክአ ኪዳነ ምሕረት]
22.8K views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ