Get Mystery Box with random crypto!

የጌታየ እናት ድንግል ማርያም ሆይ ላመሰግንሽ ልቤ ይነሳሳል አንደበቴ ግን ይሰንፋል፤ ህሊናየ በፍቅ | 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

የጌታየ እናት ድንግል ማርያም ሆይ ላመሰግንሽ ልቤ ይነሳሳል አንደበቴ ግን ይሰንፋል፤ ህሊናየ በፍቅርሽ ደስታ ተነሳስቷል አፌ ግን ቃል ያንሰዋል።
እናቴ ሆይ፦ ክርስቶስ ምንኛ ወደደን? አዛኝ እናቱን አንቺን ሰጥቶናልና ሃጥያታችን እጅግ ብዙ ቢሆን የአንቺ የፀሎትሽ ሃይልም ብዙ ነው።
በየቀኑ እንበድላለን በየቀኑም ንስሃ እንድንገባ አንቺን በህሊናችን እንመለከታለን። የዚህ አለም ውበት በእጅጉ ይስበናል የአንቺና የልጅሽ ፍቅርም በእጅጉ ይማርከናል፤ ወደ ኃጢአት እናመራለን ወደ አንቺና ወደ ልጅሽም እንመለሳለን። የልጅሽ ምህረቱ ብዙ ነው ያንቺ ፀሎትም ልዩ ነውና እንደጠፋን አንቀርም ፡ እንዳወዳደቃችንም
አንሰበርም፡፡
ድንግል ሆይ ድኩማን መሆናችን እጅግ እንዳደከመሽ አስባለሁ፤ የዘወትር በደላችንም አሰልቺ ነው አንቺና ልጅሽ ግን በእኛ ተስፋ አትቆርጡም፡፡
ድንግል ሆይ፦ ይህ የልጅሽ ፍቅር ከአእምሮ በላይ መሆኑ ድንቅ ነው፤ የአንቺም የእናትነት ፍቅር ብርቱ መሆኑ ልዩ
ነው።
ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ሆይ፦ ስለዚህ እወድሻለሁ ከፍ ከፍም አደርግሻለሁ። ከልጅሽ ጋር ሆነሽ ከእኔ እንዳትለይ አውቃለሁ። ይህም ለልቤ ደስታ ነው፡፡
አሜን ፀጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አሜን